Sena computer technology

Sena computer technology

Share

05/07/2024
08/05/2021

# የፌስቡክ አፈጣጠር ታሪክ

የፌስቡክ መስራች እና ባለቤት የሆነው ማርክ ዙከርበርግ ከክፍል ጓደኞቹ ኤድዋርዶ ሳቨርን ፣ ዱስቲን ሞስኮቭዝ እና ክሪስ ሂዩዝ ጋር ፌስቡክን ሲፈጥሩ ገና የሃርቨርድ ዩኒቨርስቲ የኮምፒተር ሳይንስ ተማሪዎች ነበሩ። በሚያስደንቅ ሁኔታ በአሁኑ ጊዜ በዓለም ላይ በጣም ተወዳጅ የሆነው የማኅበራዊ ትስስር ገጽ ፌስቡክ መጀመሪያ ሲፈለሰፍ የሰወችን ፎቶ በመለጠፍ የትኛው ያምራል የሚለውን ለማወዳደር ታስቦ የተሰራ ነበር።

🔺የፌስቡክ አጀማመር

◽️ እ.ኤ.አ በ 2003 በሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ የሁለተኛ ዓመት የኮምፒውተር ሳይንስ ተማሪ የሆነው ዙከርበርግ FaceMash ለተባለ የድረገፅ እና መጠቀሚያ ሶፍትዌር ሰራ። የኮምፒተር እውቀቱንም በመጠቀም ወደ ሃርቫርድ የደህንነት አውታረመረብ (Security Network) ሰብሮ በመግባት የተማሪዎች መታወቂያ ለይ ያሉ ምስሎችን በመሰብሰብ ያለፈቃድ FaceMash ለይ መለጠፍ ቻለ። ከዚያም ይህን ዙከርበርግን ድረገፅ የሚጎበኙ ተማሪዎች ከሚመጡላቸው ጥንድ ጥንድ ፎቶዎች አንዱ ያምራል አንዱ አያምርም እያሉ እንዲመርጡ ይጠየቃሉ።

◽️ FaceMash ጥቅምት 28 ቀን 2003 ከተከፈተ ከጥቂት ቀናት በኋላ በሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ ተዘጋ። ከዚያም ዩኒቨርስቲው ዙከርበርግን የሰዎችን ደህንነት በመጣስ ፣ የቅጂ መብቶችን በመጣስ እና የግለሰቦችን ግላዊነት በመጣስ ከባድ ክሶች ከሰሰው። ዙከርበርግ በዚህ በድርጊቱ ከሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ መባረር ቢገጥመውም በእሱ ላይ የተጣሉ ሁሉም ክሶች በመጨረሻ ተሽረውለታል።

🔺 The Facebook፡

◽️ እ.ኤ.አ. የካቲት 4 ቀን 2004 ዙከርበርግ TheFacebook የተባለ አዲስ ድረገፅ ከፈተ። TheFacebook በሃርቫርድ በዩኒቨርሲቲ የሚገኙ ተማሪዎች እርስ በእርሳቸው ይበልጥ መተዋወቅ እንዲችሉ እንዲረዳቸው ታስቦ የተሰራ ነበር። ነገር ግን ከስድስት ቀናት በኋላ የሃርቫርድ ተማሪዎች የሆኑት ካሜሮን ዊንክለቮስ ፣ ታይለር ዊንክሌቮስ እና ዲቪ ናሬንድራ ዙከርበርግ ሀሳባቸውን እንደሰረቀባቸው በመናገር ዙከርበርግን ሲሰሱት ዙከርበርግ እና The Facebook ችግር ውስጥ ገቡ። ሆኖም ግን እነዚህ የይገባኛል ጥያቄ አቅራቢዎች ከዙከርበርግ ጋር ተወያይተው ጉዳዩን ከፍርድ ቤት ውጭ ፈቱት።

◽️ The Facebook በመጀመሪያ ለሃርቫርድ ተማሪዎች የተከለከለ ነበር። ከጊዜ በኋላ ግን ዙከርበርግ ድረገፁን ለማሳደግ እንዲረዱት ጥቂት የትምህርት ቤት ጓደኞቹን አስገባቸው። ለምሳሌ ኤድዋርዶ ሳቬሪን በቢዝነሱ ፣ ዱስቲን ሞስኮቭዝ በፕሮግራሚንግ ባለሙያነት ፣ አንድሪው ማኮሉም የጣቢያው ግራፊክ አርቲስት አንድ ላይ በመሆን ድረገፁን ወደ ተጨማሪ ዩኒቨርሲቲዎች እና ኮሌጆች ለማስፋፋት ችለዋል።

🔺የፌስቡክ-እድገት

◽️ እ.ኤ.አ በ2004 የNapster መስራች እና ባለሀብት ሴአን ፓርከር የፌስቡክ ፕሬዝዳንት ሆነ። ኩባንያውም የድረገፁን ስም ከTheFacebook ወደ Facebook የቀየረው። በቀጣዩ ዓመት ኢንቬስት ካፒታል ኩባንያ አኬል ፓርትነርስ በፌስቡክ ላይ 12.7 ሚሊዮን ዶላር ኢንቬስት ያደረገ ሲሆን ይህም ፌስቡክን ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የመገናኛ የኔትወርክ እንዲፈጠር አስችሎታል።

◽️ እ.ኤ.አ. በመስከረም ወር 2006 ፌስቡክ ቢያንስ 13 ዓመት የሆነ እና እውነተኛ የኢሜል አድራሻ ያለው ማንኛውም ሰው ፌስቡክ መቀላቀል እንደሚችል አስታውቋል። እ.ኤ.አ. በ2009 ፌስቡክ በዓለም ላይ በጣም ጥቅም ላይ የዋለው የማኅበራዊ የአውታረ መረብ አገልግሎት ሊሆንም ችሏል።

◽️ የፌስቡክ ትርፍ በመጨረሻ ዙከርበርግን የዓለም ወጣቱ Multi billionair

Website