ROM Computer and Mobile Maintainance
ጭማሪ የታየበት አዲሱ የኢትዮ ቴሌኮም የዋጋ ዝርዝር
| የኢትዮ ቴሌኮም ያልተገደበ (Unlimited) የቋሚ ብሮድባንድ ወርሃዊ ክፍያ ዝርዝር፦
1. 7Mbps — 999 ብር
2. 10Mbps — 1,300 ብር
3. 15Mbps — 1,875 ብር
4. 20Mbps — 2,500 ብር
5. 30Mbps — 3,700 ብር
6. 50Mbps — 5,900 ብር
7. 100Mbps — 11,000 ብር
8. 200Mbps — 21,000 ብር
9. 500Mbps — 52,000 ብር
10. 1Gbps (1,000Mbps) — 95,000 ብር
የዋትሳፕ አካውንትዎን ከጠለፋ ለመከላከል እነዚህን አድርጉ
| በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት የዋትሳፕ (WhatsApp) አካውንት ጠለፋ በስፋት እየተለመደ የመጣና ብዙዎችን ለከፍተኛ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳት እየዳረገ ያለ ችግር ነው።
ይህንን ስጋት ለመከላከልና የሳይበር ደህንነትዎን ለመጠበቅ የሚከተሉትን ዋና ዋና የጥንቃቄ የጥንቃቄ እርምጃዎች መተግበር አስፈላጊ ነው።
👉ባለ ሁለት ደረጃ ማረጋገጫን ማተግበር፦ይህ ዘዴ አካውንትዎ እንዳይጠለፍ የሚያደርግ ቁልፍ የመከላከያ ጋሻ ነው። ይህን ካደረጉ ጠላፊው የእርስዎ ሲም ካርድ ቢኖረው እንኳ ያለ እርስዎ ሚስጥራዊ ቁጥር መግባት አይችልም።
👉የማረጋገጫ ኮድ ለማንም አለመስጠት፦ዋትሳፕ በኤስኤምኤስ (SMS) የሚልክልዎትን ባለ 6 አሃዝ ኮድ በፍጹም ለማንም አያጋሩ።
👉አጠራጣሪ ሊንኮችን አለመንካት፦ በግሩፖች ወይም በግል የሚላኩ "ነፃ የኢንተርኔት ጥቅል"፣ "የስራ ዕድል" ወይም "የቴሌግራም/ዋትሳፕ ስጦታ" የሚሉ ሊንኮች ማጥመጃ ሊሆኑ ይችላሉ። እነዚህን ሊንኮች ሲነኩ ስልክዎ ላይ ቫይረስ ሊጭኑ ወይም መረጃዎን ሊሰርቁ ይችላሉ።
👉የዋትሳፕ ድረ-ገጽ አጠቃቀምን መከታተል፦ ኮምፒውተር ላይ ዋትሳፕ ተጠቅመው ሲጨርሱ ሁልጊዜ ማድረጋቸውን ያረጋግጡ፤ እንዲሁም የሚለውን ክፍል በመግባት እርስዎ የማያውቁት ሌላ መሣሪያ ተገናኝቶ ከሆነ Log out በማድረግ ግንኙነቱን ያቋርጡ።
👉ፎቶ እና መረጃን መደበቅ፦ጠላፊዎች የእርስዎን ፎቶ እና ስም በመጠቀም አዲስ አካውንት ከፍተው ቤተሰቦችዎን "ገንዘብ ቸግሮኝ ነዉ ላኩልኝ" ብለው ሊያታልሉ ይችላሉ። በመሆኑም Settings > Privacy በመግባት Profile Photo እና About የሚሉትን ወደ "My Contacts" ብቻ ይቀይሩ።
INSA- የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር
29/12/2025
ዓለማችን የመጀመሪያውን ስክሪን አልባ ላፕቶፕ (Spacetop G1) አስተዋወቀች
| የቴክኖሎጂው ዓለም በየቀኑ አዳዲስ ፈጠራዎችን እያስተናገደ ባለበት በዚህ ወቅት፣ ሳይትፉል የተሰኘው ኩባንያ "Spacetop G1" የተሰኘውን እና ምንም ዓይነት አካላዊ ስክሪን የሌለውን ላፕቶፕ ለገበያ ማቅረቡን አስታውቋል።
ይህ ላፕቶፕ ከተለመዱት ኮምፒውተሮች ለየት የሚያደርገው በስክሪን ፋንታ እጅግ የረቀቁ የኤአር (Augmented Reality) መነጽሮችን በመጠቀም ሰፊ የሥራ ገበታን ለተጠቃሚው አይን ላይ ማሳየቱ ነው።
መነጽሩን በሚያደርጉበት ጊዜ እስከ 100 ኢንች የሚደርስ ግዙፍ የኮምፒውተር ስክሪን ከፊትዎ ተንሳፎ የሚታይ ሲሆን ይህም በጠባብ ቦታዎች ላይ ሆነው ሰፊ የሥራ ቦታ እንዲኖርዎት ያስችላል።
በተጨማሪም ስክሪኑ የሚታየው መነጽሩን ላደረገው ሰው ብቻ በመሆኑ በሕዝብ መጓጓዣዎች ወይም በካፌዎች ውስጥ ለሚሰሩ ባለሙያዎች ከፍተኛ የግል ምስጢራዊነት ጥበቃን ይሰጣል።
ከጎንዎ ያለ ሰው የሚሰሩትን ማየት የማይችልበት ይህ ቴክኖሎጂ ለደህንነት ትልቅ አስተዋጽኦ አለው።
ላፕቶፑ ስክሪን ስለሌለው ክብደቱ እጅግ የቀለለ ሲሆን ለተጓዦች እና በማንኛውም ቦታ ሆነው ለሚሰሩ የዲጂታል ባለሙያዎች ምቹ ሆኖ ተዘጋጅቷል።
መሳሪያው በSpaceOS ኦፕሬቲንግ ሲስተም የሚሰራ ሲሆን ፈጣን የ5G ኢንተርኔት ግንኙነትን እና አስተማማኝ የባትሪ አቅምን ያካተተ ነው።
ይህ አዲስ የቴክኖሎጂ ውጤት ወደፊት የሞባይል ኮምፒውቲንግን መልክ ሙሉ በሙሉ ሊቀይረው እንደሚችል የዘርፉ ባለሙያዎች እየገለጹ ይገኛሉ::
12/12/2025
የኢንተርኔት ተጠቃሚዎችን የግል መረጃ አደጋ
ላይ የጣለ አዲስ የChrome ክፍተት ተገኝቷል
| ይህን ተከትሎም ጎግል ለክሮም መረጃ ማፈላለጊያዉ በአስቸኳይ ሊተገበሩ የሚገባቸው ለሶስት አደገኛ ክፍተቶች መድፈኛ አዲስ ማሻሻያ መልቀቁን አስታውቋል።
ከእነዚህ ክፍተቶች መካከል አንዱ በተለይ እጅግ አደገኛ ሲሆን፣ የግል መረጃዎችን ለመጥለፍ በመረጃ ጠላፊዎች በንቃት ጥቅም ላይ እየዋለ ያለ Zero_day ጥቃት መሆኑ ታዉቋል።
የደህንነት ባለሙያዎች እንዳስጠነቀቁት ከሆነም ይህ አደገኛ ክፍተት የመረጃ ጠላፊዎች ኮምፒውተራችንን ወይም ስልካችንን ዘልቀው በመግባት የይለፍ-ቃሎችንና ሌሎች ሚስጥራዊ መረጃዎችን እንዲሰርቁ የሚያስችል መሆኑ ታዉቋል።
እስካሁን መለያ ቁጥር (CVE) ያልተሰጠውና በጎግል የውስጥ መለያ 466192044 ብቻ የሚታወቀው ይኸው ክፍተት፣ በክሮም ተጠቃሚዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርስ እንደሚችል ተገልጿል።
ይህ ጥቃት በፈረንጆቹ 2025 ዓ.ም. የመረጃ ጠላፊዎች በስፋት ሲጠቀሙበት የተገኘ ስምንተኛው የክሮም "ዜሮ-ዴይ" ጥቃት መሆኑም ተረጋግጧል። ይህ የሚያሳየው የክሮም ተጠቃሚዎች በተደጋጋሚ የጥቃት ኢላማ መሆናቸዉን ነው።
ታኅሣሥ 1, 2018 ዓ.ም. የተለቀቀው ይህ ማሻሻያ፤ ከላይ ከተጠቀሰው ከፍተኛ አደጋ በተጨማሪ፣ ሁለት መካከለኛ ደረጃ የተሰጣቸውን የደህንነት ክፍተቶችም ይደፍናል ተብሎለታል።
ሁሉም የክሮም ተጠቃሚዎች የግል መረጃቸዉ ሳይጠለፍ እና የባንክ አካውንታቸዉ አደጋ ላይ ሳይወድቅ ለመከላከል እንዲችሉ፣ ሁሉንም የክሮም የመረጃ ማፈላለጊያቸዉን በአስቸኳይ እንዲያዘምኑ Update በጥብቅ ይመከራል።
ማሻሻያውን_ለመተግበር፦ ወደ ክሮም Settings በመግባት፣ Help የሚለውን በመምረጥ፣ በመቀጠል About Google Chrome የሚለውን በመጫን ክሮም የመረጃ ማፈላለጊያዎን ማዘመን ይችላሉ።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Addis Ababa