Hamak attention

Hamak attention

Share

Ere amsale/Ethiopia 2022 ኧረ አምሳለ (ኢትዮጵያ) ወቅታዊ ግጥም @ hamak attention 24/06/2022

https://youtu.be/NO7nQVRnyCU

Ere amsale/Ethiopia 2022 ኧረ አምሳለ (ኢትዮጵያ) ወቅታዊ ግጥም @ hamak attention ኧረ አምሳለby Hamakኧረ አምሳለ እቴ እንዴት ነሽአለች በመከራ እንባዋን ስትዘራእኔን እኔን ይክፋኝበሞላ ማድጋ ባልጎደለ መሶብ ጦም ማደርሽ ከፋኝ

22/03/2022

በህይወት እስካለህ ልትሳሳት ፣ ልትወድቅ ትቸላለህ ፣ ሰዎች ላይቀበሉህ
ይችላሉ ፣ ወይም ሀሳብህን ላይረዱህ ፣ ቦታ ላይሰጡህ ይችላሉ ፣ በእጅህ ላይ
ያለው ሙሉ በሙሉ አመድ ሆኖ ልታገኘው ትችላለህ ፣ ሰዎች ሊጠሉህ ፣
ሊያሙህ ፣ ወይ ስም ሊያወጡልህ ፣ አሊያም ሊስቁብህ ፣ ይችላሉ።
:
" በህይወት ውስጥ ትልቁ ስህተት ለሁሉም ሰው ትክክለኛ ሆኖ ለመታየት
መሞከር ነው። መልካም ብትሆን ክፉዎች ይጠሉሀል። አዋቂ ብትሆን አላዋቂዎች
ባዶነታቸውን ስለምትገልጥባቸው አብዝተው ይፀየፉሀል። ብርሃናዊ ራዕይ
ቢኖርህ የጨለምተኞችን ጨለማ ስለምታሳይ መኖርህ ያንገበግባቸዋል። ነፃ
አውጭ ብትሆን ጨቋኞች ያሳድዱሀል።
:
ምናለፋህ በአለም ስትኖር በሙሉ ድምፅ ልትወደድም፣ ልትጠላም አትችልም።
ስለዚህ በደረስክበት ሁሉ ልክ እንደ ውሃ ቅርፅህን አትቀያይር! ከምንም በላይ
በፈጣሪህ ፊት ትክክል ሁን!"
አንድ ነገር ልንገራችሁ!
:
በህይወታችሁ ማንንም አትውቀሱ
ጥሩ ሰዎች ደስታን ይሰጡዃችሀል
መጥፎ ሰዎች ልምድ ይሆኑዃችሀል
ክፉ ሰዎች ማስጠንቀቂያ ይሆኑዃችሀል
ምርጥ ሰዎች ትዝታ ይሆኑዃችሀል

16/09/2021

#የሚያሳስበን ችግሩ ሳይሆን ችግሩን የምናይበት መንገድ ቢሆንስ? #

⚜ምንም እንኳን ስለመልካም አስተሳሰብ እና ስለ ቀና ኑሮ ደጋግመን ብንደሰኩርም አንድ መዋጥ ያለብን እውነት ግን አለ። ይህም ህይወት ነጭ እና ጥቁር አይደለችም። የጠበቅናቸው የማይከሰቱባት ያልጠበቅናቸው የሚከሰቱባት የማትተነበይ እንጂ። ችግር የማይደርስበት ኑሮ፤ ከመከራ ከሃዘን የራቀ ህይወት ለማንም አልተሰጠም። ማንም ሰው ሁሉ ተሳክቶለት እና ሞልቶለት የሚኖር አይኖርም (ምንም እንኳን ከላይ በምናያቸው ነገሮች ሁሉ ነገር የተሳካላቸው ሰዎች ያሉ ቢመስሉንም)። አነሰም በዛ እያንዳችን የምናምርርባቸው ነገሮች በህይወታችን ውስጥ አሉ።

መማረር ማለት ያለውን እውነታ መቀበል አለመቻል ነው ይላል። የምናማርረው ኑሮዋችን እኛ በፈለግነው መንገድ ስላልሄደ አልያም እንዲከሰቱ የማንፈልጋቸው ነገሮች ስለተከሰቱ ነው። እንዲህ አይነት ችግሮች ሲፈጠሩ እራሳችንን የምናወጣባቸው መፍትሄዎች አሉ። ለዚህች አጭር ጽሁፍ “The power of Now” ከተሰኘው መጻህፉ ላይ ያገኘኋቸውን ሶስት ነጥቦች ሰፋ አድርጌ ላካፍላችሁ ወደድኩኝ።

1⃣ Remove yourself from the situation–
አንዳንዴ ችግር ብለን የምንወስዳቸው ወይም የምጨነቅባቸው ነገሮች ከኛ ውጪ በሆኑ ነገሮች የሚከሰቱ ናቸው ። የሰው ልጅ ደግሞ እራሱን ከመለውጥ ባለፈ የሌላውን ሰው አስተሳሰብ እና ማንነት ለመለወጥ አይቻለውም። ስለዚህ የምንማረርባቸው ነገሮች ከኛ የመነጩ ካልሆኑ ፤ከሁኔታው አልያም ከአካባቢው እራሳችንን በማራቅ ሰላማችንን ማግኘት እንችላለን። በዙሪያችን ያሉ ነገሮች የሚያደርሱብንን ተጽዕኖ ሙሉ በሙሉ ማስወገድ ባንችልም፤ ሁኔታዎቹ ግን ሰላም እና ደስታችንን እንዳያናውጡ ጥንቃቄ ማድረግ አለብን።

2⃣ Change it– የማንፈልገውን ነገር ለመለወጥ መጣር- ብዙዎቻችን ስለችግሮቻችን ቀን እና ማታ እናወርለን ነገ ግን ለምፍትሄ የሚሆን ጊዜ የለንም። ለምሳሌ ስራ በማጣቱ የሚማረር ወጣት ቀን እና ማታ ስለስራ አጥነት ቢይወራ ምንም መፍትሄ የለውም። ከሱ የሚጠበቀው ሳይታክት ማመልከቻዎቹን ማሰራጨት ፤ ክህሎቶቹን ማዳበር እና ስራ ሊያገኝባቸው የሚችልባቸውን መንገዶች ማጤን ነው። ስለኑሮዋችን ብናማርር፤ ሌሎችን ብንወቅስ፤ እንዲህ ቢሆን ኖር እያልን በሃዘን ብንብሰከሰክ፤ ሁኔታውን ለመለወጥ ሙከራ እስካላደርግን ድረስ ምንም ጠብ የሚል ነገር የለም።

3⃣ Accept it totally– በልጅነቴ የሰማሁት ጸሎት እስካሁን ድረስም አብሮኝ አለ። ለኔ ትልቅ ትርጉም ስላለው ችግሮች ሲገጥሙኝ ሁሌም አስታውሰዋለው። ጸሎቱ እንዲህ የሚል ነው “በህይወቴ ልለውጣቸው የምችላቸውን ነገሮች እንድለውጥ ብርታቱን ስጠኝ፤ ልለውጣቸው የማልችላቸውን ነገሮች እንድቀበል ጽናቱን ስጠኝ፤ እናም በሁለቱ መካከል ያለውን ልዩነት እንዳስተውል ጠቢብነቱን አድለኝ” ይላል። አዎ ልንለውጣቸው የምንችላቸው ነገሮች ላይ ጉልበት እና ጊዜያችንን በጭንቀት ከማሳለፍ ይልቅ መፍትሄው ላይ ማተኮር ይኖርብናል። በሌላ በኩል ከኛ ቁጥጥር ውጪ የሆኑ ነገሮችን መለወጥ ካልቻልን ተቀብለናቸው መኖርን መልመድ አለብን።

🔑ከላይ የሰፈሩት መፍትሄዎች እንዳሉ ሆነው ችግሮቻችንን ይበልጥ ግልጽ በሆነ እና ቀለል ባለ መልኩ እንድናይ የሚረዳንን አንድ ትልቅ ነጥብ ላክል እሻለው። ይኸውም ችግሮችን የምናይበትን መንገድ በተመለከተ ነው።በብዛት የሚያሳስበን ችግሩ ሳይሆን ችግሩን የምናይበት መንገድ ነው። አይምሮዋችን እንደ እሳት ነው ለበጎ ነገር ከተጠቀምንበት ህልውናችን ፤ለመጥፎ ነገር ከተጠቀምንበት ደግሞ መጥፊ

ነብስ ይማር R.I.P ..... ስለ አለማየሁ እሸቴ በጥቂቱ (ethiopian musician Alemayehu eshete ) 14/09/2021

ነብስ ይማር.....ስለ አለማየሁ እሸቴ በጥቂቱ (ethiopian musician Alemayehu eshete )

ነብስ ይማር R.I.P ..... ስለ አለማየሁ እሸቴ በጥቂቱ (ethiopian musician Alemayehu eshete ) አለማየሁ እሸቴ ወደሙዚቃው እንዴት ገባ ህይወቱስ ምን ይመስል ነበር

አዲስ አማሪኛ የፍቅር ግጥም ''መለያየት ሞት ነው" (new amharic romantic poem-meleyayet mot new) 14/09/2021

አዲስ አማሪኛ የፍቅር ግጥም ''መለያየት ሞት ነው" (new amharic romantic poem-meleyayet mot new)

አዲስ አማሪኛ የፍቅር ግጥም ''መለያየት ሞት ነው" (new amharic romantic poem-meleyayet mot new) እንኳን ወደ ፟ሐ-mak attention በሰላም መጣቹ በዚ ቻናል -ታላላከቅ የሙዙክቃ ባለሞያዎች ኢንተርቪዩ (ጥበብን እንወቃት) ...

New ግጥም "ትዝታ" (Tizta amharic romantic poim with lyrics) 14/09/2021

New ግጥም "ትዝታ" (Tizta amharic romantic poim with lyrics)

New ግጥም "ትዝታ" (Tizta amharic romantic poim with lyrics)

Want your establishment to be the top-listed Arts & Entertainment in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Address


Addis Ababa