Smart Marketing

Smart Marketing

Share

15/09/2023

ካቻ 25 ሺሕ ዶላር የሚያስገኘውን የ”ቪዛ በየትኛውም ቦታ” ውድድር አሸናፊ ሆነ

አርብ መስከረም 4 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) በኢትዮጵያ የግል የሞባይል ገንዘብ ዝውውር አገልግሎትን በመስጠት ላይ የሚገኘው ካቻ ዲጂታል ፋይናንሺያል ሰርቪስ አ.ማ. 25 ሺሕ ዶላር የሚያስገኘውን የ"ቪዛ በየትኛውም ቦታ" የፊንቴክ ውድድር አሸናፊ ሆኗል፡፡

ቪዛ በኢትዮጵያ የፋይናንስ ቴክኖሎጂ (ፊንቴክ) ፈጠራን ለማበረታታት፣ የክፍያ እና የግብይት ተግዳሮቶችን ለመፍታት እንዲሁም አዳዲስ መፍትሄዎችን ለማምጣት ያስችላል ያለውን ኹለተኛውን ዙር የ"ቪዛ በየትኛውም ቦታ" የፊንቴክ ውድድር ሲያከናውን የቆየ ሲሆን፤ በውድድሩም ከ200 በላይ ተወዳዳሪዎች ተሳታፊ ሆነውበታል፡፡

በዛሬ ዕለትም ለፍጻሜ ውድድር የደረሱ 4 የፊንቴክ ድርጅቶች በአዲስ አበባ ስይንስ ሙዚየም በተዘጋጀው መድረክ ላይ፤ በተለያዩ ዘርፎች የሚገኙ ንግዶች የሚያጋጥሟቸውን የክፍያ እና የግብይት ተግዳሮቶች ለመፍታት ያስችላሉ ያሏቸውን የፈጠራ ሥራዎች በማቅረብ ለዳኞች እና ለመድረኩ ተሳታፊዎች አጭር ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ለፍጻሜ ውድድር የደረሱት 4ቱ የፊንቴክ ድርጅቶች ካቻ (Kacha)፣ ቀና (Qena)፣ ስማይል ፔይ (SmilePay) ላኪ ፔይ (LakiPay) ሲሆኑ፤ በመድረኩ ያቀረቡትን ገለጻ እና ማብራሪያ መሰረት በማድረግም የውድድሩ ዳኞች አሸናፊውን ለይተዋል፡፡

በዚህም መሰረት ካቻ ዲጂታል ፋይናንሺያል ሰርቪስ አ.ማ. የውድድሩ አሸናፊ በመሆን የ25 ሺሕ ዶላር ሽልማት የተበረከተለት ሲሆን፤ ቀና እና ስማይል ፔይ ኹለተኛና ሦስተኛ በመውጣት 15 ሺሕ ዶላር እና 10 ሺሕ ዶላር ተሸላሚ ሆነዋል።

አሸናፊዎቹ ከገንዘብ ሽልማቱ በተጨማሪ፣ ባንኮች፣ ነጋዴዎች፣ ቬንቸር ካፒታሊስቶች እና የመንግሥት አካላት የሚገኙበትን የቪዛን ሰፊ የአጋሮች መረብ ውስጥ የመካተት እና የመታወቅ እድል እንደሚያገኙ የተገለጸ ሲሆን፤ ዓለም አቀፍ ከሆኑ ታዋቂ ድርጅቶች እውቅና ማግኘት እንደሚችሉም ተነግሯል፡፡

እ.ኤ.አ. በ2021 የኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሽያጭ የክፍያ ስርዓት ኦፕሬተር በመሆን፤ የመጀመሪያውን "ቪዛ በየትኛውም ቦታ" ኢትዮጵያ ውድድርን አሪፍፔይ ማሸነፉ ይታወሳል።

Source: አዲስ ማለዳ

Want your business to be the top-listed Advertising & Marketing Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Address


Addis Ababa
1000