Blue Board
ኤርምያስ ምዕራፍ40፥ ከቁጥር 35 -38
አማራ ባንክ!
ፕሮጀክቱ 2017/18 GC ከተፀነሰበት ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ ውስጣዊና ውጫዊ ጫና ተቋቁሞ የሚገኝ ጠንካራና ጀማሪ ተቋም አማራ ባንክ ነው።
ፕሮጀክቱ የተጀመረውና ዕውን የሆነው በተቋም ግንባታ ልምድ፥ የትምህርት ዝግጅት እና ቅንነቱ ባላቸው፥ በሚዲያ የማይታወቁ ሃቀኛ ሙሁራን እና በ190ሽ ባለአክሲዮኖች ቁርጠኛነት ነው።
በተቃራኒው፦
1) ከፕሮጀክቱ ወቅት ጀምሮ በሚዲያ ሱስ የሰከሩ፥ የሙያ ስነምግባርና የቢዝነስ አቅል (Business Acumen) የሌላቸው አባላት ባንኩ ሲመሰረትም እንቅፋት ሆነው የቆዩ ግለሰቦች በአይነትና በፍላጎት በርካቶች ናቸው።
እነዚያ የፕሮጀክቱን እንቅስቃሴ እየተከታተሉ፥ በየፌቡ ገፁ ሲያሰጡ፥ የቆዩ ዛሬም እራሳቸውን የባንኩ ፈጣሪና ወላጅ አባት እንደሆኑ ቆጥረው መስዋዕትነት የከፈሉ የፕሮጀክቱን ሃላፊዎች፥ የቴክኒክ አባላት እና የ190ሽ ባለድርሻ አባላት ሚና ማሳነስ ተገቢ አይደለምና ከድርጊታችሁ ታቀቡ በሏቸው።
2) በጎጥና ጥቅም ሰንሰለት አንገታችሁ የተሳሰረ ግለሰቦች ዛሬም "አማራ ባንክ ፈረሰ" ብላችሁ "ቂቤ ጠጣን" የምትሉ፥ የህልም ቂቤ ጠጥታችሁ ይሆናል እንጅ፥ በዕውን አባ አልፈረሰም፤ ይልቁንስ ለባንኩ ስኬት ያላችሁን አሳፋሪ ግላዊ ስሜት(ego) ያሳያልና፥ ከዚህ ስንኩል አስተሳሰባችሁ በመታቀብ ለተቋማት ስኬት የሚሆን የዝምታ አስተዋፅኦ ብታበረክቱ የተሻለ ነው።
አስተዳደራዊ ዕርምቶች፦
3) አማራ ባንክ እንደ ተቋም፥
ተልዕኮ ተቀብለው የባንኩን የዕለት ከዕለት እንቅስቃሴ ሚስጥርና ሰነድ በሚያባክኑ (ነባርና የበፊት ሰራተኞች)፥ ክትትል በማድረግ አስተዳደራዊ ዕርምት ሊያደርግ ይገባል።
4)ባንኩን የራሳቸው አድርገው እንዲጠብቁት፥ የተመሰረተበትን አላማ፥ተልዕኮና ራዕይ ከግብ እንዲያደርስ፥ ሰራተኞችን የተለያዩ ማበረታቻ ፕሮግራሞችን በመዘርጋት ማነቃቃት ተገቢ እንደሆነ አምናለሁ።
በቅርቡ የተጀመረው የደመወዝ ጭማሪ በተመለከተ የተደረገው ውይይት ተፈፃሚ እንደሚሆን እምነቴ ነው።
ባለአክሲዮኖች፥
አማራ ባንክ በታሪክ ሪከርድ የሰበረ፥ ከፍተኛ ቁጥር የተሳተፈበት የባለድርሻ አካላት ተቋም እንደመሆኑ መጠን፥ ለበለጠ ስኬት የኛ የባለአክስዮኖች ብርቱ ፅናትና ትግስት ወሳኝ መሆኑን አውቀን ባንካችንን እንጠበቅ ።
ከአክብሮት ጋር!
Click here to claim your Sponsored Listing.
Contact the public figure
Telephone
Website
Address
Dallas, TX
Opening Hours
| Monday | 8am - 6pm |
| Tuesday | 9am - 5pm |
| Wednesday | 8am - 6pm |
| Thursday | 8am - 6pm |
| Friday | 8am - 6pm |
| Saturday | 8am - 6pm |
| Sunday | 9am - 1pm |