AGMAS MEDIA
14/04/2025
https://www.cafonline.com/caf-u-20-africa-cup-of-nations/news/final-draw-for-totalenergies-caf-under-20-africa-cup-of-nations-egypt-2025-to-be-held-on-sundayv/
ከ20 አመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ድልድል ይፋ ሆነ።
#በግብጽ አዘጋጅነት በሚካሄደው ከ20 አመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ 13 ሀገራት የሚሳተፉበትም ይሆናል።
የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌደሬሽን (ካፍ) በግብፅ ካይሮ ባወጣው ድልድል ምድብ አንድ ላይ አዘጋጇ ግብጽ ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ዛምቢያ ፣ ሴራሊዮን እና ታንዛኒያ ተደልድለዋል።
ጠንካራ ፉክክር ይደረግበታል ተብሎ በሚጠበቀው ምድብ ሁለት ናይጄሪያ ፣ ቱኒዚያ ፣ ሞሮኮ እና ኬንያ ሲደለደሉ በምድብ ሶስት ደግሞ ሻምፒዮኗ ሴኔጋል ፣ ዴሞክራቲክ ኮንጎ ሪፐብሊክ ፣ መካከለኛው አፍሪካና እና ጋና ተገናኝተዋል።
ለ25ኛ ጊዜ የሚደረገው ውድድር ሚያዚያ 19 ቀን እንደሚጀመር ካፍ አሳውቋል።
Final Draw for TotalEnergies CAF Under-20 Africa Cup of Nations, Egypt 2025 to be held on Sundayv The final draw for the TotalEnergies CAF Under-20 Africa Cup of Nations (AFCON), Egypt 2025 will be conducted on Sunday, 13 April at 17:00 local time (15:00 GMT). The tournament will be staged from 27 April to 18 May, 2025, with Sunday’s draw LIVE from the Egyptian Football Association headquarter...
11/03/2025
አንጋፋው ሙዚቀኛ አለማየሁ ፋንታ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
(አግማስ ሚዲያ)
ድምፃዊ፣ የግጥምና ዜማ ደራሲ፣ መሰንቆና ዋሽንት ተጫዋች፣ ክራርና በገና ደርዳሪ፣ የኢትዮጵያ የባህል ሙዚቃ መምህር የሆኑት አለማየሁ ፋንታ በህክምና ሲረዱ ቆይተው ትናንት መጋቢት 1 ቀን 2017 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡
ከ1960 ዓ.ም ጀምሮ በያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ውስጥ ከማስተማርም በዘለለ ትምህርት ቤቱ ሲከፈት የባህል ሙዚቃ ትምህርትን ለተማሪዎች እንዲሆን አድርገው ካሪኩለም በማዘጋጀት ከፍተኛ ሚናን ተጫውተዋል።
ውልደትና እድገታቸው በአሁኑ የዋግምራ ዞን ሰቆጣ አካባቢ ሲሆን፣ በልጅነታቸው በድቁና ማዕረግ ቤተክርስቲያንን አገልግለዋል፡፡
ሙዚቃን የጀመሩት በሀገር ፍቅር ቴአትር ሲሆን ከ1950 ዓ.ም ጀምሮ ለአስር ዓመታት ያህል በክፍሉ ሰርተዋል፡፡ የኢትዮጵያን የባህል ሙዚቃ በመወከል በአፍሪካ፣ በአውሮፓ፣ በአሜሪካና በእስያ በርካታ ሀገራትንም ተዟዙረዋል።
በእንግሊዝ፣ ስዊድን፣ ኖርዌይ፣ ጀርመን፣ ኦስትሪያና ሌሎችም በርካታ የአውሮፓ ሃገራት የባህል ሙዚቃ አምባሳደርነት ማዕረግን ያገኙ ሲሆን፣ ከዚህም በተጨማሪ በ1968 ዓ.ም ከዳካር የኔግሮ አርትስ ፌስቲቫል ሽልማት ከዩኔስኮ ለሙዚቃ ስራዎቻቸው እውቅና (Recognition by UNESCO
an Analogy of African music (UNESCO collection digital)) ከኮርያ ስፕሪንግ ፍሬንድ ሺፕ አርት ፌስቲቫል ዲፕሎማና የክብር ሜዳሊያና መሰል በርካታ ሽልማቶችንም አግኝተዋል::
አንጋፋው ሙዚቀኛ አለማየሁ ፋንታ በህክምና ሲረዱ ቆይተው ትናንት መጋቢት 1 ቀን 2017 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡
ስርዓተ ቀብራቸው በነገው ዕለት ፒያሳ በሚገኘው በገነተ ፅጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ከቀኑ በ9 ሰዓት እንደሚፈፀምም ታውቋል።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Address
Asmara Road
Addis Ababa
1000