Wollo Times

Wollo Times

Share

Photos from Wollo Times's post 04/05/2026

ፓኪስታን በአሜሪካ ቁጥጥር ስር የነበሩ የኢራን መርከበኞችን ልታስረክብ ነው

ፓኪስታን በአሜሪካ ቁጥጥር ስር የነበሩ 22 የኢራን መርከበኞችን ለቴህራን ልታስረክብ ነው
ፓኪስታን በአሜሪካ ጦር ተይዘው የነበረ የአንድ የኢራን መርከብ 22 አባላትን ዛሬ ሰኞ ለቴህራን እንደምታስረክብ አረጋግጣለች።

የእስላማባድ ባለስልጣናት ይህንን ውሳኔ "የመተማመን መገንቢያ እርምጃ" ሲሉ የገለጹት ሲሆን፤ ይህም በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ አካባቢ ያለውን ከፍተኛ ውጥረት ለማርገብ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

መርከበኞቹ በአሜሪካ የባህር ኃይል ቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ በፓኪስታን በኩል አልፈው ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ስምምነት ላይ ተደርሷል።

ይህ የፓኪስታን እርምጃ በቅርቡ በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ በተፈጠረው ወታደራዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ፍጥጫ ሳቢያ በኢራን እና በምዕራባውያን ሀገራት መካከል የሻከረውን ግንኙነት ለማለስለስ የሚረዳ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ተደርጎ ተወስዷል።

ርክክቡ ዛሬ ሰኞ እለት እንደሚከናወን የሚጠበቅ ሲሆን፤ እስላማባድ በቀጣናው ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ያላትን ፍላጎት የምታሳይበት እንደሆነም አስታውቃለች መባሉን የዘገበው አናዶሉ ነው።

Wollo Times

https://www.facebook.com/wollotimes12

30/04/2026

ሰበር ኢራን የአሜሪካን እገዳ በወታደራዊ ኃይል ታነሳለች።

የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር #ሞታኪ “የባህር ኃይል እገዳ ማለት የጦርነት አዋጅ ማለት ነው” ብለዋል።

የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስት ሞታኪ“ #ተዋጊዎቻችን ነገ ወይም በሚቀጥለው ሳምንት እርምጃ ሊወስዱ ይችላሉ።” ብለዋል ።

Wollo Times




https://www.facebook.com/wollotimes12

29/04/2026

ሰበር ሰበር 52 የኢራን መርከቦች እገዳውን ጥሰው አለፉ‼️

የትራምፕ እገዳ የት ነው ?
ባለፉት 72 ሰዓታት ውስጥ ብቻ 52 የኢራን መርከቦች ዩናይትድ ስቴትስ በኢራን የውሃ ክልል ላይ የጣለችውን እገዳ ጥሰው ማለፋቸውን የኢራን ፋርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።

​እስከ ሰኞ ምሽት 4፡00 ሰዓት በአካባቢው አቆጣጠር ያለውን የሳተላይት መከታተያ መረጃ ጠቅሶ የወጣው ዘገባ እንደሚያመለክተው መስመሩን ካለፉት መርከቦች መካከል 31ዱ የነዳጅ ጫኝ መርከቦች ሲሆኑ 21ዱ ደግሞ የጭነት መርከቦች ናቸው።

Wollo Times

https://www.facebook.com/wollotimes12

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Website

Address


America
Addis Ababa