Calgary Christian Youth Association - CCYA
የማቴዎስ ወንጌል 6:6 አንተ ግን ስትጸልይ፥ ወደ እልፍኝህ ግባ መዝጊያህንም ዘግተህ በስውር ላለው አባትህ ጸልይ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል።
“እልፍኝህ” የሚለው ቃል በቀላሉ በዓለም ላይ በሩን የምንዘጋበት እና መስኮቶቹን ወደ ሰማይ መክፈት የምንችልበት ቦታችን ማለት ነው::
የጌታ የኢየሱስን ሕይወት በምናጠናበት ጊዜ ለፀሎት ብቻውን ለመሆን እንደሚፈልግ ለማወቅ እንችላለን:: አንዳንድ ጊዜ ወደ ተራራ ይወጣል፣ አንዳንድ ጊዜ ደሞ ወደ ምድረበዳ ይሔዳል፣ አንዳንድ ጊዜም እንዲሁ ወደ የአትክልት ስፍራ ይሔዳል:: ይህም ማለት ለኔ ሲገባኝ ጥሩ የፀሎት ቦታ ማለት ሚስጥራዊ (የተለየ) ቦታ ነው ማለት ነው::
ሚስጥራዊ (የተለየ) ቦታ ስል ሌላ ማንም የማያውቀው ቦታ ማለቴ ሳይሆን: እኔ ብቻ ከጌታ ጋር የምገናኝበት (የምኖርበት)ቦታ ማለቴ ነው:: ሌላው ደግሞ ጌታ ለምን “አንተ ግን ስትጸልይ፥ ወደ እልፍኝህ ግባ” አለ የሚለው ነው? አሁንም ይሔ ለኔ ሲረዳኝ: ብቻህን ስትሆን ያለው ማንነትህ (የምትሆነው አኳኋንህ) ያ ያንተ እውነተኛ ማንነትህ ስለሆነ: የፀሎት ህይወትህ ልኬቱ (መመዘኛው) በአደባባይ (በጉባኤዎች መካከል) በምትፀልየው ፀሎትና ሁኔታ ላይ የተመሰረተ ሳይሆን: በስውር ብቻህን ስትሆን በምትፀልየው ፀሎትና ሁኔታ ላይ ነው:: ስለዚህ “ያን ግዜ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል” ይላል። ከጌታ ጋር ሚስጥራዊ ቦታ ያላችሁ: ታድላችሁ::
03/19/2019
I Could Sing Of Your Love Forever - Steffany Gretzinger | Bethel Music Worship Watch as Steffany Gretzinger spontaneously sings "I Could Sing Of Your Love Forever" live at Bethel Church Join our YouTube Community: http://bit.ly/BMsubscr...
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Calgary, AB