Pink house
21/06/2023
# እናስታውስ
እራስዎን መውደድን መማር እና ስለራስዎ ጥሩ ስሜት እንዲሰማዎት ለሚያደርጉ ነገሮች ጊዜ ይውሰዱ። አንዲት ሴት ስለ ራሷ ጥሩ ስሜት ሲሰማት እና በማንነቷ ላይ ከምንም ነገር በላይ በራስ የመተማመን ስሜት ካደረባት ያ ቆንጆ ነው!😊
የ 🩷 💃💓 ቤተሰቦች channal ለወዳጅ አዝማዶቻችን ለጓደኞቻቸው እና በማድረግ አጋርነታቸውን ግለጹልን።🙏🙏🙏 እናመሠግናለን
19/06/2023
ለብ ያለ ውሃ ውስጥ ሎሚ ጨምቀው ዘውትር ቢጠጡ እነዚህን 10 የጤና ጥቅሞች ያገኛሉ፡፡
1. ጉበቶን ከመርዛማ ነገሮች ያፀዳሉ፡፡ለብ ባለ ውሃ ውስጥ የሎሚውን ጭማቂ (ፈሳሽ) ብቻ ሳይሆን የሎሚው ልጣጭ ጭምር ከተን የምንጠጣ ከሆነ ደረጃ 2 የጉበት ፀረ- መርዝ ማስወገድ ተግባራን ያከናውናል፡፡
2. ጉበቶ ሐሞት እንዲያመነጭ በማበረታታት ቅባታማ ምግቦችን ሰውነቶ እንዲፈጭ ይረዳል፡፡
3. ሎሚ ከፍተኛ አንቲ ኦክሲደንት ባህሪ ስላለው ሕዋሳታችን(cells) እንዳይወድሙ ይጠብቃቸዋል፡፡
4. በሎሚ ውስጥ ያለው አንቲ- ኦክሲደንት እና ፌቶኬሚካልስ የጉበት ሕዋሳት እንዲታደሱ ይረዳል፡፡
5. በሎሚ ውስጥ ያለው ሲትሪክ አሲድ የምግብ ስርዓተ ልመትን ያፋጥናል እንዲሁም የኩላሊት ጠጠርን (kidney stone) ያሟሟል፡፡
6. ሎሚ ከሰውነት ውጭ አሲድ ሲሆን በሰውነታችን ውስጥ አልካላይን ነው ስለሆነም በሰውነት ውሰጥ ያለውን የፒ ኤች ደረጃ ሚዛናዊ እንዲሆን ይረዳል በተጨማሪም በሽታን ይከላከላል፡፡
7. በሎሚ ውስጥ ያለው ከፍተኛ መጠን የቫይታሚን ሲ ንጥረ ነገር ጠንካራ የተፈጥሮ የበሽታ መከላከል አቅም እንዲኖረን ያስችላል፡፡
8. ሎሚ የደም ቅባትን በመሰባበር በዙ ሰዎች የሚያጋጥማቸውን የሀሞት ድንጋይዎች(gall stones) በሰውነታችን ውስጥ እንዳይፈጥር ያግዛል፡፡
9. ሎሚ ከፍተኛ የቫይታሚን ሲ ንጥረ ነገር ስላላው የዩሪክ አሲድ መጠንን በመቀነስ ሰዎች በሪህ (Gout) እና የአጥንት አንጓ
10. ብግነት (Arthritis) እንዳይጠቁ ይጠብቃቸዋል፡፡
11. ሎሚ ከአንደንድ የካንስር በሽታዎችም ይከላከላል፡፡
07/01/2022
ሰላም ውድ የ ተከታታዮች።
...“ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች...”— ኢሳይያስ 7፥14
በዚህ አምላካዊ ቃል መሰረት ዛሬ በዳዊት ከተማ መድሀኒት የሆነ እየሱስ ክርስቶስ ተወለደ ምድር በደስታ ተሞላች እረኞችም በቤተልሄም ካዩትና ከሰሙት የተነሳ አደነቁ እንኳን ለብርሀነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ መልካም ገና🎅🤶🎅 ከነቤተሰብዎ!!!።
😍❤️
24/12/2021
ሰላም ሰላም✋✋ 💃 ቤተሰቦች ባለፈው ስለ አመጋገባችን ይዤላችሁ እመጣለሁ ብዬ ነበር።
ይህው በቃሌ መሰረት😊 የምንመገበው ምግብ አይነትና ብዛት ለሰውነታችን ወፍረትና ቅጥነት ትልቅ አስተዋፆ አለው።
ውፍረት ለመቀነስ በብዛት ቬጂቴብል፣ሰላጣ፣ዓሳ፣እንቁላል፣ቱና፣ሰርዲን፣ሽሪምፕ፣ቺክን ብረስት እና ፍራፍሬ መመገብ
ከፍራፍሬም ብሉቤሪ ስትሮበሪ ማብዛት መመገብ ብዙ ካሎሪ ለማቃጠል ትልቅ ጥቅም አለው። ለዲቶክስ ጥሩ ስለሆነ
ግሪን ሻይ ከምግብ በኃላ መጠጣት እንደ ኦቾሎኒ፣አልመንድ
ያሉ ጥራጥሬ በሰላጣ ላይ አድርጎ ወይም እንደ እስናክ መውሰድ።
መውሰድ የሌለብን ምግቦች ድንች ፣ሩዝ፣ስጋ፣ፓስታ፣ዳቦ፣ ስኳር፣ለስላሳ መጦች እንደዚህ ስላችሁ ምን እንብላ እንዳትሉ😁 ብዙ ጊዜ ስታርች ያላቸውን ምግቦች አለመመገብ ወይም በካርቦሀይድሬት ትንሽ የሆነውን
መጠቀም ዳቦ ሲያስፈልገን እንደ አልመንድ፣ኮኮናት ዱቄት
መጠቀም። ጤፍ ጤነኛ ቢሆንም ካርቦሀይድሬቱ በጣም ብዙ
ነው ከነዚህ ድቄት ስታወዳድሩት ማለት ነው። ወጥ ሲያምረን
መመገብ ይቻላል ግን ሳይበዛ ቲማቲም ቁርጡ ዘይት የወይራ ዘይት መጠቀም ።
ማለት ነው ማታ ከመሸ መብላት አይመከርም ከ12ሰዐት በኃላ የሚጠጣ ነገር
እንደ ሻይ በጣም የረሀብ ስሜት ካለ ፍሩት ወይም ጥራጥሬ
መውሰድ ሳይበዛ ማታ መብላት ስታቆሙ ብዙ ለውጥ አለ
እናም ሞክሩት ሀሳቡ ካላችሁ comment ላይ ማስቀመጥ ትችላላችሁ😘😘
like and share🙏🙏🙏
💃💃💃
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Telephone
Website
Address
Addis Ababa