Wollo Addis
17/07/2026
''የዝምታችን እና የመከፋፈላችን ዋጋ ለመንግስት እድል ሰቶታል " መብቱንኳ የማይጠይቅ ትውልድ በዝቷል።
አንገታችንን ያስደፋው የራሳችን ዝምታ እና የጎጥ ክፍፍል ዛሬ በሀገራችን የኑሮ ውድነቱ ሰማይ ነክቶ፣ የብዙኃኑ ዜጋ ኑሮ ከዕለት ወደ ዕለት እየከበደ የመጣው በመንግሥት ጥንካሬ ወይም መለስተኛ ስህተት ብቻ አይደለም፤ በእኛም ፍርሃት፣ ዝምታ እና እርስ በርስ መከፋፈል ጭምር እንጂ።
''መብቱን የማያውቅ፣ መብቱን የማይጠይቅ፣ ነገር ግን የተጠየቀውን ሁሉ ያለ ምንም ጥያቄ ለመክፈል የሚሽቀዳደም ትውልድ በመሆናችን ዛሬ የችግሩ ሰለባ ሆነናል።'' ሌሎች የአፍሪካ ሀገራትን ብናይ፣ በአንድ ዕቃ ወይም በአገልግሎት ላይ የ1 ብር ወይም ሳንቲሞች ጭማሪ ሲደረግ፣ ሕዝቡ በአንድነት ወጥቶ ድምጹን ያሰማል፤ መብቱን ያስከብራል።
''እኛ ጋ ግን ጭማሪው እየተደራረበ የዕለት ጉርስ ሲናፍቅ እንኳ "ለምን?" ብሎ የሚጠይቅ ጠፋ።''
ለዚህ ትልቁ ማነቆ ደግሞ በብሔር፣ በቋንቋ እና በእምነት ተቧድነን አንድነታችንን ማጣታችን ነው።
አንዱ ሲራብ ሌላው አይሰማውም።
አንዱ በኑሮ ውድነት ሲደቅቅ፣ ሌላው በብሔር ፖለቲካ ተጠምዶ ይመለከታል። የጋራ በሆነው የኑሮ ሸክም ላይ እንኳ አንድ ሆነን መቆም አቅቶናል።
በመሆኑም፣ መንግሥትን ብቻ እያማረሩ መኖር መፍትሔ አይሆንም።
''ራሳችንን መውቀስ፣ መብታችንን በሕጋዊ መንገድ በጋራ መጠየቅ እና ከጠባብ የቡድን ስሜት ወጥተን ለአጠቃላይ ሕዝባዊ ጥቅማችን መቆም ካልቻልን፣ የኑሮ ውድነቱ በጣም የከፋ ደረጃ መድረሱ አይቀሬ ነው።
ሀሳብዎን ያካፍሉን?
ሰላም ለኢትዮጲያ
ሰላም ለህዝባችን
ወሎ አዲስ የህዝብ አድማስ
ኢትዮጵያዊን ፉከራ ብቻ ነው የምናውቀው'' መጋቤ ሃዲስ እሸቱ አለማየሁ ይናገራሉ
12/07/2026
''ሕወሓት ባዶ ከሆነ በየቀኑ እሱን እያነሱ መቃዠት ምን አመጣው'' አማኑኤል አሰፋ ......
የሕወሓት ምክትል ሊቀመንበር አቶ አማኑኤል አሰፋ ባሰፈሩት መልዕክት የኢትዮጵያ መንግሥት በድርጅቱ ላይ እያካሄደ ነው ያሉትን የሚዲያና የፖለቲካ ዘመቻ በጽኑ አውግዘዋል።
አቶ አማኑኤል አሰፋ መንግሥትና የተለያዩ አካላት በየመድረኩ ስለ ህወሓት መዳከም የሚሰጡትን መግለጫዎች በመጥቀስ ድርጅቱ ማኅበራዊ መሠረት የሌለውና የፈረሰ አካል ነው ተብሎ የሚነገር ከሆነ በየዕለቱ ስሙን በተለያዩ መድረኮች ማንሳት እንደማያስፈልግ በመልዕክታቸው አስፍረዋል።
አክለውም አቶ አማኑኤል አሰፋ "ህወሓት ከሌለ ማሕበራዊ መሰረት ከሌለውና ቀፎ ከሆነ ታድያ በፓርላማ፣ በየስብሰባው፣ በየአደባባዩና በየስልጠናው በየቀኑ መጥተው ህወሓትን እያነሱ መቃዠት ምን አመጣው ሲሉ ጥያቄ አንስተዋል።
አቶ አማኑኤል እንዳሉት ከሆነ ድርጅታቸው አሁንም ያለው ተሰሚነትና ክብደት ከፍተኛ በመሆኑ መንግሥታዊ ተቋማት የየዕለቱ የትኩረት አጀንዳ እንዳደረጉት ለማሳየትም "በሞተ አካል ላይ ማንም ድንጋይ አይወረውርም" (No one throws a stone against a dead body) የሚለውን አባባል በምሳሌነት ጠቅሰዋል።
በአቶ አማኑኤል አሰፋ ሀሳብ እርሰዎ ምን ይላሉ?
ሰላም ለኢትዮጲያ
ሰላም ለህዝባችን
ወሎ አዲስ የህዝብ አድማስ
Stop civil war in Ethiopia