Top Consulting Center /TCC/
በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና አትሌቶቻችን ተጨማሪ ሜዳሊያ ለማስገኘት ዛሬ ሌሊት ይፋለማሉ
*************************
በ18ኛው የኦሪገን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ አትሌቶች ለሀገራቸው ተጨማሪ ሜዳሊያዎችን ለማስገኘት ዛሬ ሌሊት በሚደረጉ ሁለት የፍፃሜ ውድድሮች ላይ ይፋለማሉ።
ተጠባቂው የወንዶች 5 ሺህ ሜትር የፍፃሜ ውድድር ከሌሊቱ 10:05 ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል።
በዚህ ውድድር አትሌት ሰለሞን ባረጋ፣ አትሌት ሙክታር ኢድሪስ እና አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ እና እስካሁን የተገኘውን የሜዳሊያ ቁጥር ከፍ ለማድረግ የሚፋለሙ ይሆናል።
በቶኪዮ ኦሎምፒክ የ10 ሺህ ሜትር ውድድር ለሀገሩ ብቸኛውን የወርቅ ሜዳሊያ ያስገኘው አትሌት ሰለሞን ባረጋ በውድድሩ ይጠበቃል።
በሌላ በኩል የሴቶች 800 ሜትር የፍጻሜ ውድድር ሌሊት 10:35 ሲደረግ፣ በርቀቱ ኢትዮጵያን ወክላ ለፍፃሜው ያለፈችው ብቸኛዋ አትሌት ድርቤ ወልተጂ እንደ ሌሎቹ የሀገሯ ልጆች ደማቅ ታሪክ ለመጻፍ ትፋለማለች።
10ኛ ቀኑን በያዘው የኦሪገን አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ እስካሁን 4 የወርቅ፣ 4 የብር እና 2 የነሐስ ሜዳሊያ በድምሩ 10 ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ በሜዳሊያ ሰንጠረዡ ከአሜሪካ ቀጥላ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።
ኢትዮጵያ በ18ኛው የኦሪገን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ስታደርገው የነበረው ተሳትፎ ዛሬ ሌሊት በሚደረጉ ሁለቱ ውድድሮች ይገባደዳል።
24/07/2022
ወርቅውሃ ጌታቸውና
መቅደስ አበበ
በ3000 ሜትር መሰናክል ብርና ነሃስ በማምጣት
የሀገራችንን ባንዲራ ከፍ አድርገውልናልና ምስጋና ይገባቸዋል!!
በወንዶቹ ማራቶን እልህ አስጨራሽ ትንቅንቅ ሪከርድን የሰበረው ታምራት ቶላ🌷 እንኳን ደስ አላችሁ🌷🙏
በሴቶች 1500 ሜትር ፍፃሜ ጉዳፍ ፀጋዬ የብር ሜዳልያ
አትሌት ለሜቻ ግርማ በ3000 መሰናክል የብር ሜዳልያ
We are providing training on:Different Bank payment system on international procurements IncotermsConsulting on International and National bids Custom procedures etc.
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
Addis Ababa