Doc Book
01/05/2026
ታሪካቺን!
ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ጥቅምት 23 ቀን 1954 ዓ.ም ተመሠረተ ፡፡
13/04/2026
ይህን ያውቁ ኖሯል ? የደም ማነስ ምልክቶች ምንድን ናቸው ? የደም ማነስ ምልክቶች ከታየቦት ወደ ጤና ተቋም በመሄድ የጤና ባለሙያ ያማክሩ !
14/03/2026
አዲስ መረጃ
አዲሱ የአዲስ አበባ ከተማ የመንግስት ሠራተኞች አዋጅ (87/2017) ምን ይዞ መጣ?
ስለ ቅጥር፣ የብቃት ምዘና እና ጥቅማጥቅሞች
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት አገልግሎቱን ለማዘመንና በብቃት ላይ የተመሰረተ አሠራር ለመዘርጋት አዲስ አዋጅ አውጥቷል። እነዚህን ነጥቦች ይዘንላችሁ ቀርበናል፦
🔹 ቅጥር በብቃት ብቻ! ከእንግዲህ ቅጥር፣ የደረጃ ዕድገት እና ዝውውር የሚፈጸመው በዘፈቀደ ሳይሆን በ"ብቃት ምዘና እና ማረጋገጫ" ውጤት ላይ ተመስርቶ ብቻ ይሆናል። ብቃትን የሚመዝን ራሱን የቻለ ተቋምም በአዋጁ ተቋቁሟል።
🔹 የሙከራ ጊዜ ማሻሻያ አዲስ ተቀጣሪ የ6 ወር የሙከራ ጊዜ ይኖረዋል። ውጤቱ ዝቅተኛ ከሆነ ለተጨማሪ 3 ወራት ሊራዘም ይችላል፤ ከዚያም ካልተሻሻለ ስንብት ይሆናል።
🔹 ደመወዝ እና ጥቅማጥቅም
• እኩል ክፍያ፦ ተመሳሳይ ዋጋ ላላቸው ሥራዎች እኩል መነሻ ደመወዝ ይከፈላል።
• የዕርከን ጭማሪ፦ በየ2 ዓመቱ የሚደረገው የደመወዝ ጭማሪ በሥራ አፈጻጸም ውጤት ላይ የተመሠረተ ይሆናል።
• አበል፦ የመስክ ውሎ፣ የአየር ፀባይ እና የትርፍ ሰዓት ክፍያዎች በግልጽ ተደንግገዋል።
🔹 ልዩ ፈቃዶች ለጋብቻ፣ ለሐዘን እና ለፈተና በበጀት ዓመት ውስጥ 7 የሥራ ቀናት የሚከፈልበት ፈቃድ መፈቀዱ ለሠራተኛው ትልቅ እፎይታ ነው።
ስለ ሥነ-ምግባር፣ ስንብት እና ልዩ ድጋፎች
ለሴት ሠራተኞች የተሰጠ ልዩ ትኩረት
• በቅጥር እና በሥልጠና ሴቶች ቅድሚያ (Affirmative Action) ያገኛሉ።
• እያንዳንዱ መሥሪያ ቤት ለሴት ሠራተኞች የሕፃናት ማቆያ የማቋቋም ግዴታ አለበት።
• የወሊድ ፈቃድ በአግባቡ እንዲከበር ተደንግጓል።
ዲሲፕሊን እና ተጠያቂነት
• አገልግሎት ማዘግየት፣ ባለጉዳይ ማጉላላት እና ከሥራ ገበታ መቅረት ከባድ የዲሲፕሊን ቅጣት ያስከትላሉ።
• በሙስና ወይም በሥልጣን አለአግባብ መጠቀም የተገኘ ሠራተኛ አስተዳደራዊ እና የወንጀል ተጠያቂነት ይኖርበታል።
ከሥራ ስለመሰናበት
• በጤና እክል፣ በብቃት ማነስ (ተከታታይ ዝቅተኛ ውጤት) ወይም በዲሲፕሊን ምክንያት ስንብት ሊኖር ይችላል።
• የጡረታ መውጫ ዕድሜ 60 ዓመት መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በአስተዳደሩ ውሳኔ እስከ 5 ዓመት ሊራዘም ይችላል።
የቅሬታ አፈታት ሥርዓት ማንኛውም ሠራተኛ መብቴ ተጥሷል ካለ ለቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ወይም ለከተማው አስተዳደር ፍርድ ቤት አቤቱታ የማቅረብ መብቱ የተጠበቀ መሆኑን አዋጁ ይደነግጋል።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the practice
Website
Address
Addis Ababa