Fact Check Ethiopia

Fact Check Ethiopia

Share

Photos from Fact Check Ethiopia's post 04/05/2026

2010 E.C/ 2018G.C

Fact Check Ethiopia

ከታች የተያያዘውን ምስል በማጋራት አሁናዊ መረጃ ለማስመሰል የተሞከረው ሀሰተኛ መረጃን አጣርተናል።

ባደረገው ማጣራት Mohamed Oumer በተሰኘና ከ56 ሺ በላይ ተከታይ ባለው ግለሰብ ከዚህ ስር በቀረበው ሊንክ👇🏽

https://www.facebook.com/share/1SBBr3Un9g/?mibextid=wwXIfr

ከስር የተያያዘውን ስክሪን ሹት በማያያዝ በሶማሊኛ ቋንቋ በሶማሊ ክልል ሊደረግ የታሰበ መድረክ እንዳለና ለመገናኛ ብዙሀን ጥሪ እንደተደረገ ይገልፃል።

ነገር ግን በተደረገው ማጣራት ምስሉ ከ8 አመት በፊት እንደ አውሮፓውያን ዘመን አቆጣጠር አቆጣጠር አፕሪል 2018 የሶማሊ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ (Somali Regional State, Communication Bureau) የላከው መሆኑን መገንዘብ ተችሏል።

በኢትዮጵያ አቆጣጠር 2010 ወይም በፈረንጆቹ 2018 በኢትዮጵያ ታሪክ የመንግስት ለውጥ የተደረገበት መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ፣ ከ8 አመት በፊት በአውሮፓውያን አቆጣጠር አፕሪል 2018 የተጋራን መልእክት በአሳሳች መንገድ አሁናዊና በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር 2018 በማስመሰል የተሰራጨው መረጃ ፍፁም ሀሰተኛና ሆን ተብሎ የተጋራ መሆኑን ለማረጋገጥ ተችሏል።

ባደረገችው ጥልቅ ማጣራት በ2010E.C/ 2018G.C በሀገሪቱና በክልሉ የነበረውን ለውጥ ተከትሎ በጅግጅጋ የነበረውን ስነስርአት መገናኛ ብዙሀን እንዲዘግቡ የወቅቱ አስተዳደርና ኮሙኒኬሽን ቢሮ ለመገናኛ ብዙሀን ያጋሩትንና በወቅቱ ተጋርቶ የነበረ ምስልን እንደ አሁን (2018E.C/2026G.C) በማስመሰል የተጋራው መረጃ ፍፁም ሀሰተኛ ነው።

Want your business to be the top-listed Media Company in Toronto?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address


Toronto, ON
V5A2Z6