Doch HD

Doch HD

Share

12/05/2026

የፈረንሣይ ኤምባሲ ብሩክን አደነቀ 🔥

በማህበራዊ ሚዲያ በሚያቀርባቸው ፈጣንና ተአማኒነት ያላቸው መረጃዎች በማቅረብ የሚታወቀው ብሩክ ጫላ (ብሩክ ኒውስ) በፈረንሳይ ኤምባሲ አድናቆት ቀርቦለታል።

ኤምባሲው ባወጣው መረጃው ብሩክ በኢትዮጵያ በሚሊዮን የሚቆጠር ምልከታ ያላቸውን ይዘቶች የሚፈጥር መሆኑን በመጥቀስ በአጫጭር መረጃዎችና በሚያቀርባቸው ሃሳቦች ይታወቃል ብሏል።

ይህ የይዘት ፈጣሪ በኬኒያ ናይሮቢ በመካሄድ ላይ የሚገኘውን በኢኖቬሽን፣ በወጣቶች እንዲሁም የአፍሪካና ፈረንሳይ አጋርነት ላይ ያተኮሩ መረጃዎችን በቅርበት ለብዙሃን አድርሷል ብሏል።

ዶች ኤችዲ

Photos from Doch HD's post 11/05/2026

የክልሉ የጤናው ዘርፍ ጠንካራ ሥራና እምርታው 🔥

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ከተመሠረተ ጥቂት ዓመታት ቢቆጠሩም በጤናው ዘርፍ ያስመዘገባቸው እምርታዎች በተጨባጭ የህዝብን የጤና አገልግሎት ጥያቄ በመመለስ ላይ የሚገኙ ናቸው።

የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ተማም፤ የጤና መሠረተ ልማት ተደራሽነትን በማሳደግ ረገድ ባከናወነው ሰፊ ተግባር በአሁኑ ወቅት 12 የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች እና 5 ጠቅላላ ሆስፒታሎች በድምሩ 17 የመንግስት ሆስፒታሎች አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

ከእነዚህም በተጨማሪ 135 ጤና ጣቢያዎች እና 755 ጤና ኬላዎች በየቀበሌው ተደራሽ በመሆን መሠረታዊ የጤና አገልግሎትን ለኅብረተሰቡ እያቀረቡ እንደሚገኙ ጠቁመዋል።

የጤና ዘርፍ ስኬት ለአንድ አካባቢ ኢኮኖሚያዊ ጥንካሬ እና የዜጎችን ሰብአዊ ሁለንተናዊ ልዕልና የሚያረጋግጥ ትልቅ ምሰሶ መኾኑን የጠቀሱት አቶ ኢብራሂም፤ የግሉ የጤና ዘርፍ ተሳትፎም ለክልሉ የጤና ዘርፍ ስኬት ትልቅ አቅም መሆኑን በማንሳት በግሉ ዘርፍ 4 የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች እና 1,521 ሌሎች የጤና ተቋማት ጥራት ያለው የሕክምና አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆናቸውን አብራርተዋል።

የጤና መረጃ አያያዝን ወደ ዘመናዊ ዲጂታል ሥርዓት ለማሸጋገር በተከናወኑ ተግባራት በክልሉ የሚገኙ ሁሉም የመንግሥትና የግል የጤና ተቋማት በDHIS2 የመረጃ ሥርዓት ውስጥ እንዲካተቱ መደረጉንና በተለይም የኤሌክትሮኒክ ማኅበረሰብ ጤና መረጃ ሥርዓት (eCHIS) በ22 ወረዳዎች በሚገኙ 80 ጤና ጣቢያዎች እና 412 ጤና ኬላዎች ላይ ተዘርግቶ ተግባራዊ መደረጉ የመረጃ ጥራትንና ቅልጥፍናን ለማረጋገጥ ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ መኾኑን ኃላፊው አስረድተዋል።

በእናቶችና ሕፃናት ጤና ዙሪያም አገር አቀፍ ተሞክሮ ሊሆን የሚችል ውጤት መመዝገቡን የገለጹት አቶ ኢብራሂም፤ የእናቶች ቀዶ ጥገና አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማትን ቁጥር በማሳደግ፣ ከ162 በላይ አምቡላንሶችን በማሰራጨት እና የማኅጸን በር ካንሰር ልየታ ማዕከላትን ከ7 ወደ 44 በማሳደግ የሪፈራል ሥርዓቱና የሴቶች ጤና ጥበቃ እንዲጠናከር መደረጉን ጠቁመዋል።

የወባ ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በተደረገ ርብርብ የወባ ሞት ምጣኔን በ90 በመቶ መቀነስ መቻሉ ሌላው መጠቀስ ያለበት ስኬት መኾኑንና በዚህም ውጤታማ የአካባቢ ጥበቃ ስራዎችን እና የአልጋ አጎበር ስርጭትን ተግባራዊ በማድረግ የጠቅላላ የታካሚ ቁጥር በ50 በመቶ፣ በተኝቶ ታካሚ ደግሞ በ80 በመቶ መቀነሱን ተናግረዋል።

የማኅበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን (CBHI) ተጠቃሚዎች ቁጥር 2.1 ሚሊዮን መድረሱና 83 ከመቶ የሚሆኑ የጤና ባለሙያዎች የማኅበራዊ ጤና መድህን ተጠቃሚ መሆናቸው ለዘርፉ ቀጣይነትና ለባለሙያዎች የሥራ ተነሳሽነት መጎልበት ትልቅ ሚና እንዳለው የገለጹት ኃላፊው፤ የኦክስጅን ማምረቻ ማዕከላትና የደም ባንኮች ቁጥር ወደ 3 ማደጉ እንዲሁም የጤና ባለሙያዎች ቁጥር 11 ሺህ መድረሱ ክልሉ የሕዝቡን የጤና ዋስትና ለማረጋገጥ የሄደበትን ርቀት የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል።

በአጠቃላይ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የጤና አገልግሎት ተደራሽነት ከቁጥር ባለፈ በጥራትና በዲጂታል ሥርዓት እየተደገፈ እንደሚገኝ ያመለከቱት አቶ ኢብራሂም፤ በዘርፉ የተመዘገቡ ስኬቶችን በማስቀጠልና የታዩ ክፍተቶችን በመሙላት የክልሉን ሕዝብ የጤና ዋስትና ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ መሆኑንና አዳዲስ የጤና ተቋማትን በክልሉ በተለያዩ አከባቢዎች በመገንባት እንዲሁም በተገነቡት ውስጥ በኅብረተሰቡና በባለድርሻ አካላት ትብብር ቁሳቁስ የማሟላት ተግባር እየተከናወነ እንደሚገኝ ጨምረው ገልጸዋል።

ይህ ውጤት በቁርጠኝነት በሚሰሩ አመራሮች የተመዘገበ በመሆኑ የተጀመረውን የልማት ጉዞ ለቀጣይ 5 ዓመታት በተሻለ አቅም ለማስቀጠል የሕዝቡ ያልተቋረጠ ድጋፍና ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ማንሳት ተገቢ ይሆናል።

ዶች ኤችዲ

Want your business to be the top-listed Advertising & Marketing Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

http://t.me/doch_TG, http://youtube.com/@doch_hd, http://youtube.com/@doch_yt

Address


Addis Ababa
1000