Addis Home Care

Addis Home Care

Share

15/09/2023

Happy New Year!

21/07/2022

U. T. I /Kidney Infections

16/04/2022

የጭንቅላ እጢ ምልክቶች

አብዛኛዎቹ የጭንቅላት እጢ ቀጥለው ከተዘርዘሩት ውስጥ ቢያንስ ከሁለት በላይ ምልክቶች ሊያሳዩ /ሊኖርባቸው ይችላል ነገር ግን ምልክቶቹ ሁሉ የእጢ እና ዕጢ ብቻ የማይሆኑበት አጋጣሚም ይኖራል ስለሆነም በምርመራ የትኛው የአእምሮ ክፍል እና ምን አይነት ዕጢ ነው የሚባለው ነገር መታወቅ አለበት፡፡

👉 ራስ ምታት:

👉 የእይታ ችግር:

👉 የሚጥል በሽታ ካለ

👉 የሰውነት መስነፍ:

👉 መንገዳገድ (ባላንስ አለመጠበቅ)፡

👉 ምንም ምልክት አለመኖር፡- ለሌላ ተብሎ በተሰራ ምርመራ አጋጣሚ የአንጎል እጢ ሊገኝ ይችላል። የእጢው እድገት እና ባህሪ ታይቶ ኦፕራስዮን ወይም ሌላ የሕክምና አማራጭ ሊያስፈልገው ስለሚችል ክትትል ማድረግ ያስፈልጋል።

👉 መስማት መቀነስ:- አዲስ ወይም ቀስ በቀስ እየባሰ የሚሄድ የመስማት ችግር

👉 ሽንት ወይም ሰገራ መቆጣጠር አለመቻል

👉 ትንታ (chocking):
👉 ማስመለስ:

👉 የመናገር ችግር:

👉 የማስታወስ ችግር (መርሳት)፡

👉 የፊት እና አገጭ ላይ ከባድ ህመም መሰማት

👉 የንቃት መቀነስ:

👉 የጭንቅላት መጠን መጨመር:

👉 ከልክ ያለፈ የሰውነት መጠን መጨመር:

07/04/2022

"ከማህፀን ውጭ የሚፈጠር እርግዝና" - ዶ/ር ሲሳይ ተክሉ ፣ የማህፀን እና ፅንስ ስፔሻሊስት

ከማህፀን ውጪ እርግዝና የሚንለው እርግዝና ከማህፀን ውጪ ሲፈጠር ሲሆን ስንደ ስያሜው፣ በአብዛኛውን ደግሞ ይሔ የሚሆነው በማህፀን ቱቦ ውስጥ ነው፡፡ እነዚህ የማህፀን ቱቦዎች ውስጥ እርግዝና ሲከሰት ፅንሱ እድገቱን መቀጠል የማይችል እና በቱቦዎቹ ውስጥ በቆየ ቁጥር ደግሞ በእናትየው ጤና ላይ አደጋ የሚያስከስት ነው፡፡

ከማህፀን ውጭ የሚፈጠር እርግዝና በአፋጣኝ ሕክምና የሚያስፈልገው ሲሆን ፅንሱን ማስቀጠልም ስለማይቻል፣ ፈጥኖ ተገቢውን ህክምና ማግኘት ወደሚቻልበት የህክምና ማዕከል በመሄድ በመድሐኒት ወይም በቀዶ ህክምና ፅንሱን ማውጣት ተገቢ ነው፡፡

ከማህፀን ውጭ የሚፈጠር እርግዝና ምልክቶች
ከማህፀን ውጪ እርግዝና ምንም ዓይነት ምልክት ላያሳይ ይችላል፡፡ ይሔም ማለት እናቶች በፅንስ ክትትል ወቅት የፅንስ አልትራሳውንድ ምርመራ ሲያደርጉ የሚታወቅ ክስተት ሊሆን የሚችልበት አጋጣሚ ሰፊ ነው፡፡

ከዚህ ውጪ በተረፈ ምልክቶቹ (ካሉ) የሚታዩት በአብዛኛው ከ4ኛ እስከ 12ኛው የእርግዝና ሳምንት ነው፡፡

እነዚህም ምልክቶች፡-
- የወር አበባ አለማየት
- ማቅለሽለሽ እና ሌሎች የእርግዝና ምልክቶች
- በአንድ ትከሻ ጫፍ ላይ ህመም ስሜት መሰማት
- በአንድ በኩል የሚያጋድል የሆድ ህመም
-ደም ወይም ቡናማ ፈሳሽ በማህፀን መፍሰስ
-በሚሸናበት ወቅት ምቾት መንሳት ሊሆኑ ይቸላሉ፡፡

ይሄ በዚህ እንዳለ እነዚህ ምልክቶች የማህፀን ውጪ እርግዝና ምልክቶች ብቻ አይደሉም፣ የሆድ ዕቃ/ጨጓራ መታወክን ጨምሮ ሌሎች ህመሞች ምልክቶች ናቸው፡፡

ሕመሙን መኖሩን የምናረጋግጠው ከላይ የተዘረዘሩትን ምልክቶች አይተን በሽንት የእርግዝና ምርመራ ካደረግን በኋላ የፅንስ አልትራሳውንድ ምርመራ በማድረግ ነው፡፡

ከማህፀን ውጭ የሚፈጠር እርግዝና መንስኤዎች ግልፅ ባይሆኑም አልፎ አልፎ ሲከሰቱ የሚስተዋለው ዋናው መንስኤ በማህፀን ቱቦዎቹ ውስጥ ያለ ችግር ምክንያት ነው፡- ይሄም ማለት ቱቦዎቹ ሲጠቡ ወይም በሆነ ምክንያት ሲዘጉ ነው፡፡

ከዚህ በተጨማሪ አንዳንድ ለሕመሙ ተጋላጭነት የሚዳርጉ ሁኔታዎች የሚከተሉት ናቸው፡-
- በማህፀን ቱቦዎች ላይ የሚከሰት ኢንፌክሽን/ በአብዛኛው በአባላዘር በሽታዎች ምክንያት የሚመጣ፣
- ከዚህ ቀደም የተከሰተ ከማህፀን ውጭ እርግዝና- ይሔ ሲሆን ድጋሚ የሚከሰትበትን ዕድል በ 10 በ 100 ይጨምረዋል፡፡
- በቀዶ ህክምና ወቅት የሚደርስ የማህፀን ቱቦ ጉዳት - በተለይም የማህፀን ቱቦ መዘጋት
- የማህንነት ህክምና
- ማጨስ
- እድሜ መጨመር ፣ የእናቶች እድሜ ከ35-40 በላይ ሲሆን

ህክምናው

ሀኪምዎ ለእርስዎ የሚሆን የህክምና አይነት ከማህፀን ውጪ እርግዝናው እንደተከሰተበት ቦታ እና እንዳጋጠመው የጤና ውስብስብ ችግር ላይ ተመረኩዞ በመድሃኒት ወይም በቀዶ ህክምና ህክምና ያደርግሎታል፡፡

በመድሃኒት፡- ጊዜው ያልገፋ በማህፀን ቱቦ ውስጥ ለተከሰተ፣ ያልፈነዳ፣ ሊያድግ የማይችል ፅንስ ሲኖር
ቀዶ ህክምና ደግሞ በመድሃኒት ለመወገድ ትልቅ የሆነ ፅንስ ሲሆን ወይም ፅንሱ ያለበት የማህፀን ቱቦ የፈነዳ

ድጋፍ
ከማህፀን ውጪ እርግዝና ከተከሰተ በኃላ እናቶች ላይ ሀዘንን እና ትካዜን ማየት የተለመደ ቢሆንም ብዙ የሚቆይ ነገር ግን ሆኖ አይስተዋልም፡፡ ሀኪምዎ ጋር በመሄድ ስለወደፊት የእርግዝና እቅዶች እንዲሁም ስለ ስነልቦናዊ ድጋፍ ምክክር ማድረግ ተገቢ ነው፡፡

ስለተከታይ እርግዝና መሞከር

ተከታይ እርግዝና ከባለቤትዎ ጋር ለመሞከር ስታስቡ ሁለታችሁም አካላዊ እና ስነ ልቦናዊ ዝግጅት ማድረግ ይኖርባችኋል፡፡

Want your business to be the top-listed Health & Beauty Business in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Website

Address


Addis Ababa
0001