Finot Saving and Credit Association
27/10/2022
#ቤተሰቦቻችን እንዴት አደራችሁ።
#ጊዜ እንደዋዛ ያልፋል ዛሬ በፈረንጆች ጥቅምት 27/2022 ነው።ከሶስት ቀናት በኋላ ሕዳር 1 ይላሉ።
#የሐበሻይቱ ምድር ኢትዮጵያ ምንም ከማንም አልተቀበለችም ከፈጣሪ ሁሉም ነገር ተችሩኣታል። እናም በራሱኣ አቆጣጠር ጥቅምት 17/2015 ነው
#የራሱኣ የዘመን አቆጣጠር አላት። ዘመኑን በወቅት ከፍላ ለወቅቶች ደግሞ ስያሜ ሰጥታ በወቅቶችም የሚከሰቱ ክስተቶችን እና በወቅቶች የሚገኙ ትሩፋቶችንም ጠንቅቃ ታውቃለች።
#አሁን ያለንበትን ወቅት ከመስከረም 26 በኋላ ያለውን ዘመነ ጽጌ ትለዋለች። አዝእርቶች ከአበባነት ወደ ፍሬነት የሚቀየሩበት ዘመን ለማለት ነው። ይህም የአበባ የፍሬ፣ወቅት እንደማለት ነው።
#አዝእርቶች ለመብቀል መበስበስ ይጠበቅባቸዋል። ለፍሬ ለመብቃት አስቸጋሪ የክረምቱን ቅዝቃዜ፣ ብርድ፣ ጎርፍ፣ ውሽንፍር በረዶ፣ማለፍ ይጠበቅባቸዋል። #ይህ ያለድካም ፍሬ እንደማይገኝ ጥሩ ማሳያ ነው።
#ውድ ቤተሰቦቻችን ለነገ ለምንተካቸው ትውልዶች ዛሬ ዋጋ መክፈል እና ለፍሬዎቻችን ፍሬን የሚያፈሩ ተቋማትን መስርቶ ስምን መትከል አስፈላጊ ነው።
#ፍኖት ለዘላቂ ልማት ለማህበረሰብ ተደራሽነት ሚናዋ እጅግ ከፍተኛ ነው። ብዙ ሀብታትን እየወለደች ትገኛለች።
#300 ብር እንዲህ ለትውልድ የምትሆን ፍሬ ማፍራት ከቻለች የበለጠ ብናሳድጋት ደግሞ ፍሬዋ እንዲሁ ብዙ ይሆናል።
እናም ከዛሬ እስከ ጥቅምት 30 መልእክታችን
በጥቅምት/2015 ፍሬን ሳናፈራ ሌላል ክረምት እንዳይመጣብን በጥቅምት ጥሩ ዘር እናፍራ እንላልን።
። የወሩ መሪ ቃላችን ነው።
ንቅናቄውን ተቀላቀሉ።
15/10/2022
።
በቀን 04/02/2015 በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ በተካሄደ አመታዊ ስብሰባ በ2014 አመት አመርቂ ውጤት ያስመዘገቡ ተቋማት በየዘርፉ የሰርተፊኬት እና የዋንጫ ሽልማት በመስጠት እውቅና ተሰጥቱኣል።
በመሆኑም በገንዘብ ቁጠባና ብድር ካሉ 17 ማኅበራት ውስጥ ፍኖት #2ኛ በመውጣት የዋንጫ እና የሰርተፊኬት ተሸላሚ ሁኖ 2014ን አጠናቋል።
ውጤቱ የተሰጠው በየሩብ አመቱ በሚወሰዱ ከ10 በላይ መመዘኛዎች እና መመልመያ መስፈርቶች ሲሆን #1ኛ ደረጃ በመሆን ያጠናቀቀው ከ17 አመት በፊት የተመሰረት ህብረት ስራ ማህበር። ይህም ከፍኖት ጋር ሲነጻጸር ከ14 አመት ያላነሰ ልምድ ያለው ሲሆን ከፍኖት የምስረታ ጊዜ አንጻር ስንመለከተው የፍኖት ውጤት እጅግ የሚመሰገን ሂደት መሆኑን ያሳያል።
ይህ ውጤት የተመዘገበው በአመራሩ እና በሰራተኞቻችን የተጠናከረ ሥራ፣ በልበ ብርሃን እና ቅን ቤተሰቦቻችን የባለቤትነትና የእኔነት የስነ ልቦና ውቅር የድርሻችሁን በመወጣታችሁ በመሆኑ ህብረት ስራ ማኅበሩ ያመሰግናችኋል።
#ስለሆነም በ2014 አመት በታዩ ጠንካራ ጎኖች በመበርታት የታዩ ክፍተቶችን በመድፈን ያጋጠሙ ችግሮችን በመፍታት አሁን ካለንበት ደረጃ ቀዳሚ በመሆን አመርቂ ውጤት እንደምናስመዘግብ በ3ወራት ውስጥ የታየው አፈጻጸም አመላካች መሆኑን እንገልጻለን።
# የተከበራችሁ ውድ ቤተሰቦቻችን አሁን የጀመርነው እና ያስመዘገብነው ውጤት የህብረታዊ አንድነታችን ውጤት መሆኑን በመረዳት በመደጋገፍ እና በመተሳሰብ፣ አዳዲስ ቤተሰቦችን አባል በማድረግ፣ ወርሃዊ ቁጠባችንን በጊዜ በመቆጠብ፣ የፍላጎት ቁጠባዎችን በመቆጠብ፣ እጣችንን በማሳደግ እና በሙያችን አዳዲስ አሰራሮችን በመቅረጽ አንድነታችንን እና የጋራ እድገታችንን በማፋጠን የሕብረታዊ አንድነት ስኬትን እንድናረጋግጥ እና የድርሻችንን እንድንወጣ ከወዲሁ እየጠቆምን_በድጋሜ_እንኳን_ደስ_አላችሁ_እንላለን።
ፍኖት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/ህብረት ስራ ማህበር።
#ተደጋግፈን ካሰብንበት እንደርሳለን።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Addis Ababa