Light Research and Consultancy

Light Research and Consultancy

Share

13/06/2020

How do we set research objectives?.............................................
Research objectives ወይም የጥናት ስራ አላማዎች በምርምር ስራ ላይ እጅግ በጣም ወሳኝ ናቸው፡፡

ሁሌም ጥናቶች የሚሰሩት የተወሰኑ አላማዎችን ለማሳካት ነው፡፡ በመሆኑም ማንኛውም የ ሪሰርች ስራ objectives ወይም አላማዎች ይኖሩታል፡፡

የጥናት አላማዎችን (Research objectives ) እንዴት እናስቀምጣለን?

የጥናት አላማ በአብዛኛው በሁለት ተከፍሎ ይቀመጣል፡፡

1. አጠቃላይ አላማ (General objective)

አጠቃላይ አላማን ለማስቀመጥ እራሳችንን በጥናት ስራው ላይ የምንሰራው ወይም ለማግኘት የምንሞክረው ነገር ምንድነው ብለን መጠየቅ ይኖርብናል፡፡ ለዚሁ ጥያቄ የምንሰጠው መልስም የጥናቱን አጠቃላይ አላማ ይሰጠናል ማለት ነው፡፡

የጥናት አጠቃላይ አላማ በአንድ አረፍተነገር በጥቅሉ ይቀመጣል፡፡ ዝርዝሩ በ ዝርዝር አላማዎች ላይ ይብራራል፡፡

2. ዝርዝር አላማዎች( Specific objectives)

በዚህኛው ክፍል ዝርዝር አላማዎችን እናስቀምጣለን፡፡ ዝርዝር አላማዎች ሲባል በዝርዝር እያንዳንዷን ልንሰራት ያሰብናትን ነገር specific አድርገን ማስቀመጥ አለብን፡፡ ዝርዝር አላማ በምናስቀምጥበት ጊዜ በነጥብ በነጥብ (bullet points) እያደረገን አንድ አላማ አንድ ሀሳብ ብቻ ይዞ መቀመጥ ይኖርበታል ፡፡ ዝርዝር አላማዎች SMART መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

👉Specific
👉Measurable
👉Attainable
👉Relevant
👉Time based

🙏 If you have any comment or question contact at

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Address


Addis Ababa
Addis Ababa