Tibeb Media.com
22/02/2026
የብልፅግና ቁስ ተኮር ፖሊሲ እና የኢዜማ ሰው ተኮር ፖሊሲ ።
⚖️⚖️⚖️⚖️⚖️
ብልፅግና ባለፉት አመታት የትኩረት አቅጣጫው በሙሉ በሰው ልጅ ህይወት ላይ መሰረታዊ ለውጥ በማያመጡ የገፅታ ግምባታ ላይ ነው ።
ከህዝብ በአስገዳጅነት የተሰበሰበው ቢሊዮን ብሮች ፈሰሰ የተደረጉ የአስፓልት ዳር የቴራዞ ንጣፍ እና መብራት ላይ ነው ። ስራው በራሱ በመጥፎ ባይገለፅም በሀገሪቱ ዜጎች የኑሮ ሁኔታ ለውጥ ባለማምጣቱ እንዲሁም ከህዝብ የተሰበሰበው ገንዘብ ብሎም የሀገሪቱ ገንዘብ አብዛኛው ሪተርን በሌላቸው ወይም ገቢ በማያስገኙ ብሎም ምርታቸው ወደ ገበያ ገብቶ ገበያ የማያረጋጋ ፕሮጀክቶች በመሆናቸው የተፈጠረው የኢኮኖሚ መዛባት ፤ በIMF ሪፖርት መሰረት ከድህነት ወለል በታቸው የሚኖረውን የህዝብ መጠን ከ32 በመቶ ወደ 43 በመቶ ከፍ እንዲል አድርጎታል ። ይህ የህዝብ መጠን ያለ እርዳታ መኖር የማይችለው ነው ።
አብዛኛው መካከለኛ ገቢ የነበረው ህዝብ ወደ ደህንነት ፤ ብዙ ከፍተኛ ገቢ የነበራቸው በደግሞ
ወደ መካከለኛ ገቢ አሽቆልቁሏል ።
ኢዜማ የሚያምነው የማህበረሰቡን የኑሮደረጃ በመለወጥ አከባቢን ከተማን ገጥርን መለወጥ ነው ። የኢዜማ የኢኮኖሚ ፖሊሲ የትኩረት አቅጣጫው የዜጎችን የገቢ መጠን ወይም (Per Capital Income) ማሳደግ ነው ።
በአብዛኛው በጀት ፈሰስ የሚደረግባቸው ቀጠይነት ያለው ገቢ የሚያስገኙት ፤ ምርታቸው ተመርቶ በተመጣጣኝ ዋጋ ለገበያ የሚቀርቡ ።
በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ወደ ሀገር ወስጥ የሚገቡ እቃዎችን የሚተኩ የሀገር ወስጥ አምራች ዘርፎች ላይ፤ ብሎም በአለም አቀፍ ደረጃ ተፈላጊ ምርቶችን በመለየት በማምረት ለሀገሪቱ የውጭ ምንዛሬ የሚያስገኙ ፤ እንዲሁም ለበርካታ ዜጎች ተመጣጣኝ ገቢ የሚያገኙበት የስራ እድል የሚፈጥሩ ዘርፎች ላይ ነው ።
ገበሬው በቂ የሆነ የግብርና ግብአት በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኝ ፤ ተማሪዎች ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት በነፃ እንዲያገኙ ፤
ደረጃውን የጠበቀ የህክምና አገልግሎት ለሁሉም ዜጎች ለማዳረስ ነው ።
በከተማ ለሚኖረው ህዝብ የመኖሪያ ቤት ንፁህ የመጠጥ ወሃ ፤ የኤሌክትሪክ አገልግሎት እና የቴሌኮም አገልግሎት አቅሙን ባገናዘበ ዋጋ ማቅረብ ነው ።
በአጠቃላይ ዜጎቻችን በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል ተዟዙረው መስራት፤መኖር ፤ ሀብት ማፍራት የሚችሉበት አስተማማኝ የዜጋ ተኮር ፓሊሲ ነው የምንከተለው ።
ከተማዋ በመብራት ተሽቆጥቁጣ ህዝባችን እቤት መብራት ሲበራ ሲጠፋ የተሰቃየበት ፥ ከተማዋ ፏውንቴን በፏውንቴን ሆና ዜጎች በጄሪካን የሚሸከሙት የብልፅግና ውበት ተኮር ፖሊስ እንዲያበቃ ኢዜማን መምረጥ ዋነኛው መፍትሔ ነው ።
ሚዛንን ይምረጡ⚖️⚖️ ✅
via Journalist Abdlwehab Bilall
Click here to claim your Sponsored Listing.