Hanan Mohammed

Hanan Mohammed

Share

15/05/2026

#ከተባለልህ መድረስህ አይቀርም!
#ይህ ፎቶሾፕ ወይ AIይም እንዳይመስልህ።እውነተኛ ፎቶ ነው።

ዲና ሲቦማና አሁን 18 ዓመቱ ነው። የ 6 ዓመት ህፃን እያለ በኮንጎ(DRC) ብሄራዊ ፓርክ ለመጎብኘት ከወንድምና ከአክስቱ ልጅ ጋር ተገኘ።ቀኑን ግን እንዳሰቡት ሚዝናኑበት ሳይሆን ቀረ።ከኬጁ ያመለጠ ቺምፓንዚ ሶስቱ ላይ ጥቃት ሰነዘረ በዚህም ወንድሙና የኣክስቱ ልጅ ሲሞቱ እሱ ክፉኛ ተጎድቶ ተረፈ።

በደረሰበት ጉዳትም ሁለቱ ከንፈሮቹን ኣንድ ጆሮውን እና ኣንድ ጣቱን ኣጣ ፊቱም ክፉኛ ተበላሸ።

ይህ ጉዳይ ከደረሰበት ሁለት ዓመት በኃላም በ8 ዓመቱ ወደ አሜሪካ ኣቅንቶ ህክምና እንድያረግ ሚያስችል የቻሪቲ ፕሮግራም ደርሶት አሜሪካ ሄደ ህክምና ተደረገለት በዛውም እሱን በጉዲፈቻ ምያሳድጉ ቤተሰቦች አገኘ።ጥሩ ህክምና ያገኘው ሲቦማናም ታድያ ለፍሪስታይል ሪስሊንግ ልዩ ፍቅር አደረበት ልምምዱንም ጠንክሮ መስራት ቀጠለ።

አሁን 18 ዓመቱ ላይ ነው።በቅርብ በተደረገ የአፍሪካ ፍሪስታይል ሬስሊንግ ውድድርም በሶስት ቀን ውስጥ ሁለት ወርቅ ሜዳልያን ለሀገሩ ኮንጎ አስገኝቷል።ሲቦማና በወጣትም ይሁን በአዋቂ ምድብ ባረጋቸው 34 ፍልምያዎች አንድም ጊዜ ሳይሸነፍ ሁሉንም በድል አጠናቋል።አሁን ቀጣዩን የፍሪስታይል ሬስሊንግ ይቆጣጠራሉ ተብለው ከሚጠበቁ ስፖርተኞች መሀል ግንባር ቀደሙም ነው።

አትሙት ያላት ነፍስ !!!

ምንጭ:- ተግባሩ ታምራት

12/04/2026

መረጃ ፦ ዩናይትድ ኪንግደም በሆርሙዝ ሰርጥ ላይ በሚደረገው የአሜሪካ የባህር ላይ ከበባ እንደማትሳተፍ አስታወቀች።

ትራምፕ ቀደም ብሎ በሰጠው መግለጫ “ዩናይትድ ኪንግደም የጦር መርከቦችን በመላክ ታግዛለች፣ ምናልባትም ሌሎች አገሮችም እንዲሁ ያደርጋሉ” ሲል ተናግሮ ነበር።

Photos from Hanan Mohammed's post 09/04/2026

🏗️⚡🇪🇹 Ethiopia Electric Utility Headquarters – Rising Above Addis Ababa

📍 Location: Mexico Square, Addis Ababa
🏢 Structure: 5B + G + 2M + 63 Floors + 7 Upper Floors
📏 Height: 327.5 meters (300m+ landmark)

💰 Estimated Cost: 7 Billion Birr
📐 Plot Size: 20,792 m²

🏗️ Total Floor Area: 208,724 m² (subject to change)
የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ዋና መሥሪያ ቤት በአሁኑ ጊዜ በሜክሲኮ አደባባይ እየተገነባ ያለ ግዙፍ 63 ፎቅ ሰማይ ጠቀስ ሕንፃ ነው። ለኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል (EEP) ማዕከላዊ የአስተዳደር ማዕከል ሆኖ እንዲያገለግል የተነደፈው ይህ ታዋቂ ግንብ የአገሪቱን የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት፣ ማስተላለፍ እና ስርጭት በማስተዳደር ረገድ ወሳኝ ሚና ይጫወታል።

🌍 ግንባታው ሲጠናቀቅ፣ ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ክፍሎች ካሉት ረጃጅም ሕንፃዎች አንዱ ለመሆን ተዘጋጅቷል፤ ይህም የአዲስ አበባን ሰማይ ጠቀስ ሕንፃ እንደገና የሚገልጽ እና እያደገ የመጣውን የኢትዮጵያን መሠረተ ልማትና ምኞት የሚያመለክት ነው።

Website