Islam selam
29/03/2025
BREAKING NEWS: Eid Al Fitr 1446/2025 is tomorrow: Sunday, 30 March 2025
The Crescent for the month of Shawwal 1446 was SEEN in Saudi Arabia today subsequently tomorrow is the beginning of the month of Shawwal 1446
26/05/2023
በወቅታዊ ጉዳይ #ከአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ።
💫💫💫💫💫💫💫💫
መብቱን በሰላማዊ መንገድ ለመጠየቅ በወጣ ህዝብ ሙስሊም ላይ የተወሰደው እርምጃ ፍፅም ተቀባይነት የሌለው ፣ ኢ-ፍትሃዊና ኢ-ዲሞክራሲያዊ በመሆኑ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ያወግዛል።
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሸገር ሲቲ የመስጅድ ፈረሳ እንዲቆምና የፈረሱትም በአስቸኳይ መተኪያ እንዲሰጣቸው እንዲሁም በጉዳዩ ዙሪያ የሚመለከታቸው አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ በተደጋጋሚ በደብዳቤ ለሚመለከተው አካል ለማሳወቅ የተሞከረ ሲሆን የመስጅድ ፈረሳው ባለመቆሙ ህዝበ ሙስሊሙ ተቃውሞውን በዛሬው እለት በአደባባይ ድምፁን በሰላማዊ መንገድ አሰምቷል።
ይህንንም ሰላማዊ የመብት ጥያቄ ተከትሎ በታላቁ አንዋር መስጅድ የፀጥታ አካል በወሰዱት ኢ-ህገ መንግስታዊ እና ኢ ሰብአዊ እርምጃ የሰው ሂይወት አልፋል፣ብዙሃን ቆስለዋል።
በመሆኑም ይህንን አስከፊ ጥቃት የፈፀሙ እና ያስፈፀሙ የፅጥታ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ አጥብቀን እንጠይቃለን ።
በቀጣይም የሚመለከተው አካል በኦሮሚያ ክልል በሸገር ከተማ እየተከናወነ ያለውን ድርጊት እንዲያስቆምነና ወደ ውይይት በመምጣት ስር ነቀል የእርምትና እርምጃ ተጠናክሮ እንዲተገበር አጥብቀን እንጠይቃለን።
የሀይማኖት ጉዳይ እና የእምነት ተቋማት ጉዳይ ሁሌም ቢሆን በስክነት መታየት ሲገባው ከዚህ ቀደም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በእምነት በተቋማቱ ጉዳይ ሲከተሉት የነበረውን አካያሄድ እንደ ተሞክሮ ከመውሰድ ይልቅ በዚህ አከያሄድ የተሰራው አስነዋሪ ተግባር የሀገራችንን ብሎም የከተማችንን ሰላምና ደህንነት አደጋ ላይ እየጣለ ይገኛል።
በሸገር ከተማ መስጅድን በተመለከተ እየተከናወነ ያለው ድርጊት፣ሀላፊነት የጎደለው፣የህዝበ ሙስሊሙን ክብር ያዋረደ፣ሀገራችን ያለችበትን ነባራዊ ሁኔታ ያላገናዘበ፣የመንግስት የለውጥ ሪፎርምን ወደ ሀላ የሚመልስ በመሆኑ ጉዳዩ እንደ ሀገር ሊታሰብበት ይገባል።
በዛሬውም እለት በመስጅድ ፈረሳ ሳቢያ በሰላማዊ መንገድ መብቱን ለመጠየቅ በወጣው ህዝበ ሙስሊም ላይ በተወሰደው ኢ-ህገ መንግስታዊ እርምጃ ሒይወታቸው ላለፉ አላህ (ሱ.ወ) ጀነትን እንዲወፍቃቸው፣ለመላው ህዝበ ሙስሊም መፅናናትን እንመኛለን።
የከተማችንም ህዝበ ሙስሊሙ በቀጣይ ጉዳዩን በሰከነ መንፈስ እንዲከታተል አደራ እንላለን።
ግንቦት 18/2015
26/05/2023
ኢና ሊላሂ ወኢና ዒለይሂ ራጂዑን ‼
መርካቶ ጭድ ተራ ላይ አንድ ወንድማችን ህይወቱ አለፈ።
ሸሂድ ሆኗል‼
ጌታችን አላህ (ሱወ) ከእውነተኞቹ፣ ከሰማዕታቱና ከደጋጎቹ ጎን ይቀስቅሰው! አሚን!
ግፉ ከመጠን አለፈ
ኢስላማዊ ድህረ ገፅ
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the university
Website
Address
Addis Ababa