Ethio Heart Health
24/05/2026
🩺 ዙሪያ የታተመ ጥናት ዳግም ምልከታ (Revisiting a Published Research on )
🫀 በአዲስ አበባ በተደረገ የአጋጣሚ የደም ግፊት ምርመራ ፕሮግራም ላይ ሳይታወቅ የቆየ ከፍተኛ የደም ግፊትና ተያያዥ ምክንያቶች
የጥናቱ #ርዕስ፦
"Prevalence of newly diagnosed hypertension and its associated factors in an opportunistic screening program in Addis Ababa, Ethiopia"
ደራሲዎች (Authors)፦ Gashaw Solela, Balew Arega, Elias Tewabe, Rediet Ambachew, Samuel Kassahun, Seble Legese
ተጓዳኛ ደራሲ (Corresponding author)፦ Gashaw Solela - [email protected]
📌 #መግቢያ
• ከፍተኛ የደም ግፊት በዓለም ዙሪያ ከልብና ከደም ቧንቧ በሽታዎች ጋር ለተገናኙ የተለያዩ የጤና ችግሮችና ሞቶች ተቀዳሚ ምክንያት ነው።
• ብዙ ጊዜ ምልክት ስለሌለው በርካታ ሰዎች ላይ መኖሩ አይታወቅም።
• በአጋጣሚ የደም ግፊት ምርመራ ማድረግ ቀደም ብሎ ለመለየት አንደኛው ተግባራዊ መንገድ ነው።
🧪
• የጥናት አይነት: ተቋማዊ የአንድ ጊዜ ጥናት
• ቦታ: የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ
• ጊዜ: ከኖቬምበር 2023 – ፌብሩዋሪ 2024 (እ.ኤ.አ.)
• ተሳታፊዎችና ብዛታቸው: 301 አዋቂዎች
• መረጃ ለመሰብሰብ ጥቅም ላይ የዋለ መሳሪያ: WHO STEPS መጠይቅ እና መደበኛ የደም ግፊት መለኪያ
• ትንተና: ባለብዙ ተለዋዋጭ ሎጂስቲክ ሪግሬሽን
📊
• አዲስ የተገኘ (በፊት ያልታወቀ ወይም ያልነበረ) ከፍተኛ የደም ግፊት ያለባቸው ሰዎች ብዛት 36.2 በመቶ ነበረ። ይህም ማለት በአማካኝ ከ3 ሰዎች 1 ሰው ቀደም ሲል ያልታወቀ ከፍተኛ የደም ግፊት ነበረው።
⚠️
👨 ወንድ መሆን (AOR 2.06): በ2 እጥፍ አካባቢ ከፍ ያለ እድል
💍 ትዳር ያላቸው (AOR 4.8): በ5 እጥፍ አካባቢ ከፍ ያለ እድል
⚰️ ባል ወይም ሚስት የሞተባቸው (AOR 5.14): በ5 እጥፍ አካባቢ ከፍ ያለ እድል
🥗 ዝቅተኛ የፍራፍሬ እና የአትክልት አመጋገብ (AOR 2.22–2.88): ከ2 እስከ 3 እጥፍ አካባቢ ከፍ ያለ እድል
🏃 የእንቅስቃሴ እጥረት (AOR 2.26): በ2 እጥፍ አካባቢ ከፍ ያለ እድል
⚖️ የውፍረት ለቁመት ንፅፅር [Body Mass Index - BMI] (AOR 1.17 per kg/m²) መጨመር: በእያንዳንዱ 1 kg/m² መጨመር 17 በመቶ ከፍ ያለ እድል
🧠 #መደምደሚያ
• በጤና ተቋም ውስጥ በተደረገ የአጋጣሚ የደም ግፊት ምርመራ ቀድሞ ሳይታወቅ የቆየ ከፍተኛ የደም ግፊት ያለባቸው ሰዎች ቁጥር ብዙ እንደነበር ታይቷል። እንዲሁም አብዛኞቹ አጋላጭ ምክንያቶች መሻሻል የሚችሉ እንደሆኑ ጥናቱ አመላክቷል።
📌
👉 ከ3 ሰዎች 1 ሰው ቀደም ሲል ያልታወቀ ከፍተኛ የደም ግፊት እንደነበረው ታይቷል።
👉 ከፍተኛ የደም ግፊት መኖሩን ለማወቅ መደበኛ ምርመራ እና የመከላከል እርምጃዎች መጠናከር አለባቸው።
ማጣቀሻ፦ Solela, G. et al. BMC Cardiovasc Disord 24, 492 (2024). https://doi.org/10.1186/s12872-024-04171-9
በዶ/ር ጋሻው ሶለላ (የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት፣ የማህበረሰብ ጤና ባለሙያና የልብ ህክምና ፌለው)
Telegram: https://t.me/ETMedHeart
Facebook: facebook.com/ETMedHeart
📞 0928084444
በቴሌግራም ለማማከር:
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Telephone
Address
Addis Ababa