Ethio Intelligence

Ethio Intelligence

Share

Ethio_Intelligence 10/12/2024

ብርቱ ሰራተኛ ሁኑ!

“ሕልምና ራእይ ወደ እውነታ የሚመጣው በምትሃት አይደለም፡፡ በላብ፣ በቆራጥነትና ጠንክሮ በመስራት ነው” - Colin Powell

አንድ ቀን የምመኘውን አገኘዋለሁ” በማለት ቁጭ ብሎ የሚጠብቅ ሰው አንድ ቀን የሚመኘውን የማግኘቱ እድል እጅግ የመነመነ ነው፡፡ ምናልባት እንኳ እንዴት እንደሆነ ባልገባን ሁኔታ አንድ ቀን የተመኘውን ቢያገኝም እንኳ፣ አንድ ቀን ደግሞ ያንን እንዲሁ በምኞትና ባጋጣሚ ያገኘውን ነገር ያጣዋል፡፡ ይህ የሚሆንበት ዋነኛ ምክንያቱት ቁጭ ብለን ያገኘነውን ነገር በዚህ ቁጭ ባለው ማንነታችን መጠበቅም ሆነ ማሻሻል ስለማንችል ነው፡፡

በላብ፣ በድካምና በብዙ ትጋት የመጣ ነገር በዚያ ድካም ምክንያት ባገኘነው የባህሪ ጽንአታችን ይቀጥላል፣ ይሻሻላል እንዲሁም ያድጋል፡፡ ስለዚህም ተቀምጦ አንድ ነገር ደጁ ድረስ እስኪመጣለት የሚጠብቅ ሰው ለብዙ ክስረት ራሱን ያጋልጣል፡፡ ከሁሉ የላቀው ክስረቱ ግን ተቀምጦ “እድል” ሲጠብቅ የኖረበት ዘመን የሚያባክንበት “ጊዜ” የተሰኘውን ሊመለስ የማይችል ውብ ሃብቱን ነው፡፡

ሕልምን ማለም ለሁሉ በነጻ የተሰጠ ስጦታ ነው፡፡ የታለመውን ሕልም ግን እውን ለማድረግ መንቀሳቀስ ጥቂቶች የሚለማመዱት ልምምድ ነው፡፡ ሁሉም ነገር በህልምና በራእይ ቢጀመርም የሚቀጥለው ግን በትጋትና በጠንካራነት ነው፡፡

በሚከተሉት ነጥቦች ላይ በሚገባ አስቡና እቅድን በማውጣት ለመጻፍ ሞክሩ . . .

1. መለወጥ፣ ማደግና መሻሻል የምፈልግባቸው ነገሮች ምን ምን ናቸው?

2. ለውጡን ለማምጣት መጀመር ያለብኝ ነገሮች ምን ምን ናቸው?

3. ለውጡን ለማምጣት ማቆም ያለብኝ ነገሮች ምን ምን ናቸው?

4. መቼ የት መድረስ እፈልጋለሁ?

5. ከነገ ጀምሮ ማድረግ የምጀምራቸው ነገሮች ምን ምን ናቸው?

መልካም ምሽት ይሁንላችሁ!

https://t.me/Ethio_Intelligence

http://Youtube.com/Ethio_Intelligence

https://www.facebook.com/EthioIntelligence/

Ethio_Intelligence Life Skill and Personal Development ! You can contact me Youtube.com/Ethio_Intelligence 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ

21/10/2021

ገንዘብ ትልቅ ውሻ ይገዛል፤ ነገር ግን ጅራቱን እንዲወዛወዝ የሚያደርገው ደግነት ብቻ ነው። ደግነት መስማት የተሳናቸው ሰዎች ሊሰሙት የሚችሉትና ማየት የሚችሉበት ቋንቋ ነው ። አንድ ወዳጃችን ሲሞት በመቃብሩ ላይ አበቦችን ከማሳየት ይልቅ በሕይወት እያለ በደግነት መያዝ ይሻላል ። አንድ ሰው የደግነት ድርጊት ቢፈጽምም ሆነ ቢፈጸምለት በእሱ ላይ ጥሩ ስሜት እንዲሰማው ያደርገዋል ። ደግነት የተንፀባረቀበት ቃል ምላስን ፈጽሞ አይጎዳውም።
መልካም መሆን ለምርጦች ሁሉ✊

Want your school to be the top-listed School/college in Adama?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address


Adama