Feta Daily -Wollo
የሰሜኑን ጦርነት ድጋሜ ላለማየት ሁሉም መነቃቃት አለበት፤ አጠገብህ ያለው ገፋ አድርግና ሰላም ለዘላለም በለው፠
05/02/2026
With Yirga Sisay Kitaw / ይርጋ ሲሳይ ቅጣው – I just got recognised as one of their top fans! 🎉
12/12/2024
💥ደቡብ ወሎ ዞን - ተውለደሬ ወረዳ - አርዲቦ ሀይቅ💥
ውብ መልከዓ ምድር - መልካም ቀን
Visit Wollo - Tourism
11/12/2024
አማራጭ የሌለው ምርጫችን ክፍል - 2
**************************************
//ወሎ ተሪሸሪ
******************************************
✍️በማህበረሰባችን ውስጥ እንደ ብርሃን ብቅ ብለው የማህበረሰቡን አልፎ የሀገር ተስፋ ተጥሎበት ሚልየኖች ቁጥራቸው በመፍታች ያላቸውን በመለገስ በተስፋ ከሚጠብቁት ትልቁ እና አንዱ ተቋም ቢሆን ወሎ ተሪሸሪ እና ኬር ሆስፒታል አንዱ ነበር።
✍️በወሎ ተሪሸሪ እና ኬር ሆስፒታል ማስገንቢያ በቢልየን ገንዘብ በሀገር ውስጥ እና በውጭው አለም የተሰበሰበ ሲህን አሁን ተቋሙ ሆነ ገንዘቡ የት እና እንደት እንዳለ እየተዘነጋ እና እየተረሳ መጥቷል። ለዚህ ትውቋም ግንባታ እጅግ ሰፊ ቦታ ተሰጥቶ አሁንም ቦታው አፉንንከፍቶ እንደተቀመጠ የአደባባይ ምስጢር ነው።
✍️ይህ ተቋም በወቅቱ በተገለፀው እና ይፋ በተደረገው መሰረት በሀገር ደረጃ ቀርቶ ከመላው አፍሪካ ሪፈር በመባል እየመጡ ለመታከው አገልግሎት ሊሰጥ የሚችል አቅም የነበረው ተቋም እንደሚሆን ነበር።
✍️ተቋሙ ይህ ከነበረ ደግሞ ማህበረሰባችን ያጣቸው መልካም እድሎች የሚከተሉት ናቸው ፦
እንደ ማህበረሰብ ያለው ፋይዳ
****************************
☘️ይህ ፕሮጀክት እውን ሲሆን የአካባቢው የሆቴል ቱሪዝሙን ያሳድጋል ፤
☘️ ለማህበረሰቡ ትልቅ የህክምና አገልግሎት በቅርቡ ያገኛል ፤
☘️ ለሀገር እና ለማህበረሰቡ ትልቅ የህክምና የምርምር ተቋም በመሆን ያገለግላል ፤
☘️ ለማህበረሰቡ ትልቅ የኢኮኖሚ ምንጭ ይሆናል
☘️ ለብዙሃን የማህበረሰብ ክፍል የስራ እድል ይፈጥራል ☘️ የወሎን ማህበረሰብ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ በእጅጉ ያሳድጋል ፤
☘️ የማህበረሰባችን ክፍል አካባቢያቸውን ለቀው ለስደር ከሚሄዱ በቅርቡ የስራ እድል በማመቻቸት በአካባቢያቸው እንዲያለሙ እና እንዲሰሩ ያስችላል፤
☘️ ይህን ፕሮጀክት ተያይዞ ለሌሎች ካምፓኒዎች ፣ ድርጅቶች እና ተቋማት ወደ አካባቢው መሳብ አስተዋፅዖ ያበረክታል፤
☘️ የከተሞች እድገትን ያፋጥናል ፤
☘️ ህሙማኑ እና ሰራተኛው ሀገራዊ እና አለማቀፋዊ ስለሚሆኑ የወሎን መልካም እሴት በማሳየት ትልቅ እና ጉልህ ሚና ይኖረዋል፤
☘️ ሀገራዊ እና አለማቀፋዊ ልምድ ልውውጦሽን ማህበረሰባችን ያገኛል።
🇪🇹እንድው ሀገር ያለው ፋይዳ
**************************
☘️ ዜጎች ለህክምና ወደውጭ የሚያደርጉትን እንግልት እና የዶላር እጥረት ይቀንሳል፤
☘️ ዜጎች በሀገራቸው በሚኖራቸው ትልቅ ተቋም ኩራት ይሰማቸዋል ፤
☘️ ከጎረቤት ሀገራት መጥተው የሚታከሙ ዜጎች ገቢያችን ይጨምራል ፤
☘️ የሀገር መልካም ገፅታ ይገነባል ፤
☘️ የዜጎች የስራ እድል ይጨምራል፤
☘️ በሀገራቸው ተምረው በውጭው አለም ለስራ የሚኮበልለው የሀኪም ቁጥር ይቀንሳል።
ስለዚህ መንግስት በተደጋጋሚ ከመለስ ዜናው ጀምሮ እነ ሀይለማርያም ደሳለኝ እንድሁም ብልፅግና መንግስት ቃል በመግባት ህዝቡን በተስፋ ሆዱን መንፋት ሳይሆን የታለመው እንድሁም የተሰበሰበው የህዝብ ገንዘብ መሬት ላይ በማውረድ የህዝባችነን ጥያቄ ሊመለስ ይገባል።
እጅግ የሚያሳዝነው ነገር ቢኖር ወሎ መች ይሆን ለህዝቡ እና ለማህበረሰቡ የሚጠቅም ስራ የሚሰራ አመራር የሚኖረው። ባለፈው በክፍል አንድ 👇👇
https://www.facebook.com/100003152187532/posts/5462780363836982/?d=n
እንዳሳወኩት የደሴ ኮምቦልቻ ሽንቁር መንገድ የታገደው በክልሉ የልማት ጥላቻ እንደሆነ አሳውቄያለሁ ይህን እንኳን ለምን ብሎ የክልል ምክር ቤት ሊሞግት የሚችል እንድሁም በተወካዩች ምክር ቤት ሊያቀርብ የሚችል አንድም ተወካይ አለመኖሩ እጅግ የሚያሳዝን ነው።
ስለሆነ አሁንም ይህን እንደ አይናችን የምናየውን ተቋም በተገባው ቃል እና እቅድ መሰረት ወደ መሬት እንዲወርድ እንጠይቃለን።
ሀገራችን በአሁኑ ሰዓት ብዙ አዳድስ ፕሮጀክቶችን እየሰራች እንደሆነ እሙን ሲሆን ይህን የወሎ ተሪሸሪ ኬር ሆስፒታል በመገንባት መንግስት ህዝባችን ለሀገረ መንግስት ግንባታ የከፈለውን መስዋትነት ታሳቢ አድርጎ ሊክሰው ይገባል።
የወሎ ማህበረሰብ ይህ ብቻ ሳይሆን የሚከተሉት መሰረታዊ ጥያቄወችን በተደጋጋሚ ሲጠይቅ የኖረ ሲሆን አንዳቸውም አልተፈቱም።
🌴 የኮምቦልቻ ሃራ ገቢያ ባቡር ፕሮጀክት
🌴የደሴ ኮምቦልቻ ሽንቁር መንገድ ፕሮጀክት
🌴 የመካነ ሰላም አየር መንገድ ፕሮጀክት
🌴የዋግ ዩኒቨርሲቲ ግንባታ
🌴የቆቦ ጊራና ውሃ ፕሮጀክት
🌴የመርሳ ቆዳ እና ሌጦ ፋብሪካ መቆም
🌴 የሰቆጣ አስፋልት ስራ
🌴የወሎ ሀይቆች ልማት ፕሮጀክት
🌴 የነ ጊሸን ማርያም አስፋልት ስራ
🌴የወሎ ዞኖች እና ወረዳዎች በጀት ጉዳይ
🌴እና ሌሎች መሰረታዊ ጥያቄ የነበሩ ሲሆን ፦
ይህ የሚያሳየው በክልሉ እና በፌደራል መንግስቱ የተሰጠው የልማት ጥያቄ ትኩረት ግምት የወረደ ሳይሆን የወደቀ መሆኑን እንደ ማህበረሰብ እንረዳለን።
|ለሁለተኛ ጊዜ የተፖሰተ|
ጥያቄያችነን ሸር በማድረግ ያጋሩ 🙏🙏🙏
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Addis Ababa