Int. Volunteering group

Int. Volunteering group

Share

11/05/2026

ትርጉም ወደ አማርኛ
የህወሓት ሳምንታዊ መልዕክት
የህዝባችን መንግስት ለድሉ ይዋጋ!
ወደ 2.8 ሚሊዮን ሕዝብ ተወካይ የሆነውና የትግራይ ሕዝብ ውክልና ያለው የትግራይ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ከሚያዚያ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ይፋዊ ሥራውን ጀምሯል። የምክር ቤቱ የመጀመሪያ ጉባኤ ተካሂዶ ፕሬዝዳንት፣ የምክር ቤት ሰብሳቢ እና ምክትል ሰብሳቢ ተመርጠዋል፤ የተለያዩ ውሳኔዎች ተላልፈው ሞሽን ፀድቆ በድል ተጠናቋል። የትግራይ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ከፕሪቶሪያ ስምምነት ተከትሎ ለሰላም ሲል ታግዶ ቆይቷል። የብልጽግና ስርዓት ፕሪቶሪያ ስምምነትን ሙሉ በሙሉ ስለናዳው ታግዶ የቆየው የትግራይ ሕዝብ ምክር ቤት ወደ ሥራው መመለስ ግዴታ ስለሆነ ይፋዊ በሆነ መንገድ ወደ ሥራው ተመልሷል።
የትግራይ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት እንደ ሌሎቹ የትግራይ ሕዝብ ተቋማት ሁሉ ህልውናው እንዲቋረጥና እንዲፈርስ ከውስጥም ከውጭም በተቀናጀ ሁኔታ ዘመቻ ሲካሄድበት ቆይቷል። አሁን በጠላት ጎራ ተሰልፎ የሚገኘው ሀገራዊ ክህደት የፈፀመው ቡድን ምክር ቤቱን ለማፍረስ ያልቀደደ ድንጋይ የለም። ከዚህ በተጨማሪ የትግራይን አቅም ለበተን የጠላትን ጎን ይዞ የትግራይ ሕዝብ በፕሪቶሪያ ስምምነት መሰረት፤ "ሉዓላዊነቴ ይመለስ፣ ሞትና ስቃይ ይቁም፣ ወደ መኖሪያዬ ጉዞ ይቻልልኝ፣ የጅምላ ጭፍጨፋ ተጠያቂነት ይረጋገጥ" ሲል ጦርነት ፈላጊ የሚለውን መሰየሚያ እየለጠፈ ዝምታ እንዲጠብቅ ሲያደርገው ቆይቷል። ይህም ትግራይ ሕዝብን እንደ ሕዝብ ለማጥፋት በዕቅድ እየሰራ ላለው የብልጽግና ስርዓት ምቹ ሁኔታ የፈጠረ ሲሆን የትግራይ ሕዝብ ሁኔታ ከሕሙም ወደ ሕሙም ወደ ከፋ እያሽቆለቆለ እንዲሄድ ምክንያት ሆኖ ቆይቷል።
ስድስተኛ ዘመን ስድስተኛ መደበኛ ጉባኤ የትግራይ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤትን ለማስቆም ያስችሉናል የተባሉ ሁሉም መንገዶች ከውስጥም ከውጭም በተቀናጀ ሁኔታ ተሞክረዋል። ሕዝባችንንና የምክር ቤት አባላትን ለማሸበር ተኩስ ተከፈተ፤ የብልጽግና ስርዓት ድሮኖች በመቀሌ ሰማይ ላይ ሲዞሩ ቆዩ፤ ጉባኤው በሚካሄድበት ሰዓት ደግሞ የጦር አይሮፕላን ልኮ ለማስተጓጎል ሞከረ። ሆኖም ግን የምክር ቤቱ አባላትም ሆኑ አመራሩ መስዋዕትነት ቢጠይቅ እንኳ ለትግራይ ሕዝብ የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት የሚከፈል መስዋዕትነት ነው ብለው ሊወስኑ ያቀዷቸውን አጀንዳዎች ተወያይተው ጉባኤያቸውን በድል አጠናቀቁ።
የትግራይ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ፈፃሚ አካሉን ዘርግቶ እየሰራ እንዲቆይ ምክር ቤቱ በሰጠው ኃላፊነት መሰረትም የካቢኔ የመጀመሪያ ስብሰባ አካሂዶ ይፋዊ ሥራውን ጀምሯል። የትግራይ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት መመለሱ ለትግራይ ሕዝብ የትግል መድረክ ይሆናል። ትግራይ ስርዓት ያለው ያለምክር ቤት ቁመና ባለው መንግስት እንድትተዳደር፣ ፈፃሚ አካሉ ላይ ቀጣይ ክትትልና ተጠያቂነት እንዲሰፍን የሚያደርግ ነው። ዋናው ደግሞ የትግራይ አቅሞችን በማደራጀት የትግራይ ሕዝብ ሀገራዊ ተቋማት እንደ ሕዝብ ተፈናቅሎ ካለው አደጋ ጋር የሚጣጣም አቋምና አደረጃጀት ፈጥረው እንዲሰሩ የሚያስችል ነው። በአጠቃላይ ደግሞ በተቀናጀ መንገድ ሲበታተን የቆየው የትግራይ አቅምን ለማሰባሰብ፣ ለሚመጡ ፈተናዎች ለመቋቋም የሚያስችል አቅም የሚፈጥር ነው። በዚህም ሉዓላዊ ድንበር ትግራይ እንዲከበር፣ በወራሪዎች ሥር እየተገደሉና እየተሰቃዩ ያሉ ወገኖቻችን ነፃ እንዲወጡ፣ የተፈናቀሉና የተሰደዱ ወገኖቻችን ወደ መኖሪያቸው እንዲመለሱ፣ የጅምላ ጭፍጨፋ ፈፃሚዎች ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ፣ የትግራይ ዳግም ግንባታና ፈውስ እንዲጀምር፣ በአጠቃላይ ትግራይ ሕዝብ ካንዣበበበት ህልውና አደጋ ወጥቶ ዋስትናው እንዲረጋገጥ የሚያስችል ትግል ለማካሄድ ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር ነው። ድርድርና ውይይት ለማካሄድ ሲደረግ ካለው ጥረት አንፃርም ተጨማሪ አቅም የሚፈጥር ነው።
ሙሉ የትግራይ ሕዝብ ለሰላም ካለህ ፍላጎት ፕሪቶሪያ ስምምነት እንዲፈፀም በትዕግስት ስትጠይቅ ቆይተሃል። ሆኖም ግን የብልጽግና ስርዓት ስምምነቱን ሌላ ዓይነት ጅምላ ጭፍጨፋ እያደረጉ ሲጠቀሙበት ቆይቶ አሁን ደግሞ ሙሉ በሙሉ አናዷቷል። አሁንም ቀደም ሲል እንደምታደርገው ያንዣበበህን ህልውና አደጋ ለመቋቋም ከመንግስትህና ከመሪ ፓርቲህ ህወሓት ጎን ተሰልፈህ ወሳኝ ሚናህን እንደምትወጣ አይጠራጠርም። ለሚፈጠርልህ አቅም ከዚህ አደጋ ወጥተህ ባትወጣ ብለው ቀጣይ ባለ ሁኔታ ላይ ከሀገር ውስጥም ሆነ ከውጭ የሚደረጉ ዘመቻዎችን ከምንም ጊዜ በላይ ከሀይ ብለህ ለማስቆም ወደ አንድነትህና ድርጅቶቸህ ትኩረት ሰጥተህ ማይቀረውን ድልህን የሚያፋጥን ትግል ማካሄድ ያስፈልጋል።
ታግዶ የቆየው የትግራይ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት መመለሱ ከጦርነትና ከጦርነት ወሬ ጋር ፈፅሞ ያስተሳስረዋል ብለን አናምንም። የትግራይ ሕዝብና አመራሩ ህወሓት አሁንም ቢሆን ሁሉም አለመግባባቶች በድርድርና በውይይት መፈታት አለባቸው የሚለው አቋማቸው ነው። ከዚህ በተጨማሪ በሕዝብ የተመረጠ መንግስት ወደ ሥራው መመለሱ በምንም ዓይነት መልኩ የጦርነት ምክንያት ነው ብለን እንደማናምን በዚህ አጋጣሚ ለመግለፅ እንፈልጋለን።
የህዝባችን መንግስት ለድሉ ይዋጋ!
ለሰማዕታቶቻችን ዘለዓለማዊ ዝክርና ምስጋና!
ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ!
ሚያዚያ 3 ቀን 2018 ዓ.ም

15/06/2025

🫡 🇮🇷💪
“የኢራንን ሉዓላዊነት እስከመጨረሻው እስትንፋሳችን እናስጠብቃለን!” – የኢራን ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም
********************

“ለሀገራቸው ነብሳቸውን ከማይሰስቱ ጀግና ወታደሮቻችን ጋር በመሆን የኢራንን ሉዓላዊነት እስከመጨረሻው እስትንፋሳችን እናስጠብቃለን” ሲሉ የኢራን ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ሜጀር ጄነራል አሚር ሃታሚ ገለፁ።

የቀድሞ የኢራን ወታደራዊ መኮንን የነበሩት ሜጀር ጄነራል አሚር ለተሰየሙበት ኃላፊነት ዝግጁ መሆናቸውንም ባጋሩት መልዕክት ገልፀዋል።

ከቀናት በፊት በእስራኤል ጥቃት ሕይወታቸው ባለፈው አመራሮች የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘንም ገልፀዋል።

ለጥቃቱ አመርቂ የሆነ የአፀፋ ምላሽ ለመስጠት ለሚወሰዱ እርምጃዎች ቁርጠኛ መሆናቸውንም ነው ጠቅላይ ኢታማዦር ሹሙ የተናገሩት።

አክለውም የጦር ሠራዊቱ የሚጠበቅበትን በሟሟላት የውጊያ አቅሙን ለማጠናከር እንደሚሰራ መጥቀሳቸውን የሀገሪቱ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።

4ኛ ቀኑን በያዘው የሁለቱ ሀገራት ግጭት በሁለቱም አካላት በኩል የሰዎች ሕይወት ሲያልፍ የመሰረተ ልማት ውድመቶችም ደርሰዋል።

በአፎሚያ ክበበው

14/06/2025

መድኃኒዓለም አዳኝም መድሀኒትም ነው! በሚሰጥህ ማንኛውም መድሀኒት እና በሚያክሙህ ሀኪሞች ላይ አድሮ እሱ ጨርሶ ይማርህ።
አድኖህ አሁናዊ የክብሩ መገለጫ ፤ የማዳን ሀይሉ ማሳያ ያድርግህ።
ባሪያውን ኢዮብን በዚያ ሁሉ ፈተናና መከራ ውስጥ ያፀናውና ያሳለፈው ሊያጠፋው ሳይሆን ሊያድነው ነውና እነሆ ባንተም ላይ የማዳኑ ሀይል ይምጣ። ፊቱን ወዳንተ ያንሳ አስጨናቂውን ማዕበል በአንዴ ያስቆመው የእግዚአብሔር ልጅ ይህንንም እነሆ ስለ ማያልፈው ቃሉ፤ ስለ ክብሩ፤ስለ ስሙ፤ ስለ ታማኝነቱ፤ ስለ የማይናወጥ አለኝታነቱ እና የማይናወጥ መመኪያነቱ፤ ስለ ከሞት የሚያስነሳው ሀይሉና አዳኝነቱ፤ ስለ ዘለዓለማዊ ምህረቱና ቸርነቱ ጨርሶ ይማርህ። አሜን !!🙏 አቤቱ አዳኛችን እግዚአብሔር ሆይ ስለዚህ ወንድማችን ማንኛው ሰው የሚፀልየውን ፀሎት እባክህን ተቀበል 🙏 ብላተናህንም አድን 👏👏👏🙏🙏🙏🙏 አሜን!!!

11/12/2024

Celebrating my 2nd year on Facebook. Thank you for your continuing support. I could never have made it without you. 🙏🤗🎉

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Doha?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address

Doha