Bel

Bel

Share

23/03/2022

የማህበረሰብ ደን ይዞታን ለግል ጥቅም ያዋሉግለሰቦች በእስራት ተቀጡ።

ተከሳሾች፡-1/አቶ መንግስቱ ጌቴ
2/አቶ ይበልጣል አበዋ
3/አቶ አዳነ ላቀ
4/አቶ ሙሉአለም ወለላው
5/አቶ ደሴ ጤናአለም
6/አቶ አየለ ቢያዝን
7/አቶ በድሉ ጅጋር
8/አቶ አበባው ተደሰ የተባሉት የአነደድ ወረዳ ሻፎ ጉዳልማ ቀበሌ ነዋሪዎች ነሐሴ 18 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ሲሆን በሻፎ ጉዳልማ ቀበሌ የሚገኘውን የሻፎ ጉዳልማ ማህበረሰብ የሆነውን ደን በመጨፍጨፍ በቁመት 30 ሜትር በወርድ 200 ሜትር አርሰው ስንዴ በመዝራታቸው የአነደድ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት በደረሰው ጥቆማ መሰረት ምርመራ በማጣራት የምርመራ መዝገቡን ለወረዳው ዐቃቤ ህግ ጽ/ቤት ልኳል፡፡
የአነደድ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤትም የፖሊስን የምርመራ መዝገብ መርምሮ ግለሶቦቹ በተጠረጠሩበት የወንጀል ህግ አንቀፅ 686(2) መሰረት በአነደድ ወረዳ ፍ/ቤት ክስ በመመስረት ሲከራከር የቆየ ሲሆን የወረዳው ፍ/ቤትም በቀን 08/07/2014 ዓ/ም በአስቻለው ችሎት ከ1ኛ እስከ 7ኛ የተጠቀሱት ተከሳሾች በ1 ዓመት ከ8 ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጡ 8ኛ ተከሳሽ ደግም 1 ዓመት ከ6 ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ወሳኔ ሰጥታል በማለት የአነደድ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት መረጃ ያመለክታል፡፡
የአማራ ክልል ፍትህ ቢሮ

Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Wicklow?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address

Wicklow