Yes we can

Yes we can

Share

Photos from Lideta sub-city communication office's post 10/06/2024
Photos from Yes we can's post 05/06/2024

ከፒያሳ-ሜክሲኮ፣ ከሜክሲኮ- ቄራ-ወሎሰፈር- ቦሌ የኮሪደሩ ትሩፋት ያሸበረቀው መንገድ!

አይን ዘግቶ የመክፈት ያክል ፍጥነት ያለው የኮሪደሩ ልማት ስራ ከፒያሳንና አራት ኪሎ ሌላ የማናቀው አዲስ ሰፈር አስመስሎ ማራኪ መዝናኛ አድርጎ አይተናል። የሚገርመው ብዙዎች ልብ ያላሉት የኮሪደሩ ልማት ከተማዋን አቆራርጦ እንዴት በዘመናዊ መልኩ እያገናኘ እንደሆነ አለማየታችን ነው። ፒያሳ ፒያሳ ሲባል ሜክሲኮን ረሳናት እንጅ ያ ሁሉ የህዝብ ጋጋታ፣ ህገወጥ ነጋዴዎች ግርግር እና የሌቦች አስቸጋሪነት ሲበረክት የነበረበት ሜክሲኮም ልዩ ሆኗል!

ከፒያሳ በብሄራዊ አድርጎ ሜክሲኮ የሚሄደው መንገድ በታክሲ መሄድ ነውር መስሏል። የተሰራውን እያደነቁ ሲፈልጉ እያረፉ የሚሄዱበት ልዩ መንገድ ሆኗል። ከሜክሲኮ ወደ ቄራ በአፍሪካ ህብረት ፊት ለፊት ያለው የኮሪደሩ ድምቀት ተራምዶበት የሚጠገብ ነውን? ያረቢ! ሂዱና እዩ ብቻ! ወርቅ በተፈጥሮ ነው ይላሉ እንጂ የሰው ልጅም እጆቹን ካሰራ ወርቅ የመሰሉ ስራዎችን መስራት እንደሚችል አይተናል።

ከሜክሲኮ ቄራ አድርጎ በጎተራ አልፎ ወሎ ሰፈር ደረሶ ወደ ቦሌ መንገዶ የሚገባው መንገድ እየተሰራ ያለው ስራ፣ የተሰራበት ፍጥነት፣ አሁን የሚታየው ገፅታ አጃዒብ ነው። ምን አለፋችሁ አዲስ አበባ ሌላ ሁናለች! መንገድ ዳር መሽናት ልማድ በነበረበት ከተማ አሁን መዝናኛው ሁሉ መንገድ ዳር ሆኖ አገኘነው። የት የተገኘ ልምድ ነው ግን በአንዴ እንዲህ በአዲስ አበባ የበራው ፀሃይ?

ወዳጄ! ለሙሽራ መሞሸርያ ፎቶ ቦታ በፍለጋ የምታገኝ የአዲስ አበባ ህዝብ አሁን በየመንገዱ ከፒያሳ እስከ ሜክሲኮ፣ ስትፈልግ ከሜክሲኮ ቄራ አይ ካልክ ከቦሌ እስከ መስቀል አደባባይ ሰፊ ቦታ በአማራ ተፈጥሮ ይጠብቀሃል። ለቲክታክ መስሪያ ቦታ ሲመርጥ የነበረ ሁላ አሁን ሁሉ ቦታዎች የተመረጡ ሆነዋል። እንግዳም ከመጣ ከከተማ ወጣ ማለት አይጠበቅባችሁም እዚው ዞራችሁ የማትጨርሱ መዝናኛ አለላችሁ፣ በምሽት ሲሆን ደግሞ ልዩ ነው!

Want your business to be the top-listed Beauty Salon in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address


Addis Ababa