Tocha Communications
28/05/2026
በቶጫ ወረዳ የ10 ወራት የገቢ አሰባሰብ አፈጻጸም ግምገማ እና በቀሪ ቀናት በሚከናወኑ ተግባራት ዙሪያ የጋራ ውይይት ተካሄደ።
የቶጫ ወረዳ ገቢዎች ጽህፈት ቤት የ10 ወራት የገቢ አሰባሰብ አፈጻጸም ግምገማ እና በቀሪው የበጀት ዓመት 40 ቀናት ውስጥ በሚሰበሰቡ የገቢ ትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር የጋራ የምክክር መድረክ አካሂዷል።
የዉይይት መድረኩን የመሩት የቶጫ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታምራት ታደሰ እንደጠቆሙት፦የራስን ገቢ በራስ አቅም ማሳደግ ለወረዳው ልማትና መልካም አስተዳደር መረጋገጥ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።
ባለፉት 10 ወራት የተከናወነው የገቢ አሰባሰብ ስራ የሚበረታታ ቢሆንም፣ ወረዳችን ካለው የገቢ አቅም አንጻር ገና ብዙ መስራት እንደምጠበቅ በማንሳት በቀሪዎቹ 40 ቀናት ውስጥ የተጣለብንን እቅድ ሙሉ በሙሉ ለማሳካት እያንዳንዱ አመራርና ባለሙያ በቁርጠኝነትና ባልተቆጠበ እምቅ አቅሙ መንቀሳቀስ እንዳለበት አሳስበዋል።
የቶ/ወ/ብ/ፓ/ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አንድነት ቡንጉዶ በበኩላቸው፣ የገቢ አሰባሰብ ስራን ውጤታማ ለማድረግ የህግ የበላይነትን ማስከበርና የባለድርሻ አካላትን ቅንጅት ማጠናከር እንደሚገባ ጠቁመዉ ፓርቲው የገቢ አቅምን ለማሳደግ የሚደረገውን የተደራጀ እንቅስቃሴ በቅርበት እንደሚከታተልና እንደሚደግፍ ገልጸው፣ የግብር ከፋዩን ማህበረሰብ ግንዛቤ በማሳደግ ረገድ የፖለቲካ አመራሩ ሚና ከፍተኛ መሆን እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል።
የዳዉሮ ዞን ገቢዎች መምሪያ ከፍተኛ ባለሙያ አቶ በጋሻው ግርማ በበኩላቸው፦በቶጫ ወረዳ የታዩ ጥንካሬዎችንና የታዩ ክፍተቶችን በዝርዝር አቅርበዉ በቀሪዎቹ ቀናት ውስጥ ያሉትን የገቢ አማራጮች አሟጦ ለመጠቀምና የታክስ ስወራን ለመከላከል የሚያስችሉ ስልታዊ አቅጣጫዎችንና የቴክኒክ ድጋፎችን ለተሳታፊዎቹ አብራርተዋል።
በመጨረሻም የመድረኩ ተሳታፊዎችና የጽህፈት ቤቱ ባለሙያዎች በቀረበው ሪፖርትና በቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ሰፊ ውይይት ካደረጉ በኋላ፣ የተሰጣቸውን ግብረ-መልስ መሰረት በማድረግ በቀሪዎቹ 40 ቀናት ውስጥ የገቢ እቅዱን 100 በመቶ ለማሳካትና የበጀት ዓመቱን በስኬት ለማጠናቀቅ ቃል በመግባት መድረኩ ተጠናቋል።
ዘገባዉ፦የቶጫ ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳች ጽ/ቤት ነዉ።
23/05/2026
የቶጫ ወረዳ ትምህርት ጽሕፈት ቤት የ9 ወራት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ አካሂዷል ።
የቶጫ ወረዳ ትምህርት ጽሕፈት ቤት በ2018 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸሙን ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ገምግሟል።
በመድረኩ ላይ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በትምህርት ተደራሽነት፣በጥራት ማሻሻል፣ በግብዓት አቅርቦትና በትምህርት ቤት መሠረተ ልማት ግንባታ ዙሪያ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት የቀረቡ ሲሆን፥ የተመዘገቡ ስኬቶችና ያጋጠሙ ማነቆዎችን በመለየት ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል።
በሌላ በኩል፦በትምህርት ዘርፉ የተጀመሩ አዎንታዊ ለውጦችን አጠናክሮ ማስቀጠልና የቀሩትን የቤት ሥራዎች በቀሪው የበጀት ዓመት ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ መላው የትምህርት ማኅበረሰብ በቁርጠኝነት መንቀሳቀስ እንዳለበት ተጠቁሟል ።
በግምገማ መድረኩ ላይ የደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መ/ፐ/ሰ/የሰ/ሀ/ል/ብሮ ም/ኃላፊ እጩ ዶ/ር ገዛኸኝ ገበየሁ ቶጫ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታምራት ታደሰ፣የወረዳው ብ/ፓ/ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አንድነት ቡንጉዶ እና የዳዉሮ ዞን ትምህርት መምሪያ ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ቴዎድሮስ ተክለ የቶጫ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አፈወርቅ ዮሐንስን ጨምሮ የወረዳዉ ትምህርት ጽ/ቤት ባለሙያዎች፣ የግልና የመንግስት ትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራንና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
ዘገባዉ፦የቶጫ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ነዉ።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the organization
Telephone
Website
Address
Toamasina