ITCOM

ITCOM

Share

17/09/2025

ለዊንዶዉስ /Windows/ 10 የሚቀርቡ ወሳኝ ማሻሻያዎች ከ28 ቀናት በኋላ ይቋረጣሉ::

አዲስ አበባ፤ መስከረም 6/2018፡- ማይክሮሶፍት ኩባንያ ከመጪዉ ጥቅምት 4/2018 ዓ.ም (October 14, 2025) በኋላ ለዉንዶዉስ-10 ምርቶች የሚያቀርበዉን ወሳኝ የሆኑ ማሻሻያዎች እንደማያቀርብ በድጋሚ ለደንበኖቹ አሳዉቋል።

ለዊንዶውስ-10 የደህንነት ማሻሻያ ሲቋረጥ፤ ከዊንዶዉስ-10 ምርት ከዚህ ቀደም በየወሩ የሚያገኙት ደህንነትን (security)፣ የሲስተም መረጋጋትን (stability) ወይም ከአጠቃቀም ጋር ለሚፈጠሩ ክፍተቶች ጥገናዎችን ወይም ቴክኒካል ድጋፍን መስጠት ያቆማል።

በጥቅምት 4/ 2018 ዓ.ም (October 14, 2025) በኋላም የዊንዶውስ 10 ስሪት 22H2 (Home፣ Pro፣ Enterprise፣ Education፣ እና IoT Enterprise እትሞች) በሙሉ የአገልግሎታቸዉ እንደሚያበቃ ታዉቋል።

ማይክሮሶፍት እነዚህ የዊንዶዉስ-10 ምርት ተጠቃሚዎች ወሳኝ የሆኑ የደህንነት ዝመናዎችን በቀጣይነት ለማግኘት የዊንዶዉስ ምርታቸዉን ወደ ዊንዶዉስ -11 እንዲያሳድጉ መክሯል።

ነገር ግን የዊንዶዉስ-10 የደህንነት ማሻሻያዎች እንዳይቋረጥ የሚፈልጉ ተጠቃሚዎች ለዊንዶዉስ ሆም (Home) ተጠቃሚዎች 30 የአሜሪካን ዶላር እንዲሁም ለኢንተርፕራይዝ (Enterprise) ተጠቃሚዎች ደግሞ ለእያንዳንዱ መሳሪያ በአመት 61 የአሜሪካ ዶላር በመክፈል ወርሃዊ ዝመናዎችን ማስቀጠል እንደሚችሉ አሳዉቋል።

በመሆኑም የዊንዶዉስ-10 ተጠቃሚዎች ጊዜዉ ከማለፉ በፊት የምትጠቀሙበትን የዊንዶዉስ ምርትን ወደ ዊንዶዉስ-11 ከፍ በማድረግ የደህንነት ማሻሻያዎች መቋረጠቻዉን ተከትሎ በሳይበር ጥቃት ተገላጭነት ሊደርስ የሚችለዉን አደጋ እንድትከላከሉ ለማሳወቅ እንወዳለን።

09/09/2025

ኮምፒዉተር የሚዘጋበት ወይም ክራሽ የሚያደርግበት 5 ምክንያቶች
👇👇👇👇👇👇👇👇
🔷🔶1. የሀርድዌር መቃረን
ለ Windows ክራሽ የማድረግ ዋነኛው ምክንያት የ Hardware መቃረን ነው፡፡እያንዳንዱ Hardware ክፍሎች ለመግባባት IRQ(interrupt request channel) ያስፈልጋቸዋል፡፡ እነዚህ IRQ ለየሀርድዌሩ የተለዩ ወይም የተነጠሉ መሆን አለባቸው፡፡ ለምሳሌ አንድ ፕሪንተር IRQ 7 ሲኖረው ኪቦርድ ደግሞ IRQ 1፡፡እያንዳንዱ ሀርድዌር የራሱ የሆን IRQ ለመያዝ ጥረት ያደርጋል፡፡ ግን ብዙ የሀርድዌር እቃዎች ስንጠቀም ወይም የሀርድዌሩ ሶፍትዌር በስርዓት ካልተጫነ ሁለት ሀርድዌሮች ተመሳሳይ IRQ ሊጋሩ ይችላሉ፡፡ በዚህም ሰዓት ሁለት የሀርድዌር ዕቃዎች በተመሳሳይ ሰዓት ለመጠቀም ስንሞክር ክራሽ ሊከሰት ይችላል፡፡
🔷🔶2. የተበላሸ ራም
ራም Ram (random-access memory) ችግሮች ዋናው የብሉ እስክሪን ኦፍ ዴዝ (blue screen of death) ዋና መንስኤ ሲሆን የሚያሳየው መልእክት ፋታል ኤክሰብሽን ኢረር( Fatal Exception Error) የሚል ነው፡፡ ፋታል ኢረር የሚነግረን አሳሳቢ የሀርድዌር ችግር አለ ማለት ነው፡፡ አንዳንዴ የሀርድዌር ክፍል ስለተጎዳ መቀየር እንዳለበት ይናገራል፡፡ በራም የሚመጡ ችግሮች ብዙ ግዜ የራሙ ከኮምፒዉተሩ ጋር ሳይጣጣም ሲቀር ነው፡፡ ይህም ማለት ለኮምፒዉተር የራም ስሎት ጋር ሳይመጣጠን ሲቀር ፤ የራሱ ያልሆነ ሞዴል ስንጠቀም እና የተለያየ አይነት ራም በአንድ Computer ውስጥ ስንጠቀም ነው፡፡ለምሳሌ 70ns ለይ 60ns ራም ስንጠቀም ኮምፒተሩን ፍጥነት ይቀንሳል፡፡ይሄ ደግሞ ራሙን ከአቅሙ በላይ ይጫነዋል በዚህ ግዜ window ክራሽ ያደርጋል፡፡
🔷🔶3. ባዮስ ሴቲንግ( BIOS settings)
እያንዳንዱ ማዘር ቦርድ ሲመረት የራሱ የሆነ የተለያዩ ቺፕሴት ሴቲንግ አብሮት ይጫናል፡፡ እነዚህን ሴቲንግ ለመጠቀም በኮምፒውተራችን ኪቦርድ ላይ F2 ወይም F10 (እንደ ኮምፒዉተሩ ይለያያል) ኮምፒዉተሩ ስንከፍት ከጥቂት ሰከንድ በኻላ በመንካት ሴቲንጉን አክሰስ ማድረግ ይቻላል፡፡ ነገር ግን አንዴ ባዮስ ዉስጥ ከገባን ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አለብን፡፡ ማንኛውንም ሴቲንግ ከመቀየራችን በፊት ፎቶ ወይም ወረቀት ለይ ሴቲንጎቹን ማኖር አንድ ያበላሸነው ነገር ካለ በቀላሉ መቀየር ያስችለናል፡፡ብዙን ግዜ የባዮስ ችግር የራም ላተንሲ ችግር ነው፡፡ የድሮ ኮምፒዉተር ራም ላተንሲ 3 ሲሆን የቅርብ ግዜ ራሞች ደግሞ ላተንሲ 2 ናቸው፡፡ ይሄንን ሴቲንግ በምንቀይርበት ጊዜ ኮምፒዉተሩ ክራሽ ያደርጋል ወይም ፍሪዝ ይሆናል፡፡
🔷🔶4. ቫይረስ
ቫይረሶች የኮምፒዉተር ፕሮግራም ሲሆኑ እራሳችውን በማብዝት ወይም ኮምፒዉተር ፋይሎች ላይ በማጣበቅ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርሱ ይችላሉ፡፡ ቫይረሶች የትእዛዞች ስብስብ ሆኖ እራሱን በሌላ የኮምፒዉተር ፕሮግራም ያጣብቃሉ(ብዙ ግዜ ኦፕሬቲንግ ሲስተሙን)፡፡ ኮምፒዉተራችን ውስጥ ቫይረስ ሲያጠቃ የኦፕሬቲንግ ሲስተሙን ፋይል የመቀየር ሀይል ስላለው ኮምፒዉተሩን ክራሽ ወይም ፍሪዚ ሊያረግ ይችላል፡፡
🔷🔶5. መጋል
በኮምፒዉተራችን ዉስጥ ካሉ ሀርድዌሮች በጣም አስፈላጊው እና ዋናው ሲፒዩ ነው፡፡ ሲፒዩ በኤሌትሪክ ሃይል የሚሰራ ሲሆን ካለው ውስብስብ የትራዚስተር ብዛት አማካኝነት የሚፈጥረው ከፍተኛ ሙቀት ሲፒዩን ሊያበላሸው ወይም ከጥቅም ውጪ ሊያደርገው ይችላል፡፡ ሲፒዩ ብዙ ጊዜ ከማቀዝቀዣ ቬንትሌተር ከኮምፒዉተራችን አንድ ላይ ይመጣል፡፡ እነዚህ ቬንትሌተር ከተበላሹ ወይም ሲፒዩ ካረጀ የኮምፒዉተራችን ሲፒዩ መጋል ይጀምራል፡፡ ይህ ደግሞ በ

Photos from ITCOM's post 09/09/2025

ሀገሬ እንኳን ደስ አለሽ

Baga gammaddan biyya koo

በቃላት ስለማይገለጥ ስጦታዉ እግዚያብሄር ይመስገን። ዛሬ ደስስስስስስስስስ ብሎኛል ጌታ ኢትዮጵያንና ዜጎቿን እንዲሁም መሪዋን ስለረዳ ግድቡ ስላለቀ። እንኳን ደስ አለን
ጠ/ሚኒስትራችን እናመሰግናለን🙏🙏🙏🥰

Baga gammaddan biyya koo

Want your business to be the top-listed Engineering Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Culinary Team

Attire

Telephone

Website

Address


Gereji
Addis Ababa