Useful Info
02/07/2022
በክሪፕቶከረንሲ 4 ቢሊዮን ዶላር ያጭበረበችው ግለሰብ የኤፍ.ቢ.አይ ዋነኛ ተፈላጊዎች ዝርዝር ውስጥ ተካተተች
**************************
በክሪፕቶከረንሲ 4 ቢሊዮን ዶላር ያጭበረበችው ግለሰብ በአሜሪካ የፌዴራል ወንጀል ምርመራ ኤጀንሲ /ኤፍ.ቢ.አይ/ 10 ዋና ዋና ተፈላጊዎች ዝርዝር ውስጥ መካተቷን የሀገሪቱ ባለሥልጣናት ገለጹ።
“የክሪፕቶ ንግሥቷ” በሚል ቅፅል ስም የምትታወቀው ሩጃ ኢግናቶቫ የተባለች ግለሰብ፣ ‘OneCoin’ /ዋንኮይን/ በተባለ ሐሰተኛ የዲጂታል ገንዘብ ከተለያዩ ሰዎች ከ4 ቢሊዮን ዶላር በላይ አጭበርብራ መሰወሯ ነው የተገለጸው።
በኤፍ.ቢ.አይ በእጅጉ ተፈላጊ ከሆኑ 10 ዋና ዋና ግለሰቦች ውስጥ ብቸኛዋ ሴት የሆነችው ኢግናቶቫ፣ የፈፀመችው የማጭበርበር ወንጀል እጅግ ትልቁ እንደሆነም ተነግሯል።
ግለሰቧ ወንጀሉን ስትፈፅም መቆየቷን የገለጸው ኤፍ.ቢ.አይ፣ ከ2017 (እ.አ.አ) ወዲህ ደብዛዋ አልተገኘም ብሏል።
እንደ ቢቢሲ ዘገባ፣ ግለሰቧ ማንነቷን ቀይራ ሊሆን ይችላል የሚል ጥርጣሬ በአሜሪካ ባለሥልጣናት ዘንድ ተፈጥሯል።
በ2019 የኤሌክትሮኒክስ ማጭበርበርን ጨምሮ በስምንት የተለያዩ የወንጀል ጉዳዮች ክስ ቀርቦባታል።
ዐቃቤ ሕጎች እንዳሉት ሩጃ ኢግናቶቫ የምትመራው ኩባንያ በዋናነት ‘ዋንኮይን’ን እንደ ፒራሚድ በመጠቀም ሌሎች ሰዎች ዋጋ የሌለውን ክሪፕቶከረንሲ እንዲገዙ እንዲያሳምኑላቸው ለአባላቱ ኮሚሽን ይከፍላል።
በአሜሪካ ማንሃታን ግዛት ከፍተኛ የፌዴራል ዐቃቤ ሕግ የሆኑት ዳሚያን ዊሊያምስ እንደገለጹት፣ ግለሰቧ የማጭበርበር ዕቅዷን የተጠቀመችው ስለክሪፕቶከረንሲ ብዙ ሲወራለት በነበረበት ወቅት ነው።
‘ዋንኮይን’ የተባለው የዲጂታል ገንዘብ በታሪክ ውስጥ ትልቁ የማጭበርበሪያ ዘዴ እንደሆነም ዐቃቤ ሕጉ መናገራቸውን ዘ ኢንዲፔንደንት ዘግቧል።
የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/c/EBCworld/
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/EBCNEWSNOW
የተመረጡ አጫጭር የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የቲክቶክ አካውንታችንን ይከተሉ
https://www.tiktok.com/
27/06/2022
Haga clic aquí para reclamar su Entrada Patrocinada.
Categoría
Contacto la empresa
Página web
Dirección
Madrid