Hashim tube

Hashim tube

Share

08/12/2025

ሙስሊም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

3፥102 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ተገቢውን መጠንቀቅ ተጠንቀቁት፡፡ እናንተም *”ሙስሊሞች ኾናችሁ እንጅ አትሙቱ”* ፡፡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ حَقَّ تُقَاتِهِۦ وَلَا تَمُوتُنَّ إِلَّا وَأَنتُم مُّسْلِمُونَ

መግቢያ
“ሙሥሊም” مُسْلِم የሚለው ቃል “አሥለመ” أَسْلَمَ “ታዘዘ”፣ “ተገዛ”፣ ” አመለከ” “ሁሉ ነገሩን ሰጠ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙ “አቢድ” عَابِدُ ማለትም “አምላኪ” አሊያም “ቃኒት” قَانِتِ ማለትም “ታዛዥ” ማለት ነው፤ አላህ ለኢብራሂም “አሥሊም” أَسْلِمْ ማለትም “ታዘዝ” ብሎ ሲለው እርሱም ለዓለማት ጌታ “አሥለምቱ” أَسْلَمْتُ ማለትም “ታዘዝኩ” አለ፦
2፥131 ጌታው ለእርሱ *”ታዘዝ”* ባለው ጊዜ መረጠው፡፡ ለዓለማት ጌታ *”ታዘዝኩ”* አለ፡፡ إِذْ قَالَ لَهُۥ رَبُّهُۥٓ أَسْلِمْ ۖ قَالَ أَسْلَمْتُ لِرَبِّ ٱلْعَٰلَمِينَ
22፥34 *አምላካችሁም አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ ለእርሱም ብቻ ታዘዙ*፡፡ ለአላህ ተዋራጆችንም አብስራቸው፡፡ فَإِلَـٰهُكُمْ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ فَلَهُ أَسْلِمُوا ۗ وَبَشِّرِ الْمُخْبِتِينَ
39፥54 «ቅጣቱም ወደእናንተ ከመምጣቱና ከዚያም የማትርረዱ ከመኾናችሁ በፊት ወደ ጌታችሁ በመጸጸት ተመለሱ፡፡ *ለእርሱም ታዘዙ*፡፡ وَأَنِيبُوا إِلَىٰ رَبِّكُمْ وَأَسْلِمُوا لَهُ مِن قَبْلِ أَن يَأْتِيَكُمُ الْعَذَابُ ثُمَّ لَا تُنصَرُونَ

“ታዘዙ” ለሚለው ቃል የመጣው “አሥሊሙ” أَسْلِمُوا ሲሆን “ሙስሊም” ማለት አንዱን አምላክ የሚታዘዝ ታዛዥ ማለት ነው። ስለዚህ ሙስሊም ማለት የዓለማቱን ጌታ አንዱን አምላክ በብቸኝነት የሚያመልክና የሚታዘዝ ማለት ነው። “ኢሥላም” إِسْلَٰم ደግሞ ሃይማኖቱ ሲሆን “ሢልም” سِّلْم ማለትም “መታዘዝ” ወይም “መገዛት” ማለት ነው፦
2፥208 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ሁላችሁም *”በመታዘዝ”* ውስጥ ግቡ፡፡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ٱدْخُلُوا۟ فِى ٱلسِّلْمِ كَآفَّةًۭ

ይህ “መታዘዝ” ደግሞ በዲን ይመጣል፤ “ዲን” دِين ማለት “ሃይማኖት” “ፍትህ” “ፍርድ” “ሕግ” “መርህ” ማለት ነው፤ አላህ ዘንድ ያለው ሃይማኖት ኢስላም ብቻ ነው፤ ከኢስላም ሌላ ሃይማኖትን የሚፈልግ ሰው ፈጽሞ ተቀባይ የለውም፤ እርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም ከከሳሪዎቹ ነው፦
3፥19 አላህ ዘንድ የተወደደ ሃይማኖት *“ኢስላም”* ብቻ ነው፡፡ إِنَّ ٱلدِّينَ عِندَ ٱللَّهِ ٱلْإِسْلَٰمُ
3፥85 *”ከኢስላም ሌላ ሃይማኖትን የሚፈልግ ሰው ፈጽሞ ከርሱ ተቀባይ የለውም”*፡፡ እርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም ከከሳሪዎቹ ነው፡፡ وَمَن يَبْتَغِ غَيْرَ ٱلْإِسْلَٰمِ دِينًۭا فَلَن يُقْبَلَ مِنْهُ وَهُوَ فِى ٱلْـَٔاخِرَةِ مِنَ ٱلْخَٰسِرِينَ

“ሠለም” سَلَم ማለት ደግሞ “ታዛዥነት” በሚል መጥቷል፦
16፥87 አጋሪዎቹ በዚያ ቀንም *ታዛዥነታቸውን* ወደ አላህ ያቀርባሉ፡፡ ይቀጣጥፉት የነበሩትም ሁሉ ከእነርሱ ይጠፋቸዋል፡፡ وَأَلْقَوْا إِلَى اللَّهِ يَوْمَئِذٍ السَّلَمَ ۖ وَضَلَّ عَنْهُم مَّا كَانُوا يَفْتَرُون

04/11/2025

የአሏህ ህልውና

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

22፥6 ይህ አላህ እርሱ መኖሩ የተረጋገጠ፣ እርሱም ሙታንን ሕያው የሚያደርግ፣ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ በመሆኑ ነው፡፡ ذَٰلِكَ بِأَنَّ اللَّهَ هُوَ الْحَقُّ وَأَنَّهُ يُحْيِي الْمَوْتَىٰ وَأَنَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ

በአንድ ወቅት የነገረ ልቦና ምሁር ሲይግመን ፍሮይድ፦ "ሁሉን የሚቆጣጠር እና የሚመግብ አምላክ ፍቅር፣ እንክብካቤ እና ጥበቃ በሚያስፈልገው በሰው ሥነ ልቡና የተፈጠረ ነው"The God who controls and provides everything, is created by the human psyche in response to its need for love, saftey and security" በማለት ኢ-አማኝነቱን ገልጿል። ይህ የኢልሓድ እሳቤ ነው፥ በፈጣሪ እሳቦት ውስጥ ኢማን፣ ኩፍር እና ኢልሓድ ተጠቃሽ ናቸው።
"ኢልሓድ" إِلْحَاد የሚለው ቃል "አልሐደ" أَلْحَدَ‎ ማለትም "ኢ-አመነ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን በአምላክ መኖር "ኢ-አማኒነት"atheism" ማለት ነው፥ በነጠላ "ሙልሒድ" مُلْحِد ማለት "ኢ-አማኝ"atheist" ማለት ሲሆን "ሙልሒዱን" مُلْحِدُون‎ ደግሞ የሙልሒድ ብዙ ቁጥር ነው። ሙልሒድ የኢልሓድ እሳቤ የሚያራምዱ ናቸው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 87 ሐዲስ 21
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ “ነቢዩም፦ “ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “አሏህ ዘንድ የተጠሉ ሦስት ሰዎች አሉ፦ “በሐረም ውስጥ ያለ ሙልሒድ፣ የጃሂሊያህን ሡናህ ኢሥላም ውስጥ ለማስቀረት የሚፈልግ እና ያለ ሕግ የአንድ ሰው ደም ማፍሰስ የሚፈልግ ናቸው"። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم قَالَ أَبْغَضُ النَّاسِ إِلَى اللَّهِ ثَلاَثَةٌ مُلْحِدٌ فِي الْحَرَمِ، وَمُبْتَغٍ فِي الإِسْلاَمِ سُنَّةَ الْجَاهِلِيَّةِ، وَمُطَّلِبُ دَمِ امْرِئٍ بِغَيْرِ حَقٍّ لِيُهَرِيقَ دَمَهُ. ‏

"ዉጁድ" وُجُود የሚለው ቃል "ወጀደ" وَجَدَ ማለትም "አለወ" "ኖረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "መኖር" ሃልዎት" "ህልውና" ማለት ነው፥ "ዉጁዱል ሏህ" وُجُود الله ማለት "የአሏህ ህልውና"the existence of Allah" ማለት ነው። የአሏህ መኖር የተረጋገጠ ነው፦
22፥6 ይህ አላህ እርሱ "መኖሩ የተረጋገጠ"፣ እርሱም ሙታንን ሕያው የሚያደርግ፣ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ በመሆኑ ነው፡፡ ذَٰلِكَ بِأَنَّ اللَّهَ هُوَ الْحَقُّ وَأَنَّهُ يُحْيِي الْمَوْتَىٰ وَأَنَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ
24፥25 በዚያ ቀን አላህ እውነተኛ ዋጋቸውን ይሞላላቸዋል፡፡ አላህም እርሱ "መኖሩ የተረጋገጠ" ሁሉን ነገር ገላጭ መኾኑን ያውቃሉ፡፡ يَوْمَئِذٍ يُوَفِّيهِمُ اللَّهُ دِينَهُمُ الْحَقَّ وَيَعْلَمُونَ أَنَّ اللَّهَ هُوَ الْحَقُّ الْمُبِينُ

"አል ሐቅ" الْحَقّ ማለት "መኖሩ ተረጋገጠ" ማለትም ሲሆን አንድ ሰው የአሏህን መኖር የሚረጋገጠው እንደ ሲይግመን ፍሮይድ ማየት፣ መስማት፣ ማሽተት፣ መቅመስ እና መዳደስ በሚባሉት አምስት የስሜት ሕዋሳት ሳይሆን በመኽሉቅ፣ በፊጥራህ፣ በዐቅል፣ በነቅል፣ በአደብ ነው። እነዚህ ማረጋገጫዎች እንመልከት፦

30/03/2025

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ወገኖቼ፣ መልካም ኢድ አል-ፈጥር:: የሰላም የጤና እና የብልፅግና ይሁንላችሁ::

Edi Mubarak! Wishing you Joy, peace, and good health this Eid-al-Fitr. May this special day bring happiness to you and your loved ones!❤️

Want your business to be the top-listed Food & Beverage Service in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address


Adiss Abeba
Addis Ababa