Islamic World

Islamic World

Share

13/05/2022
13/05/2022

በአንድ ወቅት ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ቢላል ኢብኑ ረባህን ከኃላው በፍቅር ስሜት እቅፍ አድርገው ይይዙትና ድምፃቸውን ቀይረው...

 ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) :- "እኔ ማን ነኝ"?

ቢላል (ረ.ዐ) :- ዑመር (ረ.ዐ) ነህ?

 ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) :- አይደለሁም

ቢላል (ረ.ዐ) :- አቡብክር (ረ.ዐ) መሆን አለብህ?

 ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) :- አሁንም ተሳስተሃል

ቢላል (ረ.ዐ) :- በቃ ዑስማን (ረ.ዐ) ነህ?

 ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) :- አላወቅከኝም

ቢላል (ረ.ዐ) :- ዓሊ (ረ.ዐ) ነህ ማለት ነው... እያለ ያቀፈውን ሰው ማንነት ሲጠይቅ ይቆያል። ከዚያም ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ለቀቅ አደረጉትና ከፊት ለፊቱ በመምጣት "ቢላል ሆይ! እውነት እኔ መሆኔን አላወቅክም ነበር እንዴ"? ሲሉ ጠየቁት ቢላልም "የአላህ መልእክተኛ ሆይ!" በደንብ አውቄዎታለሁኝ ነገር ግን ለረጂም ጊዜ እንድታቅፉኝ ስለፈለኩኝ እንጂ ሲል መለሰላቸው።

ሰለዋቱ ረቢ ወሰላሙ አለይከ ያ ረሱሊላህ

12/05/2022

“የሰራተኛን ክፍያ ላቡ ሳይደርቅ በፊት የሰራበትን ክፈሉት።”
˙·٠•● ነቢዩ ﷺ ስለአሏሁ አለይሂ ወሰለም ●•٠·˙
 ኢብኑ ማጃህ ዘግበውታል (2443)

10/05/2022

ዋኢላት ኢብኑ አል-አስቀዕ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፡‐
በወንድምህ ላይ በደረሰ ችግር አትደሰት :: አላህ እርሱን ሰላም አድርጎ አንተን ይፈትንሃልና ::

 ((ትርሚዚ ዘግቦታል ))

وعن واثلة بن الأسقع رضي الله عنه قال‏:‏ قال رسول الله صلى الله عليه وسلم ‏:‏ ‏

"‏ لا تظهر الشماتة لأخيك، فيرحمه الله ويبتليك‏"‏‏.‏

 ‏(‏‏(‏رواه الترمذي وقال‏:‏ حديث حسن‏)‏‏)‏

◦•●◉✿ ከሐዲሡ የምንማራቸው ቁም ነገሮች ✿◉●•◦

 በሙስሊም ወንድም ላይ በሚደርሰ መከራ መደሰት ሐራም ነው

 ይህን የሚያደርግ ሰው ከመጪው አለም በፊት በዚህች ዓለም ይቀጣል ::

 እውነተኛ ሙስሊም ማለት የሙስሊሞች ስቃይና መከራ እርሱንም የሚያንገበግበውና የሚሰማው ነው።



በየቀኑ የሚለቀቁ ሃዲሶችን ለመከታተል ግሩፑን ይቀላቀሉ ጆይን ያድርጉ

Want your place of worship to be the top-listed Place Of Worship in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Address


Addis Ababa