MSS Entertainment
11/22/2023
ክፍል 3
"ሂጅ ከዚህ!"
እነዚህ ሁለት ቃላት ብቻ እማማ ሎላሼን የጨው ሃውልት ለማድረግ በቂ ነበሩ።
ልክ ቀልባቸው ሲመለስ፣መጮህ ጀመሩ! "እርዱን! እርዱን! ልጄን እየገደለው ነው!"
ወዲያው፣የአስናቀች ኩባንያ ዋርድያዎች መጥተው ከበቧቸው።
"ምን ተፈጠረ፣እማማ ሎላሼ?" አለ የዋርድያዎች አለቃ ወይዘሮዋን በማስታወሱ ሄዶ እየከለላቸው።
"ቶማስዬ! እስኪ ይኼን ደቃቃ ሰው አንዴ እየው!" አሉ እማማ ሎላሼ ታምሩ ላይ እየጮኹ። ልክ የኾነ ነገር ለማድረግ ሲዘጋጁ፣ አንድ ድምፅ ከኋላቸው ተሰማ!
"ምን የምታደርጉ ይመስላችኋል?"
እጅግ አስደማሚ ውበት ያላት ፣የለበሰችው ረጅሙ ወርቃማ ቀሚስ የቅዱስ ሚካኤል እህት አስመስሏታል። በባዲ ጋርዶቿ መታጀቧ ደሞ ለፀብ ሳይሆን ልንግስ የወጣች አማላክትን እንድትወክል አድርጓታል። ከንፈሯውን የተቀባችው ቀይ ሊፕስትክ ከንፈሯን ጉረሱኝ ጉረሱኝ ያስብላል። የሰውነት ቅርጿ ከአሊባባ በሚገዙ ቁሳቁሶች ያልተሰራ መኾኑን ያሳብቃል። እያንዳንዷን እንቅስቃሴዎቿን እየተከተሉ ከሰማይ ወፎች ይዘምሩላታል፣የሚያዩዋት ወንዶች ልብ ተሰቅሎ አልወርድ ይላል። ሳር ቅጠሉ ካልሰግንልሽ ይላል። ከብልፅግና ገበታ ለሀገር ሪዞርቶችና ፓርኮች የበለጠ ውብ አማላይ ናት። ባዲ ጋርዶች ዓይናቸውን ተክለው መንቀል ተስኗቸዋል ።
"አቶ ታምሩ ደህና ኖት?
ሴትዮዋ ያን ሁሉ ያፈጠጠባትን ወፈ ሰማይ ዓይኖችን ንቃቸው ቀጥታ ወደ ታምሩ አመራች።
"ማን ልበል ?" አለ ታምሩ ግራ ገብቶት። ማን እንደሆነች ለማጣራት አተኩሮ እያያት። ንዴቱን አቀዝቅዞታል።
"ስላገኘሁክ ደስ ብሎኛል፣ ጫልቱ ጴጥሮስ እባላለው። አቶ ቶንቦሌ ነው የላከኝ። አለች ያን እንደ ታላቁ ሩጫ ሯጮች ግጥም ያለውን በረዶ ጥርስ እየበረገደችለት።
" ጫልቱ ጴጥሮስ? " የዱንጉዛ ቤተሰብ ወራሽ?
"የፈጣሪ ያለ?!" ምን ልታደርግ መጣች?"
ጫልቱ ጴጥሮስ እጅግ ዝነኛ ሰው ናት።ከተማው በሙሉ የሚያውቃት። ቆንጆ ፣ተፅእና ፈጣሪና ብልጣብልጥ ነገር ናት።ገና በ22 ዓመቷ የዱንጉዛ ኮባንያን በእጇ አስገብታለች።የራሷን ግዙፍ ድርጅት ለማቋቋም አምስት ዓመት ብቻ ነው የፈጀባት።
"አሃ ፣አንቺ ነሻ።" ታምሩ...ራሱን ነቀነቀ።
ስለ ጫልቱ ከዚህ በፊት ሰምቷል። ከአቶ ቶንቦሌ ጋር ግኑኝነት እንዳላቸው ግን አያውቅም ነበር።
"አቶ ታምሩ ፣እባክዎን መኪና ውስጥ ይጠብቁኝ።ይኼን ጉዳይ እኔ አበርደዋለው"
ብላ ጣቶቿን አንቋቋቻቸው። እሷን ተከትለው ባዲ ጋርዶቿው ወደፊት ተጠጉ። የድርጅቱ ዋርድያዎች ወደኃላ አፈገፈጉ።
"ከርስዎ በኃላ፣አቶ ታምሩ" ብላ ማንም ሱሪ የታጠቀ እጁን ሊያነሳ እንዳልሞከረ ስታይ ጫልቱ ፈገግ እያለች ታምሩን ወደ መኪናው መራችው። ምንም ሳይተነፍስ ፣ታምሩ የተሰባበሩ ከአዞ ጥርስ የተሰሩ ፣የተሰባበሩ ሃብሎችን ከመሬት ሰብስቦ ጫልቱን ተከትላት። የሚያቆመው እኔ ነኝ ያለ ሰው ጠፋ።
"ምንድነው ችግሩ? እንዴ? እንዲሁ በነፃ በቃ ለቀቃቹት ማለት ነው?" አያሉ ጮኹ፣እማማ ሎላሼ እየሆነ ያለውን ነገር በጥሞና ካስተዋሉ በኃላ።
አሁንም አንድም ሰው ጫልቱ ላይ ጣት ጠቋሚ እንኳን ጠፋ!
የባሰ እርስ በርስ ተያይተው ላለማውራት ሁላ አፋቸውን ያዙ-ዋርድያዎቹ።
"ምን ተፈጠረ?"
አሉ ሳራና ስናፍቅሽ ግርግሩን አይተው።
"ሳርዬ፣መጣሽልን! እሴይ! እይው እስኪ ወንድምሽ እንዴት እንደተቀጠቀጠ" አሉ እማማ ሎላሼ ልጃቸውን ሲያዩ ማልቀስ ጀምረው። ልክ እርሳቸው እንደተደበደቡ ለማስመስል እየቃጣቸው።
"ምን ተፈጠረ? ማነው ይኼን ያደረገው?" አለች ሳራ አስፓልት ላይ የተገለበጠ የተረኞች ሪቮ የመሰለውን የወንድሟን ቁስል እያየች። ስሜቷም ተረበሸ።
"ያ ታምሩ ነዋ!" አሉ እማማ ሎላሼ ፣እንባቸው እየፈሰሰ።
"አሁን እዚሁ አገኘነው። ጳውሎስዬ ለእምነቱ ያደረው ልጄ ፣እሱ መሬት ላይ የጣለውን አንገት ሃብል አንስቶ ሊሰጠው ሲል ወንድምሽን ሌባ፣ከኔ ሰርቀህ ነው ብሎት እንደ አሰላው የአህያ ጭንቅላት ቅጥቅጥ አደረገው ። በጐ ለሰራ ይኼ ነው ምላሹ?"
አሉ የበለጠ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው እያለቀሱ።
"ታምሩ" አለች ሳራ በንቀት።
ለሦስት ዓመታት ያህል በዘለቀው ትዳራቸው ማንነቱን ጠንቅቃ ታውቃለች። እንዲሁ ያለ ምክንያት ቱግ የማይል፣እንደብልፅግናው መንግሥት ህገ ለማስከበር የማይቸኩል፣ ነገሮችን በሰከነ አእምሮ የሚመለከት የተረጋጋ ሰው ነው። ያለ ምክንያት ከሜዳ ተነስቶ የሰው ልጅ ላይ እጁን አያነሳም።
"እስኪ ወንድምሽን ተመልከችው።የሚታየው እውነት አይበቃሽም? ካላመንሽን፣ እነዚህን ዘበኞች ጠይቅያቸው።ሁሉንም የኾነውን አይተዋል።" አሉ እማማ ሎላሼ ዋርድያዎችን በዓይናቸው እየቃኙ።
"እትዬ ሳራ፣እናትዎ ልክ ናቸው" አለ የዋርድያዎቹ ሃለቃ ሃላፊነቱን በሚገባ እያስተዋለ።
"ያለውን ሰማሽ? እኔኮ በባዶ ሰው አልወነጅልም። እንዲሁም እሱ አሁን ሌላ ሴት ሁሉ ይዟል"
ይኼን ስትሰማ ሳራ የበለጠ አዘነች።የእውነት ታምሩ እንዲህ አይነት ነገር አደረገ?ምን አልባት ስለ ፍቺው ተቆጥቶ በወንድሜ በኩል እየተበቀለኝ ይኾናል። ይህ እውነት ከኾነ፣አልተረዳሁትም ማለት ነው። አለች ለራሷ።
በሁነታዎች መሃል...."እየመጡ ነው፣ እየመጡ ነው..."የሚለው የአረጋኻኝ ወራሽ አዲሱ ዜማ ስፍራውን ያዘ።
ይቀጥላል
©ኢንጆይ ሪድንግ
© Tarekegn S Hadero
🖊 ኾላ
Click here to claim your Sponsored Listing.