Edget Digital Marketing Services
Follow Our linkedin page for news updates and tips!
05/04/2023
ኢሚል ማረኬቲንግ (Email marketing)
ቀደም ባለው ፅኁፍ ስለ ዲጂታል ማርኬቲንግ እና ባህላዊ ማርኬቲነግ(ማስታወቂያ) ልዩነት እንዲሁመ ዲጂታል ማርኬቲንግ ስለሚሰጠው ዘርፈ ብዙ ጥቅም በተወሰነ መልኩ ለማየት ሞክረናል፡፡ በዛሬው ፅሁፋችን ደግሞ ከዲጂታል ማርኬቲንግ አይነቶች አንዱ ስለሆነው ኢሚል ማረኬቲንግ (Email marketing) ቀንጨብ አድርገን ለማይት እንሞክር፡፡
ኢሚል ማረኬቲንግ (Email marketing) ድርጅቶች ከነባር ደንበኞች እንዲሁም ወደፊት ምርት እና አገልግሎቶቻችንን ሊጠቀሙ ከሚችሉ ደንበኞች ጋር የተሻለ ግንኙነት ለመፍጠር የሚረዳን አንዱ ውጤታማ ከሚባሉ የዲጂታል ማርኬቲንግ ዘረፍ ነው፡፡ ኢሚል ማረኬቲንግ (Email marketing) የኢሜል አድራሻቸው ዝርዝር ላለን ደንበኞች ስለ ምርት እና አገልግሎታችን፣ አዲስ ስላመረትነው ወይም ለመስጠት ስለ ተዘጋጀንበት አዲስ አገልግሎት፣ ስለ ዋጋ ለውጥ ( ጭማሪ ወይመ ቅናሽ) ስለምርት እና አገልግሎት አጠቃቀም፣ በድርጅታችን አስራር እና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ስላደረግነው ለውጥ፣ እንዲሁም ወርሃዊ ሳምንታዊ አዳዲስ ወሬዎችን( ዜና መፅሄቶችን) በቀጥታ በአድራሻቸው በመላክ የምናስተዋውቅበት ዘዴ ነው፡፡
የኢሚል ማረኬቲንግ (Email marketing) ጥቅሞች፡-
1. ጎብኝዎችን በቀላሉ ወደ ደንበኞችነት ለቀየር ያግዘናል
በኢሜል መልኩ በምናደርገው ምርት እና አገልግሎትን የማስተዋወቅ ዘመቻ ዊብሳይታችን ላይ በምንደርገው የዋጋ ቅናሽ፣ ለሚደረግ ግዢ የነፃ ትራንስፖረት አገልግሎት፣ የቦነስ እና የስጦታ ማስታወቂያዎች የዊብሳይታችንን ጎብኝዎች በቀላሉ ደንበኛ እንዲሆኑ እና ፍላጎት እንዲያድርባቸው ማድረግ ይቻላል፡፡
2. ጠቃሚ መረጃዎችና ዜናዎችን ለደንበኞቻቸችን ለማጋራት ይጠቅመናል
በድርጅታችን፣ በተሰማራንበት ኢንዱስትሪ እንዲሁም በአገሪቱ ውስጥ ስላለው ተያየዥ የህግ የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ መስተጋብር ለውጦች እና አዳዲስ ነገሮችን በቋሚነት ለደንበኞቻችን በማጋራት ቤተስባዊ ትስስር መፍጠረና ዘላቂ ደንበኞችን ማፍራት እንችላለን
3. ደንበኞች እንደዬ ሁኔታቸው በመከፋፈል ቀጥታ ግንኙነት ለመፍጠር ያስችላል
ደንበኞችን በፍላጎታቸው፣ በፆታ፣ በእድሜ በአካባቢያወቸው በመከፋፈል እና ለእያንዳንዱ ክፍል ዪሚስብ እና የሚጠቀም መረጃዎች በማጋራት የተሻል ግንኙት መፍጠር ዛሬ ላይ ለምርት እና አገልግሎት ፍላጎት ያሳዩ ጎብኝዎች ነገ በቀላሉ ደንበኛ እንዲሆኑ ያስችላል፡፡
4. ግብረ መልሱን በቀላሉ ማውቅ መቻል
በኢሚል ስናስተዋውቅ ስንተ ደንበኛ ኢሜሉን እንደከፈት ምን ያህሉ አንባቢ ወደ ፈለግነበት ገፅ ገብቶ እንዳነበበ እና ምን አይነት ተግባራትን እንዳከናወነ እና ለምን ያህል ጊዜ እንደቆየ እንዲሁም ለመግዛት ያሳየውን ፍላጎት እና የምርት እይነት በቀላሉ መረዳት ስለሚያስችል ያለውን ዳታ በማጤን ማስተካከል ማረም እና ማሻሻል እንችላለን፡፡
ውጤታማ የኢሜል ግንኙነት እንዴት ማድረግ እንችላለን
• ለዚሁ አገልግሎት የተዘጋጁ ፕላት ፎረሞችን መጠቀም
• ጠቃሚ የሆኑ አድራሻዎችን ብቻ በመዘርዘር ማዘጋጀት እና መላክ
• አሰልቺ ባልሆነ መልኩ አልፎ አልፎ ብቻ መላክ
• ግብ ለይቶ ማስቀመጥ እና የምንልከው መልእክት ማሳካት ከፈልግነው ግብ ጋር የተሰናሰለ መሆኑን እርግጠኛ መሆን
• የምንልከው ኤሜል አይነት ለይቶ ማወቅ
• ኤሜል ከላክን በኋላ መከታትል እና አስፈላጊውን ግብረ መልስ መስጠት ነቸው
በሌላ ፅሁፍ እስክንገናኝ መልካም ቀን፡
ለማንኛውም የዲጂታል ማርኬቲንግ አገልግሎት እና ነፃ ምክር በስልክ ቁጥር 0923753535 በኢሜል [email protected] ማገኘት ይችላሉ፡፡ ለተጨማሪ መረጃ ዊብሳይታችንን www,edgetdigital.com ይጎብኙ ወይም በቴሌግራም ቻናላችን ቤተሰብ ይሁኑ t.me/EdgetDigital
Edget Digital Marketing and Promotion Let's work together for Mutual Growth! 🌐 Website Design and Development 🎯 Digital Marketing 📢 Social Media Marketing and management 🏗 SEO 🖱 PPC 🏷 promotional Items 📞 0923753535 🌐 www.edgetdigital.com 📩 [email protected]
05/04/2023
Edget Digital Marketing and Promotion is Providing result-oriented Digital Marketing Services in Ethiopia, Addis Ababa.
Follow Edget Digital Marketing g and Promotion Social Media Channels for more updates, news, and Tips on page https://www.facebook.com/100089753680371/
Telgram https://t.me/EdgetDigital
LinkedIn page https://www.linkedin.com/.../edget-digital-marketing.../.
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
Bole Sub City
Addis Ababa