Value Podcast
04/04/2024
ግብር የሚከፈልበት የቤት ኪራይ ገቢ
ግብር የሚከፈልበት የኪራይ ገቢ የሚባለው በግብር ዓመቱ ግብር ከፋዩ ቤት በማከራየት ካገኘው ጠቅላላ ዓመታዊ ገቢ ላይ ለግብር ከፋዩ የተፈቀደው ጠቅላላ ወጪ ተቀናሽ ተደርጎ የሚቀረው ገቢ ላይ ነው፡፡
የተከራይ አከራዮች
• የተከራይ አከራይ በግብር ዓመቱ ያገኘው ግብር የሚከፈልበት ገቢ ነው የሚባለው የተከራይ አከራይ በግብር ዓመቱ ከተቀበለው ጠቅላላ የኪራይ ገቢ ላይ ለዋናው አከራይ የሚከፍለው ኪራይ እንዲሁም ገቢውን ለማግኘት ያወጣቸው ሌሎች ወጪዎች ከተቀነሱ በኋላ የሚቀረው ገንዘብ ነው፡፡
• ተከራይ የተከራየውን ቤት መልሶ እንዲያከራይ የሚፈቅድ የቤት ባለቤት ተከራዩ ግብሩን ሳይከፍል ቢቀር ስለእርሱ ሆኖ ግብሩን የመክፈል ኃላፊነት ይኖርበታል፡፡
Ministry of Revenues of Ethiopia /Ministry of Revenues of Ethiopia /የገቢዎች ሚኒስቴር / ሚኒስቴር /
04/04/2024
LOGO
የሰነደ ሙአለ ንዋይ ገበያ አዲስ መለያ ይፋ አደረገ።
Website (https://bit.ly/capital_site) | Facebook (https://bit.ly/capital_fb) | X (https://bit.ly/capital_X) | TikTok (https://bit.ly/Capital_tiktok) | Instagram (https://bit.ly/Capital_Insta) | Linkedin (https://bit.ly/Capital_In) | Youtube (https://bit.ly/capital_yt)
29/03/2024
ዛሬ በሚጠናቀቀው የአክሲዎን ሽያጭ Amhara Bank አማራ ባንክ በሰነደ መዋእለ ንዋይ ገበያ (Securities Exchange) ላይ ከግል ኢንቨስተሮች ከፍተኛ ባለድርሻ የሚያረገውን አክሲዎን ገዛ።
አማራ ባንክ ከፍተኛውን መዋዕለ ነዋይ በመመደብ የ 10 በመቶ የአክሲዮን ድርሻ መግዛቱን ገልጿል።
ባንኩ የሰነደ መዋዕለ ገበያን ላይ በ 90.6 ሚሊዮን ብር ከፍተኛዉን ድርሻ የገዛ የግል ኩባንያ መሆን ችሏል። ይህን ተከትሎ የአክሲዮን ግዢን የመፈፀመ አምስተኛዉ ባንክ ሆኗል።
ካፒታል ገበያን በኢትዮጵያ ለማቋቋም ድርሻ ከገዙት ባንኮች ዉስጥ እስካሁን 308.1 ሚሊዮን ብር መሰብሰብ ተችሏል ።
Via- Capital
Commercial Bank of Ethiopia የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሰሞኑ በተፈጠረው የሲስተም ችግር ሳቢያ ከ 9 ሚሊዮን ብር በላይ የወሰዱትን ወደ 567 የሚጠጉ ግለሰቦችን ማግኘት አለመቻሉን አስታወቀ
ንግድ ባንክ ባጋጠመው የሲስተም ችግር ምክንያት ከተወሰደዉ ከ 801 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ 622 ሚሊዮን ያህሉን ወደ ባንኩ ተመላሽ ማድረጉን የገለፀዉ እና ቀሪ 567 ግለሰቦች ደግሞ የወሰዱትን 9.8 ሚሊዮን ብር ማግኘት አለመቻሉን አስታዉቋል።
መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ.ም. ምሽት ላይ ከ 3 ሰዓት ጀምሮ እስከ 8: 45 ድረስ ባለዉ 25 ሺህ 761 ደንበኞች ብር 801.4 ሚሊዮን መወሰዳቸውን ገልጿል።
ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት በማሰብ በሂደቱ ዉስጥ የተሳተፉ 15 ሺህ ያህል የሂሳብ ቁጥሮችን ማግኘቱን ያስታወቀው ባንኩ 14 ግዜ ግበይት ነበራቸው ብሏል።
በዕለቱ 238 ሺህ 293 ግብይት መደረጉን እና አንድ የባንኩ ደንበኛ ከ 9 ጊዜ በላይ ግብይት መፈፀሙን የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ለሁለተኛ ጊዜ በሰጡት መግለጫ አስታዉቀዋል።
በሂደቱ ላይ 57 በመቶ ተሳታፊ የነበሩት የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች መሆናቸው ተነግሯል። አቶ አቤ ሳኖ እንደገለፁት እስከ ትላንት መጋቢት 16 ፤ 2016 ዓ.ም. ድረስ ከተወሰደዉ ገንዘብ 78 በመቶ ወይም ከ 622.9 ሚሊዮን ብር በላይ ወደ ባንኩ ተመላሽ ተደርጓል ብለዋል።
በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ዉስጥ በፍቃደኝነት ገንዘብን ተመላሽ ያላደረጉ ግለሰቦች ስማቸዉን ጨምሮ ማንነታቸውን የሚገልፅ ምስዕል ከዛሬ ጀምሮ በተለያዩ አማራጮች ይፋ እንደሚያደርግ አስታዉቋል ።
Capital
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Telephone
Address
Addis Ababa