TES MIEDA
30/07/2024
#ጎፋ የታወጀው ብሔራዊ ሐዘን ቀን ማጠቃለያ የሻማ ማብራት ስነ-ስርዓት በሳውላ ከተማ!
ነፍስ ይማር፤ በድጋሚ!
30/07/2024
Job Title: Graphic Designer & Video Editor,marketing,accounting
Work Location: Addis Ababa, Ethiopia
Applicants Needed: Both
Requirements:
-ስለስራው በቂ እውቀት ያለው
-ከሰራተኞች ጋር ተግባብቶ የሚሰራ
-የተሰሰጠውን ሰራ በአግባቡ መወጣት የሚችል
• Knowledge of Graphic Design theory
• Experience using image editing and design software such as Adobe Illustrator, Photoshop, Premiere pro & After Effect
• Creativity and artistic ability to create unique visuals that express ideas, concepts and narratives
• Excellent knowledge of Facebook, Telegram, Instagram, Tik tok and other social media
Inbox Us your Portfolio
👉
Call:0910203513/0939508804
ቪፒኤን ስንጠቀም ማድረግ ያሉብን ጥንቃቄዎች
በኢትዮጵያ በተለይም የተወሰኑ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ገደብ መጣሉን ተከትሎ የቪፒኤን ፍላጎት በ1430 በመቶ ጨምሯል።
በአንድ ሀገር ያለ ኔትወርክ በብዙ ምክንያቶች መደበኛ የኔትወርክ ገደብ ሲጣል ቨርቹዋል ፕራይቬት ኔትወርክ ወይም ቪፒኤን በሚል የሚጠሩ መተግበሪያዎችን መጠቀም የተለመደ ነው።
በኢትዮጵያም መደበኛው የኔትውርክ አገልግሎት ገደብ ሲጣልበት የተለያዩ የቪፒኤን መተግበሪያዎችን በማውረድ መጠቀም ተለምዷል።
በአሁኑ ወቅትም በኢትዮጵያ በተለይም የተወሰኑ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ገደብ መጣሉን ተከትሎ ተጠቃሚዎች በቪፒኤን በመጠቀም ላይ ናቸው።
የቪፒኤን መተበሪያዎች ባጭሩ አንድ ሀገር ሆነን በሌላ ሀገር ኔትወርክ መጠቀም ማለት ሲሆን በተለይም የምንጠቀምበትን ሰርቨር፣ የምንጠቀማቸውን ዌብሳይቶች፣ የተጠቀምናቸወን ፋይሎች እና ሌሎች መረጃዎችን ሰዎች አልያም ስለ እኛ ማወቅ የሚፈልጉ አካላት መረጃውን ማግኘት እንዳይችሉ ያደርጋሉ።
ይሁንና ሁሉም አይነት የቪፒኤን መተግበሪያዎች አስተማማኝ ባለመሆናቸው የተወሰኑት በቀላሉ ለመረጃ መንታፊዎች ሊያጋልጡን ስለሚችሉ መጠንቀቅ ያስፈልጋል።
በአውስትራሊያ በተደረገ ጥናት 67 በመቶ የዓለማችን ቪፒኤን መተግበሪያዎች ቢያንስ አንድ መረጃ መመንተፊያ ቫይረስ ያላቸው ሲሆን ከተጠቃሚዎች የወሰዷቸውን መረጃዎች ለሶስተኛ ወገኖች አሳልፈው ይሸጣሉ።
የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ከተጠቃሚዎች መረጃዎችን በመግዛት የማስታወቂያ ስራዎቻቸውን የሚያከናውኑ ሲሆን የቪፒኤን ተጠቃሚዎች ዋነኛ ኢላማ እንደሚሆኑም ተገልጿል።
በተለይም ነጻ የቪፒኤን መተግበሪያዎች ለመረጃ መንታፊዎች የተጋለጡ ሲሆኑ 65 በመቶ ነጻ የቪፒኤን መተግበሪያዎች መረጃዎችን ከተጠቃሚዎች ወስደው ለቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ይሸጣሉ።
ይሁንና በክፍያ የሚገኙ የቪፒኤን መተግበሪያዎች ከመረጃ መንታፊዎች የተጠበቁ ሲሆን ደንበኞች ለመረጃዎቻቸው የሚጠነቀቁ ከሆነ የክፍያ ቪፒኤን መተግበሪያዎችን እንዲጠቀሙ ይመከራል።
በአጠቃላይ ቪፒኤን መተግበሪያዎችን መጠቀም ለመረጃ ምንተፋ፣ ለቫይረስ ጥቃት፣ ለከፍተኛ የኔትወርክ ክፍያ፣ ካለፍላጎት እና ለአሰልቺ ማስታወቂያዎች እና ለኔትወርክ መዘግየት ሊያጋልጥ ይችላል ተብሏል።
ምንጭ:– አል አይን
22/02/2023
በሶማሌላንድ የተከሰተውን ግጭት በመሸሽ ከ83 ሺሕ በላይ ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ ገቡ
በሶማሌላንድ ግዛት በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎችና በተቃዋሚ ኃይሎች መካከል የተፈጠረውን ግጭት የሸሹ ከ83 ሺሕ በላይ የሶማሌላንድ ነዋሪዎች፣ ወደ ኢትዮጵያ ድንበር በመዝለቅ በሶማሌ ክልል እየሠፈሩ ነው፡፡
በአፍሪካ ቀንድ ከሶማሊያ ተነጥለው የሚገኙት ሶማሌላንድና ፑንትላንድ ግዛቶች ድንበር መካከል በምትገኘው ላስካኑድ ከተማ የተከሰተው ግጭት፣ የበርካታ የሶማሌላንድ ነዋሪዎችን ሕይወት የቀጠፈ ሲሆን፣ በርካታ ሴቶችና ሕፃናት ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ዶሎ ዞን እየገቡ መሆናቸውን የተመድ የስደተኞች ዋና ኮሚሽነር አስታወቀ።
የኮሚሽኑ ሕዝብ ግንኙነት ክፍል ለሪፖርተር እንደገለጸው፣ እስከ ቅዳሜ የካቲት 11 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ 14 ሺሕ የሚሆኑ አዳዲስ አባወራዎች (ወይም 83 ሺሕ ግለሰብ ስደተኞች) ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል። ስደተኞቹም በሶማሌ ክልል ዶሎ ዞን ውስጥ ቦህ፣ ገልሃሙርና ዳኖድ በተባሉ ሦስት ወረዳዎች ተጠልለው እንደሚገኙ አስታውቋል፡፡
ዓርብ የካቲት 10 ቀን 2015 ዓ.ም. ተመድ አውጥቶት በነበረው መግለጫ አብዛኞቹ ስደተኞች ባለፈው ሳምንት ነበር ወደ ኢትዮጵያ የገቡት። በሦስቱ ወረዳዎች በ13 ቦታዎች ሠፍረው እንደሚገኙ፣ እንዲሁም የተወሰኑት በትምህርት ቤትና መሰል የሕዝብ መገልገያ ሥፍራዎች ላይ መጠለላቸውን፣ ሌሎች ደግሞ ያለ መጠለያ ሜዳ ላይ እንደሚገኙም አስረድቷል፡፡
ከሶማሌ ክልል የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ቢሮ ጋር በመሆን ከ1,500 በላይ ለሆኑ በከፍተኛ ሁኔታ ለተጎዱ አባዎራዎች የተለያዩ ቁሳቁሶችና መሰል ድጋፎችን እየሰጠ እንደሚገኝ፣ ለተጨማሪ 9,000 አባዎራዎችም በቀጣይ ቀናት ድጋፉን እንደሚያደርግ ተመድ ገልጿል፡፡
ምንጭ ሪፖርተር
22/02/2023
በኮንታ 38 አዳዲስ አማንያን ሥርዓተ ጥምቀት ተፈጽሞላቸው የሥላሴን ልጅነት አገኙ፡፡
(EOTC TV //የካቲት ፲፭ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም አዲስ አበባ)
አዲስ የተሠራችው የቁታ ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ምርቃት የካቲት 12 ቀን 2015 ዓ.ም የኮንታ ወረዳ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ገነት ቆሞስ አባ መዓዛ ቅዱሳን አዳነ በተገኙበት ቅዳሴ ቤቱ ተከብሯል፡፡
በዕለቱም 38 አዳዲስ አማንያን ሥርዓተ ጥምቀት ተፈጽሞላቸው የሥላሴን ልጅነት ማግኘታቸውን ማኅበረ ቅዱሳን አስታውቋል።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the public figure
Website
Address
Bulegarya
Addis Ababa