Roba junior .kebe

Roba junior .kebe

Share

01/08/2022

እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ (ለምን እንላለን)



በቤተክርስቲያናችን ስርዓት ሁል ጊዜ ካህኑ እግዚአብሔር ከታሰራችሁበት ኃጥያት ማሰሪያ ይፍታቹ ሲሉ 12 ጊዜ እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስና 12 ጊዜ ደግሞ በእንተ እግዝትነ ማርያም መሐረነ ክርስቶስ ያስብላሉ ። ካህናትና ምእመናን በጣቶቻችን እየቆጠርን ይህኑን 12 ጊዜ እንላለን ።
እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ ማለት አቤቱ ክርስቶስ ማረን ሲሆን በእንተ እግዝእትነ ማርያም መሐረነ ክርስቶስ ደግሞ ስለ እመቤታችን ማርያም ብለህ ክርስቶስ ሆይ ማረን ማለት ነው ።
አስራ ሁሉት ጊዜ መሐረነ መባሉ ለቀኑ 12 ሰዓት በእንተ እግዝእትነ ማርያም ደግሞ ለሊቱን 12 ሰዓት ሲሆን በአጠቃላይ በየሰዓቱ ለሰራነው ኃጥያት በሃያ አራቱ 24ቱ ሰዓት ምሕረት እናገኝ ዘንድ ነው።
ሌላው አስራ ሁለት ጊዜ የሆነበት ምክንያት፦
1ኛው በስመ ሥላሴ ነው በእያንዳንዱ ፊደል
አ ብ ወ ል ድ መ ን ፈ ስ ቅ ዱ ስ
፩ ፪ ፫ ፬ ፭ ፮ ፯ ፰ ፱ ፲ ፲፩ ፲፪
2ኛው የድህነታችን ምክንያት በሆነች በእመቤታችን ስም ፊደል ነው ።
ቅ ድ ስ ት ድ ን ግ ል ማ ር ያ ም
፩ ፪ ፫ ፬ ፭ ፮ ፯ ፰ ፱ ፲ ፲፩ ፲፪

#እግዚኦ መሐረነ

አቆጣጠረም እግዚኦ መሐረነ ሲባል በአውራ ጣት እየቆጠሩ ከጠቋሚ ጣት ወደ ታች ፣ ቀጥሎ በመሐል ጣት ወደ ላይ ከዚያም በቀለበት ጣት ወደ ታች ተደርጎ በማርያም ጣት /በትንሿ/ ጣት ወደ ላይ ነው ።
ከጠቋሚ ጣት ወደ ታች ~ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን ከሰማየ ሰማያት መውረዱን በዚህ ምድር መመላለሱን ሕማሙንና ሞቱን እናስባለን ።
መሐል ጣት ወደ ላይ ~ማረጉን ወደ ሰማይ መውጣቱን በቀለበት ጣት ወደ ታች ስንቆጥር ወደዚች አለም ለፍርድ መምጣቱን፤ በትንሿ/ ጣት ወደ ላይ ስንወጣ ደግሞ በትንሳኤ ዘጉባኤ ይዞን ወደ ሰማይ እንደሚያወጣን እያሰብን ነው።

በእንተ እግዝእትነ ማርያም መሐረነ ክርስቶስ
________________ ____________________
በእንተ እግዝትነ ማርያም ስንል አቆጣጠሩ ከትንሿ ጣት ወደ ታች ይጀመርና በጠቋሚ ጣት ወደ ላይ ይፈጸማል ይህም እመቤታችን ድንግል ማርያም ከትሕትና ወደ ልዕልና ከፍ ማለቷን የሚያሳይ ምሥጢር ነው ።

ብእንት ሲባል በትንሿ ጣት ወደ ታች የሚጀመር ራሷን ዝቅ አድርጋ የትህትናዋ ምሳሌ ስለሆነ ነው ከላይ ወደ ታች ሚጀመረው።

“ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳል፥ ራሱንም የሚያዋርድ ሁሉ ከፍ ይላል” (ማቴ 23፣12)

እንዲሁም የበእንተ እግዝእትነ ማርያም . . . ፍጻሜ ወደ ላይ የሚያልቀው ሚስጢሩ እመቤታችን በመቃብር አልቆየችም ወደላይ ዐርጋለች ለማለት ነው።

“ አቤቱ፥ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ፥ አንተና የመቅደስህ ታቦት”
- መዝ 132፡8

ባሕረ ጥበባት ቅድስት ቤተክርስቲያን የምስጢር ጓዳ ናት

13/06/2022

✅🚹 ወንዶች ሆይ ልብ በሉ!! 🚹✅

🌀አምላክ ልቧ ቆንጆ የሆነችውን ሴት እንዲስጣችሁ አምላክን ለምኑ።

🌀 ያንተ የሆነችውን ሴት አምላክ እስኪሰጥህ ትእግስት ይኖርህ ልብህ ያርፈባትን ውደድ አፍቅር አይንህ እዛም እዚህም አይቀላውጥ በቁንጅና፣ በተክለ ሰውነት እና ባለባበስ አትማርክ ሴት ልጅ ባለባበሷ እና በመልኳ አይትህ አትናቅ ቆንጆ ስታማርጥ ያንተ የሆነችውን እና ህይወትህን የምታጣፍጥህልህን ሴት እንዳታጣ።

🌀 ለማፈቀር ወይም ለመፈቀር ሰው መሆን በቂ ስለሆነ።

🌀 የስው አስቀያሚ የለውም የአስተሳስብ እንጂ ቆንጆ አይደለችም ፣አለባበሷ ይደብራል፣አቋሟ አያምርም አትበል ቀርበህ የውስጧን ውበት ሳታይ በላይ ውበቷ አታጣጥላት ለተርዳው ስው እና በሳል ለሆነ ስው ከላይ ውበት ይልቅ የውስጥ ውበት ሚዛን ይደፍል እና ስለዚህ ላንተ ከተመቸችህ ምንም ትሁን የአንተንህይውት አንተ እንጂ ሌላስው አይኖርልህም ለራስህ ብለህ ኑር ለራስህ ብለህ አስተውል ለስው ብለህ ምንም ነገር አታድርግ ለህሊናህ እንጂ።

🌀 ቆንጆ አግብቼ የእከሌ ሚስት ቆንጆ ናት ወዘተ እንዲባልልህ ሳይሆን ለህይወትህ የምትመችህን የምትስማማህን ሀሳብህን የምትርዳህ እና ከልብ የምታፈቅርህን ከፈለክ አይንህ ሳይሆን ልብህ ያያትን አግባ።

Want your business to be the top-listed Advertising & Marketing Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address


A/A
Addis Ababa