Pastor Binyam Zenebe

Pastor Binyam Zenebe

Share

06/07/2024

☝ ያዕቆብ 1÷20
“የሰው ቍጣ የእግዚአብሔርን ጽድቅ አይሠራምና።”
...................................................................
🗣 የልብ ለልብ ግንኙነታችን እንዲታደስ
እና እንዲታነጽ። መልክት_አለኝ❗

+ በዘመኑ ላይ የቃሉን ብርሃን እድናኖር የተጠራን እኛ
እግዚአብሔርን ገላጭ አገልግሎት የክርስቶስ መሆኑን
እንረዳ። አመጸኝነትን : ክፋትን : ነውርንም : ስድብንም
ከእግዚአብሔር ጉባዔ ለማራቅ ከእግዚአብሔርም እርሻ
አረሙን ለመንቀል :- የልባችን ዓይኖች እና መንፈሳዊ
ደረጃችን ምን ያህል ከፍ ብሎአል ?
ከጨለማስ እውቀት ምን ያህል ርቀናል ?

+ መልክታችን ስህተት የማወጣት ትኩረት ብቻ ያለው
ሳይሆን መንፈስ እና ጸጋ ለማካፈል የበረታ ሊሆን
እንደ ቃሉ ይገባል። የድንዛዜው ብዛት የት እየወሰደን
እንዳለ ማየት አለብን።
......... + .........
[ ። ]
..........+ .........
ምክሬ ከቅንነት ነው
➡ የራሳቹሁን ጽድቅ አታቁሙ አደጋ አለው።
የራሳቸውን ጽድቅ ያቆሙ ሰዎች
.....................................
🗝 የኮነኑትን ራሳቸው ሆኑት
🗝 የተቃወሙት አገኛቸው
🗝 የጠሉት ወረሳቸው።

[ ። ]
እረኛ ቢንያም ዘነበ
ቀን 29 / 10 / 2016 🙏

14/06/2024

!!!
🏛🏛🏛🏛
👉መንፈሳዊው አለም ቀድሞ የፈጠረን እንደገና በሥነ ምግባር ለመፍጠር የሚሰራበት አለም ነው።
🗣 አቦው እንዲህ ይላሉ..
[ የሰው ልጅ ጤና ሥነ ምግባሩ ነው። ]

#አገልጋዮቹ❗
¶ ከበላያቸው ንፋስ ሳይሆን እግዚአብሔር እዳለ የሚያምኑ ያሉበትን ሥፍራ እንደ ንስሐ የቆጠሩ።
ሰውን እግዚአብሔር በነጻነት መፍጠሩ ለሰው ያለውን
ክብርና ፍቅር የተረዱ ናቸው 👉 አገልጋዮቹ

¶ ሚዛን ሚዛን ለመሆን ተንቀጥቅጦ ነው አገልጋይነት
ቀላልነት አይደለም በአንድ ጊዜ ሁለት ሰው መሆንም
አይደለም አገልጋይነት ልኬ ይሔ ነው ማለት መቻል ነው።
የልክን ድንበር አልፎ መባዘን አይደለም ተመሪ ሆና መሪ
መሆን ታራሚ ሆኖ አራሚ መሆን እንጂ። ተባረኩ
እረኛ ቢንያም ዘነበ
[ ቀን 7 / 10 / 2016 ]

Want your place of worship to be the top-listed Place Of Worship in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address


Addis Ababa