Yared Computer &Mobile

Yared Computer &Mobile

Share

30/11/2017

የኮምፒውተራችንን ፍጥነት ለመጨመር የሚያግዙ 5 ጠቃሚ ሀሳቦች
የኮምፒውተራችንን ፍጥነት ከሚቀንሱ እና አዝጋሚ እንዲሆን ከሚያደርጉ ምክንያቶች መካካል የቆዩ ፋይሎች በኮምፒውተሩ ውስጥ ተሰግስገው መገኘት ፣ በርከት ያሉ ፕሮግራሞችን በአንድ ጊዜ ከፍቶ መጠቀም አበይቶቹ ናቸው።
ይሁንና ኮምፒውተራችን የተሻለ ፍጥነት እንዲኖረው ለማድረግ የተለያዩ አማራጮችን ብንጠቀም የተሻለ እንደሆነ ነው የሚመከረው።
1.ለኦፕሬቲንግ ሲስተም የሚረዱ አዳዲስ ሶፍትዌሮችን መጠቀም፣
የኮምፒውተርዎን ኦፕሬቲንግ ሲስተም ወቅቱ በሚጠይቀው የሶፍትዌር አይነት በመጫን ፍጥነቱን ለማስተካከል መሞከር አንዱ ዘዴ ነው።
የተለያዩ የኮምፒውተር አምራቾች ኮምፒውተራችን በተሻለ ፍጥነት እንዲያገለግለን የሚረዱትን ሶፍትዌሮች በማምረት በየጊዜው ለገበያ ስለሚያቀርቡ እነዚህን መጠቀም ይኖርብናል።
ስራ ከመጀመራችን በፊት ኮምፒውተራቸንን አጥፍቶ ማብራቱም ሌላው ፈጣኑ እና ቀላሉ አማራጭ ነው።
2.የቆዩ እና የማንፈልጋቸውን ፋይሎች በዘላቂነት ከኮምፒውተራችን ላይ ማጥፋት፣
ለረዥም ጊዜ በኮምፒውተራችን ውስጥ የተቀመጡ መረጃዎችን ወደ ሀርድ ዲስክ በማስገባት እና ብዙ ጊዜ አገልግሎት ላይ የማናውላቸውን ሶፍትዌሮችን መቀነስም ይኖርብናል።
እጅግ ከፍተኛ የምስል ጥራት ያላቸውን ምስሎች ለመጫን ረዘም ያለ ጊዜን ስለሚወስዱ እና የኮምፒውተራችን ፍጥነት አዝጋሚ እንዲሆን ስለሚያደርግ ጥንቃቄ ማድረግ አለብን።
3.የዋይ ፋይ ግንኙነታችንን ከኮምፒውተር መረጃ በርባሪዎች ዝግ ማድረግ፣
የዋይ ፋይ ግንኙነታችን ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ ለማስኬድ እያንዳንዱን አይከን ዝግ እንዲሆን የሚያደርግ ዘዴን መጠቀሙ ኮምፒውተራችንን በተሻለ ፍጥነት እንድንጠቀምበት ያግዘናል።
4.በአንድ ጊዜ በርካታ ፕሮግራሞችን አለመክፈት፣
የኮምፒውተራችን ራንደም አክሰስ ሜሞሪ(ራም) የኮምፒውተሩ የማሰላሰያ ክፍል ልንለው እንችላለን ውጥረት እንዲከሰትበት እያደረግን ነው ማለት ነው፤ ስለሆነም የተከፈቱ ነገር ግን አሁን እየተጠቀምንባቸው ያለሆነ ፕሮግራሞችን በጊዜያዊነት ማጥፋት ይኖርብናል።
5.ወቅታዊ ፀረ ቫይረስ ሶፍትዌሮችን መጫን፣
ኮምፒውተራችን አዝጋሚ እንዲሆን ከሚያደርጉት ነጥቦች መካከል ከቀዳሚዎቹ ተርታ የሚሰለፍ ነው የኮምፒውተራችን በቫይረስ መጠቃት።
ስለሆነም ቫይረሱን ከኮምፒውተሩ በማስወጣት ከከፋ አደጋ ለመጠበቅ እና በተመሳሳይ የተሻለ ፍጥነት እንዲኖረው ለማስቻል ወቅታዊ የሆኑ ፀረ ቫይረስ ሶፍትዌሮችን በየጊዜው በኮምፒውተራችን ላይ መጫን ይመከራል።

Photos 29/10/2015

come on u proud by our service

Want your business to be the top-listed Computer & Electronics Service in Adama?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address


Adama Mebrat Hayl
Adama