Natii

Natii

Share

06/01/2023

የልደት ስጦታ
እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን የልደት በአል አደረሰን አደረሳችሁ! ገና በመጣ ቁጥር በብዙዎቻችን ሕሊና ስጦታ ይመጣበናል በእውነትም በአለም ላይ ያሉ ውድስጦታዎች ሁሉ የተበረከቱበት አንዳንዶቹ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ የተሰጡበት ልዩ የስጦታ ቀንም ነው!
እግዚአብሔር አብ አንድያ ልጁን ለአለም የሰጠበት
እግዚአብሔር ወልድ እራሱን ለአለም የሰጠበት
እመቤታችን ልጇን የሰጠችበት
እነዚህ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ግዜ የተሰጡ ሲሆን
ከሰብአ ሰገልም ያለው ወርቅ መካከለኛ ያለው እጣን ምንም የሌለው ከርቤ የሰጡበት
በቁስ የሚሰጥ የሌላቸው እረኞች ምስጋና የሰጡበት
መላእክት የተለመደውን ምስጋና የሰጡበት
እንስሳት እስትናፋሳቸውን የገበሩበት
ሰማይ ከምድር ፣ ሰው ከእግዚአብሔር ፣ ነፍስ ከስጋ፣ ሰው ከመላእክት የታረቀበት ድንቅ የስጦታ ቀን።
ይህን የስጦታ ቀን ለራስህ ራስህን ስጠው የሚገባህን እንድትኖር ለሌሎች እንድትተርፍ ለወላጆችህ ተሰጥተሃል ለራስህ ተሰጥ እና ለሌሎች ትረፍ!!!
መልካም የመስጠት ቀን!

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Adama?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address


Adama