Emad TECH

Emad TECH

Share

ELA TECH || ኤላ ቴክ BOT 03/02/2022

✴️ አፕሊኬሽን ከGoogle Play Store ዳውንሎድ ከማድረጋችን በፊት አፕሊኬሽኑ ጎጂ ወይም ጠቃሚ መሆኑን እንዴት ማረጋገጥ እንችላለን?

🔥ከGoogle Play Store ላይ የምናወርዳቸው አፕሊኬሽኖች ጠቃሚ መሆናቸው የተረጋገጠላቸው እና ጎጂ እንዳልሆኑ የተመሰከረላቸው ናቸው፡፡

🔥ነገር ግን አንድ አንድ ግዜ ጠቃሚ መስለው ጎጂ አፕሊኬሽኖችን Play Store ላይ ልታገኙ ትችላላችሁ፡፡

🔥ታድያ Play Store ላይ አፕሊኬሽን ዳውንሎድ ስናደርግ አፕሊኬሽኑ ጠቃሚ ወይም ጎጂ መሆኑን እንዴት መለየት እንችላለን?

⚡️❶. አፕሊኬሽኑ ምን ያህል ግዜ ዳውንሎድ እንደተደረገ መመልከት

🔥ዳውንሎድ ማድረግ የፈለግንው አፕሊኬሽን ዳውንሎድ ከማድረጋችን በፊት አፕሊኬሽኑ ምን ያህል ግዜ ዳውንሎድ (Download Count) እንደተደረገ በደንብ መመልከት

🔥ለምሳሌ ዳውንሎድ የምታደርጉት አፕሊኬሽን አንድ ሚሊዮን ግዜ ወይም ከዚያ በላይ ዳውንሎድ እንደተደረገ ካያችሁ ወድያው አፕሊኬሽኑ የተለቀቀበት ቀን በደንብ መመልከት፡፡

🔥ምክንያቱም አብዛኛው አፕሊኬሽን ከተለቀቀበት ግዜ ጀምሮ አንድ ዓመት ወይም ከዚያ በላይ የቆየ ሲሆን ነወ ከሚሊዮን በላይ ዳውንሎድ ሊኖረው የሚችለው፡፡ ስለዚህ እናንተ ማውረድ የፈለጋችሁት አፕሊኬሽን ከተለቀቀ አንድ ዓመት ካልሞላው እና ዳውንሎድ የተደረገው ከሚሊዮን በላይ ከሆነ አፕሊኬሽኑን ከማውረድ ብትቆጠቡ ይሻላል፡፡

⚡️❷. ስለ አፕሊኬሽኑ የተሰጡ የተወሰኑ አስተያየቶችን ማንበብ

🔥ዳውንሎድ ማድረግ የምትፈልጉት አፕሊኬሽን ከማውረዳችሁ በፊት ከዚህ በፊት አፕሊኬሽኑን ዳውንሎድ ያደረጉ ሰዎች ስለ አፕሊኬሽኑ አስተያየት (Reviews)ያስቀምጣሉ፡፡ እነዚህን አስተያቶች በጥንቃቄ ማንበብ፡፡

🔥ስለ አፕሊኬሽኑ በጣም የሚያማርሩ አስተያየቶች ካነበባችሁ አፕሊኬሽኑ ከማውረድ እንደጥቆጠቡ እመክራለሁ፡፡

⚡️➌.የአፕሊኬሽኑ ስምምነት በጥንቃቄ ማንበብ

🔥አፕሊኬሽኑ ከላይ የተጠቀሱትን ፍተሸዎች ካለፈ ዳውንሎድ ታደርጉታላችሁ፡፡ ከዚያ ኢንስቶል ስታደርጉት የአፕሊኬሽኑን ስምምነት በጥንቃቄ ማንበብ ያስፈልጋል፡፡

🔥ሁላችንም ማለት ይቻላል አፕሊኬሽን ኢንስቶል ስናደርግ ስምምነቱን ሳናነብ "Accept" እንላለን፡፡ ልክ አይደለም፡፡
ምክንያቱም የሳይበር ወንጀለኞች ይህንን ባህሪያችን ስለሚያውቁ እኛን ሊጎዱ የሚችሉ ነገሮችን ስምምነቱ ላይ በማስገባት ጥቃት ሊፈፁሙብን ይችላሉ፡፡

🔥ስለዚህ ስምምነቱን ስታነቡ ለምሳሌ data mining, data sharing, pop-ups ወዘተ የሚሉ ቃላት ከተመለከታችሁ የአፕሊኬሽኑን ኢንስቶሊንግ ሂደት እንድታቋርጡ እመክራለሁ፡፡፡

🔥ስለዚህ ዳውንሎድ ማድረግ የፈለጋችሁት አፕሊኬሽን ቢያንስ እነዚህን 3 ፍተሸዎችን ካለፈ ጎጂ አይደለም ማለት ነው፡፡
════❁✿❁ ═══════


🔶የ Youtube ቻናላችንን Subscribe በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ👇
https://m.youtube.com/channel/UC0m3-0LnFPjCMTm0-EUIHyw

ELA TECH || ኤላ ቴክ BOT You can contact right away.

31/01/2022

የዋይፋይ ቁልፍ ወይም ፓስወርድ ለመስበር ኮማንድ ፕሮምትን በመጠቀም። To Crack Wi Fi password using CMD.
https://m.youtube.com/watch?v=lAY95LYz2lI

የዋይፋይ ቁልፍ ወይም ፓስወርድ ለመስበር ኮማንድ ፕሮምትን በመጠቀም። To Crack Wi Fi password using CMD. 04/01/2022

https://m.youtube.com/watch?v=lAY95LYz2lI&t=112s

የዋይፋይ ቁልፍ ወይም ፓስወርድ ለመስበር ኮማንድ ፕሮምትን በመጠቀም። To Crack Wi Fi password using CMD. የዋይፋይ ቁልፍ ወይም ፓስወርድ ለመስበር ኮማንድ ፕሮምትን በመጠቀም። To Crack Wi Fi password using CMD.

Want your business to be the top-listed Computer & Electronics Service in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Address


Addis Ababa