Kumneger
20/03/2026
እነዚህ ዝርያቸው እየተመናመነ ያለው ኖርዘርን ዋይት ራይኖ በአሁኑ ወቅት ብዛታቸው ሁለት ብቻ ሲሆን ከማንኛውም አደን ለመጠበቅ ሲባል 24 ሰአት በጠባቂዎች ይጠበቃሉ!
15/03/2026
ኢራን የሆርሙዝ የባህር ስርጥ የተዘጋው "ለጠላቶቿና ለባልደረቦቻቸው" መሆኑን አስታወቀች
የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራቅቺ፤ ስልታዊ ጠቀሜታ ያለው የሆርሙዝ የባህር ስርጥ ክፍት ቢሆንም፣ "ለኢራን ጠላቶችና ለባልደረቦቻቸው" ግን ዝግ መሆኑን ገለጹ።
ሚኒስትሩ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፤ የባህር ስርጡ ለዓለም አቀፍ የንግድ መርከቦች ዝውውር ክፍት ሆኖ እንደሚቆይ ጠቁመው፣ ነገር ግን ከኢራን ጋር ግጭት ውስጥ ላሉ ወገኖችና ለደጋፊዎቻቸው የነዳጅ ጫኝ መርከቦችም ሆኑ ሌሎች የንግድ መርከቦች ማለፊያ እንደማይሆን በግልጽ አስታውቀዋል።
ይህ የአባስ አራቅቺ መግለጫ የወጣው በኢራን፣ በእስራኤልና በአሜሪካ መካከል ያለው ቀጠናዊ ውጥረት በከፍተኛ ሁኔታ በጨመረበትና የባህር ላይ ደህንነት ስጋት በገነነበት ወቅት ነው።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Addis Ababa