Gifaataa Tube

Gifaataa Tube

Share

New Ethiopian music Seniye ሰኒዬ Lij Motolomi gifaataa tube official video 01/07/2025

https://youtu.be/jhi1TmyHQrI?si=T3LB4Lp9NDBvlaLv

New Ethiopian music Seniye ሰኒዬ Lij Motolomi gifaataa tube official video የyoutube ቻናላችንን ሳብስክራይብ አድጉwww.youtube.com/.tiktok.com/.naatu.keettaaNew Ethiopian music video አዲስ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ቪዲዮ

21/06/2025

‎ !
‎ ዐፄ ምኒልክ ዳግማዊ አንድ የሆነችውን ኢትዮጵያ ለመፍጠርና ሁሉንም ጠቅልሎ ራሱ ለመግዛት አቅደው በተነሳው ከፍተኛ ውጊያ በየብሔሩ ንጉሥ አንግሠው የሚተዳደር ህዝብ መንግሥታዊ ሥርዓቱን፣ ባህሉን፣ቋንቋውን፣ ሀብትና ንብረቱን፣በሕይወት የመቆየት ዕድሉንም ጭምር በዐፄው እጅ እያስረከበ ወደ አገዛዙ ይቀላቀል ነበር። የምኒልክ ጦር በኃልና በቁጣ ተሞልቶ በጉልበት እየገባ ግዛትን ሁሉ የምኒልክ እያደረገ ከሰሜናዊ ኢትዮጵያ አቅጣጫ ወደ ደቡብ እየገሰገሰ ሲመጣ አንድ ያልታሰበ አደጋ ገጠመው። ቀይ መሥመር ! እሳተ-ገሞራ! የማይወጣ ግዙፍ ተራራ! ነጎድጓዱ ንጉሥ አስፈሪውና አስደንጋጩ ካዎ ጦና! ባልሽያ ማታ! ጋንጌ ፈረስ! ማጫምያ እና ጎንዳልያ! በቀይ፣ ቢጫና ጥቁር ቀለም ያጌጠ እንደአሸዋ የማይቆጠር ቁጡ ህዝብ! ታላቁ ንጉሥ ካዎ ጦና ጋጋ የሚያስተዳድረው የወላይታ መንግስት!!! በዓፄው ተልዕኮ የመጣው የመጀመሪያው ዙር ጦር በደቡቡ እሳት ባህር ውስጥ ሰጥመው ቀረ። ሁለተኛ ዙርም የተላከው ጦር የማጫምያ ቶራ እራት ሆነ።
‎ የዐፄውን ጦር አላሻገር ያለውን የእሳቱን ባህር ለመጎብኘት ራሱ ዓፄ ምኒልክ ጦር እየመራ መጣ። ከሰው እስከ ንብ በዓፄ ምኒልክ ጦር ላይ ተረባረቡበት። ሸና። ፈራ። ግን ወደኃላ ከተመለሰ በሽንፈት መንፈስ አንገቱን ደፍተው ሌሎችን መግዛት ስለማይችል መሞትን መረጠ። ደጋግመው ሞከረ። የሰው ሕይወት በሁለቱም በኩል ረገፈ። የሰው ደም እንደ ዓባይ ወንዝ ጎረፈ። ካዎ ጦና ብሎም ዓፄ ምኒልክ በግምባር የተሣተፉበት ጦርነት በአልሸነፍ ባይነት ቀጠለ።
‎ በመጨረሻም አፄ ምኒልክ አንድ ነገር አሰበ። ጉልበት ሄጄማ ይህን ንጉሥ ማሸነፍ አልችልም አለ። ሌላም ዘዴ መዘየድ እንዳለበት ገባው። ባንዳ መፈለግ ጀመረ። አገኘም። "የወላይታ ህዝብ ቤቱንና ልጆቹን እጅጉን ስለሚወድ ሕዝቡ ከፊት እየተዋጋ ከኃላ ቤታቸውን በእሳት ብታቃጥል የካዎው ጦር ቤቱንና ልጆቹን ለማትረፍ ወደቤቱ ይሮጣል" የሚትል ምክር በገንዘብ ከተገዛ ባንዳ ተለገሰችለት። የባንዳው ምክር እውን ሆነ። ለዓፄውም ተሳካለት። አሸነፈ። ካዎውንም ያዘ። ሁለቱ ጀግኖች እጅ ለእጅ ተያይዞ እንጦጦ ገቡ።
‎ ዓፄ ምኒልክ ዳግማዊ ጦርነቱን በብዙ ትግል ከረታ በኃላ በጀግናው በወላይታ ህዝብ ዘላለማዊ ቂም ያዘ። ኢትዮጵያ እስካለችበት ዘመን ሁሉ የትኛውም መንግሥት ሲመጣ በተመሳሳይ አቋም የሚተገብረውን በደል ለወላይታ ህዝብ ቀርፆ በአደራ መልክ አስቀመጠ። ከዚህ የተነሳ መንግሥት በሌላ መንግሥት ሲተካም በወላይታ ህዝብ በደል ጉዳይ አይደራደርም። ከዓፄ ምኒልክ ዳግማዊ መንግሥት አገዛዝ ጀምሮ እስከ ብልፅግና መንግሥት በወጥ አቋም ወላይታን የማድቀቅ ሥራ በብቃትና በንቃት እየሠሩ መጥተዋል።
‎ አዎ፣ ከጥንት ጀምሮ የኢትዮጵያ ፖለቲካ በወላይታ ህዝብ ላይ በተለያዩ መልኩ ጫናዎችን ሲያሳድር መቆየቱ የታሪክ እውነታ ነው። ይህ ጫና የወላይታን ነባር የራስ ገዝ አስተዳደር፣ ባህልና ማኅበራዊ ገጽታዎች ላይ ተጽዕኖ ሲያደርግ ቆይቷል። እስኪ የኢትዮጵያ መንግሥት ምን አይነት በደሎችን በወላይታ ህዝብ ላይ እየሰነዘረ ነው የሚለውን ከብዙ ጥቅቱን እንመልከት፦

‎ 1.

‎ :- የወላይታ ህዝብ በ13ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ እስከ 19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ድረስ በ"ካዎ" በሚባሉ ነገሥታት የሚመራ ጠንካራና የራሱ የሆነ የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ መዋቅር ያለው መንግሥት ነበረው። ይህ የራሳቸው የራስ ገዝ አስተዳደር የወላይታ ህዝብ የራሱን ዕድል በራሱ እንዲወስን አስችሎ ነበር።
‎ :- በ1894 ዓ.ም. (1900 እ.ኤ.አ.) ዐፄ ምኒልክ ዳግማዊ የደቡብ ግዛቶችን ወደ ኢትዮጵያ ግዛት የማካተት ዘመቻ አካል ሆኖ የወላይታ መንግሥት ከባድ ጦርነት ከተካሄደ በኋላ ተጠቃለለ። ይህ ወረራ የወላይታን የፖለቲካ ነፃነት በማስቆም የበርካታ ዓመታት የፖለቲካ ጫና መጀመሪያ ሆነ። ንጉሥ ካዎ ቶና የመጨረሻው ገለልተኛ ንጉሥ በመሆን ከፍተኛ ተቃውሞ አድርገው ነበር።

‎ 2.

‎ :- ወላይታ የኢትዮጵያ አካል ከሆነች በኋላ፣ በአዲስ አበባ ከተሾሙ ገዥዎች (ሹሞች) ሥር እንድትተዳደር ተደረገች። የወላይታ ባህላዊ የአስተዳደር መዋቅር ተዳክሞ በማዕከላዊው መንግሥት ቁጥጥር ስር ወደቀ። ይህ ደግሞ ህዝቡ የራሱን ጉዳዮች በራሱ የመወሰን ሥልጣን እንዲያጣ አደረገ።
‎ :- ወላይታ በወቅቱ በሲዳሞ ክፍለ-ሀገር ሥር እንደ አውራጃ ሆና እንድትተዳደር ተደረገች። ይህ ውሳኔ የወላይታ ህዝብ የፖለቲካዊ ውክልናውንና ተሰሚነቱን እንዲያጣ አደረገ፣ ምክንያቱም የሌላ ትልቅ ክፍለ-ሀገር አካል በመሆኑ በሀገራዊ የፖለቲካ ምህዳር ውስጥ የራሱን ድምጽ በበቂ ሁኔታ ማሰማት አልቻለም።
‎ :- ለረጅም ጊዜ የወላይታ ህዝብ በአገር አቀፍ የፖለቲካ ውሳኔዎች ላይ ተገቢውን ተሳትፎና ተፅዕኖ ማድረግ አልቻለም። ይህ ደግሞ በህዝቡ ላይ የፖለቲካዊ ጫና እና የእኩልነት ስሜት እንዲፈጠር አስተዋፅኦ አድርጓል።

‎ 3.

‎ :- "ወላይታ" የሚለው የህዝቡ እውነተኛ ስም ቢሆንም፣ ከውህደቱ በኋላ "ወላሞ" በሚለው ስያሜ በውጪ አካላት በሰፊው መጠራት ጀመረ። ይህ የስም ለውጥ የአንዳንድ የማንነት ጫናዎች ምንጭ ሆኖ ቆይቷል።
‎ :- በማዕከላዊው መንግሥት ለአማርኛ ቋንቋና ለዋናው የኢትዮጵያ ባህል ቅድሚያ የመስጠት ዝንባሌ የነበረ ሲሆን፣ ይህ ደግሞ እንደ ወላይታቶ ዶና ያሉ የአካባቢ ቋንቋዎችና ባህሎች ተገቢውን ዕውቅና እንዳያገኙና እንዲዳከሙ ጫና ፈጥሯል።

‎4. (ከ1995 ዓ.ም. በኋላ)

‎ :- በ1995 ዓ.ም. የተቋቋመው የፌዴራል ሥርዓት ብሔር-ብሔረሰቦች የራሳቸውን ክልል እንዲመሰርቱ መብት ቢሰጥም፣ የወላይታ ህዝብ የራሱን ክልል ለማደራጀት እያደረገ ያለው ጥያቄ ለረጅም ጊዜ ምላሽ ሳያገኝ ቀርቷል። ይህ የፖለቲካዊ ውሳኔ መጓተት በህዝቡ ላይ ከፍተኛ ጫናና ቅሬታ ፈጥሯል። ህዝቡ የራሱን ባህል፣ ቋንቋና ልማት በራሱ ክልል ውስጥ በተሻለ መንገድ ማስተዳደር እንደሚፈልግ ያምናል።
‎ :- በአሁኑ ወቅት የወላይታ ዞን የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አካል ነው። ይህ ክልል በርካታ ብሔር ብሔረሰቦችን በአንድ አስተዳደር ስር የሚያካትት በመሆኑ፣ የወላይታ ህዝብ የፖለቲካዊ ክብደቱንና ተሰሚነቱን አጥቷል የሚል ስሜት ሰፊ ነው።
‎ :- በአጠቃላይ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህዳር ውስጥ፣ የብሔር ጥያቄዎች እና የማንነት ውክልና ጉዳዮች ውስብስብ በመሆናቸው፣ የወላይታ ህዝብ የፖለቲካዊ ጥያቄዎቹን በበቂ ሁኔታ ማስተናገድ አስቸጋሪ ሆኖበታል።
‎ :- የወላይታ ሕዝብ ቁጥር በኢትዮጵያ ኦሮሞን ቀጥሎ ሁለተኛ ደረጃ የያዘ ነው። ወላይታ ከ26 ሚልዮን ሕዝብ በላይ ነዋሪዎች የሚኖርባት ምድር ናት። ነገር ግን የመሠረተ ልማት ጥያቄዎችና የልማት ቅድሚያዎች ላይ ተፅዕኖ እንዳለ ይታመናል። ከዚህም የተነሳ ወጣቶቿ በስደት ወደዓለም ክፍል ሁሉ ተበትኗል። ለትውልዱ ሰፊ የሥራ ዕድል መፍጠር የሚችል አንድ ፋብሪካ የላትም። ሌላው ቀርተው የገዛ መሬቷ በሌላ አካባቢ ተወላጅ ኢንቨስተሮች ተቆጣጥረው ነዋሪው በዘመናዊ ባርነት በገዛ ቀዬው ለባዳ ተሸክመው ውሎ የዕለት ጉርስ ይዞ ይገባል።

‎ #ማጠቃለያ

‎ከዐፄ ምኒልክ ወረራ ጀምሮ እስከ አሁኑ የፌዴራል ሥርዓት ድረስ፣ የኢትዮጵያ ፖለቲካ በወላይታ ህዝብ ላይ የራሱ የሆነ ጫና ሲያሳድር መቆየቱ ግልጽ ነው። ይህ ጫና በዋነኛነት ከራስ ገዝ አስተዳደር ማጣት፣ ደካማ የፖለቲካ ውክልና፣ የማንነት ጥያቄዎችና የልማት ፍላጎቶች ጋር የተያያዘ ነው። የወላይታ ህዝብ የራሱን ማንነትና መብት ለማስጠበቅ የሚያደርገው ትግል ደግሞ የዚህ ጫና ውጤት ነው።

‎በወላይታ ሁለንተናዊ የሚዲያ አገልግሎት ማዕከል ተዘጋጅቶ የቀረበ ሰኔ 14 ቀን 2017 ዓ.ም።
‎ለበለጠ መረጃ:-
‎email - [email protected]
‎Wwebsite- http://gifaataatubeblogspot.com
‎Youtube- https://youtube.com/
‎Tiktok- https://tiktok.com/.naatu.keettaa
‎ Facebook:- https://www.facebook.com/share/1EZRVzrQtr/
https://www.facebook.com/share/16t5CTL6jo/
https://www.facebook.com/share/16kTnUc3pQ/
https://www.facebook.com/wolayta.dicha.982731
‎telegram- https://t.me/gifaataatube

Photos from Gifaataa Tube's post 18/06/2025

‎ አንድ እውነት በንግግር ሳይሆን በተግባር ማየት ከቻልክ አንተ ትክክለኛ ተመራማሪ ነህ። እውቀትም እውነትም በትክክለኛው መንገድ ታገኝበታለህ። በንግግርማ ማንኛውም የትናቱ ወጠጤ ራሱን በሰማይ አስቀምጦ አያስነካህም። ከአፉ የሚወጣውን ቃል አልፈህ ወደ ታሪኩ ሲትመጣ ግን ነገሩ ጉም መጨበጥ ይሆንብሃል። በአፈ-ታሪክ የመሸወድ ጊዜ ይብቃህ።
‎ ና! ወደ 50+ ነገሥታት ሀገር ወደ ወላይታ ና! በላይና በታች የሚንጫጫ የጫጩቶች ድምፅ አልፈህ ና! የትናንትናዎቹ አዲስ ጎጆቹን አልፈህ ከጥንት ጀምሮ መሠረቱን በዓለት ላይ ወዳደረገው ቤት ወደ ወላይታ ና!
‎በአቅራቢያው ካሉት ወገኖች ቀንጨብ ቀንጨብ አድርጋ በመውሰድ ብሔሯንና ባህሏን ገና እየቀረፀች ካለችው ከግልገሏ አልፈህ ብዙኃኑን አቅፈው ቋንቋውንና ባህሉና በልግስና ተሰጥቷቸው በሥልጣኔ ጎዳና ላይ እንዲራመዱ ወዳደረገው ወደ ወላይታ ና!
‎ መጥቼ ምን የተለየ ነገር አያለሁ ትላለህ? ጥሩ ጥያቄ ነው ያነሳኸው። መጥተህ የሚታየው:-
‎ #1. ከሃምሣ በላይ የወላይታ ነገሥታት ታሪክን ፤ የመንግሥታቸውን ሥርዓት ፤ ዲፕሎማሲያቸውን፤ ድንበር ጠባቂ ብቻ ሳይሆኑ የተለያዩ አናሳ ጎሳዎችን በራሳቸው እያጠቃለሉ ድንበራቸውን ያስፋፉ መሆናቸውን፤ ጀግንነታቸውንና ሥልጣኔያቸውን ትመለከታለህ።
‎ #2. ማርጩዋ ታያለህ። ማርጩዋ ምንድ ነው ልትል ትችላለህ። በዱሮ ገበያ ሥርዓት ሰው የተለያየ ዕቃ ይዘው ወደ አንድ ሜዳ በመሰብሰብ ዕቃን-በዕቃ እየቃያየሩ የሚገበያዩበት ሥርዓት ነበር። ይህንን ሥርዓት በማዘመን በአህጉር ቀዳሚ የሆነውን ማርጩዋ የተባለውን የሀገሩ ገንዘብ በማምረት ዕቃን በገንዘብ የመግዛት ዘመናዊ የገበያ ሥርዓት ያመጣ በአፍሪካ ተቀዳሚ ሀገር ወላይታ ነው። በዚያን ዘመን በማርጩዋ ዓለም አቀፋዊ ንግድ እንደሚደረግና አንድ ማርጩዋ በስድስት ዶላር እንደሚመነዘር ታሪኩ ያረጋግጣል። ና ላሳህ!
‎ #3. ታሪካዊና መዝናኛ ቦታዎችን ትጎበኛለህ። ካዎ ጋሮታ(ቤተ-መንግሥታት)፤ ታሪካዊና ከ70,000 ዓመት በላይ ዕድሜ ያስቆጠሩ ዋሻዎችን፤ በአፍሪካ ደረጃ ረዥም የተባሉ ፏፏቴዎችን፤ ጦሳ ዛርጵያ(የእግዜር ድልድይ)፤ የተፈጥሮና ሰው ሠራሽ ሐይቆችን፤ እስከ አጎራባች አፍሪካ ሀገራት ድረስ ተዘርግተው ለሃገራችን ከፍተኛ የገቢ ምንጭ የሆነውን ጊቤ-3 ኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድብ፤ ተክል ድንጋዮችን፤ ጥንታዊና ታሪካዊ ከተሞችን፤ ሙሉ የወላይታ ህዝብ ጥንታዊ የቤት ቁሳቁሶችንና የጦር መሣሪያዎችን የያዙ ሙዚየሞችን፤ በራሱ ዘመን አቆጣጠር መሠረት አዲስ ዓመትን የሚቀበልበት የጊፋታ በዓልን፤ ወዘተ ትመለከታለህ።
‎ #4. ጥንታዊ የወላይታ ህዝብ ሙዚቃ መሣሪያዎችንና ህዝባዊ ዘፈኖችን ታያለህ፤ትሰማለህም። በአፍሪካ አህጉር ከወፎች ዝማሬ በስተቀር በዜማ የሚከፈት የሰው አፍ ባልነበረበት ዘመን የወላይታ ህዝብ ለሠርግ፤ ለደቦ ሥራ፤ ለልደት፤ ለሙሾ፤ ለበዓላትና ለተለያዩ ጉዳዮች እንደየሁኔታቸው የቃል ግጥም በማዘጋጀት ኩነቶችን በዜማ ይገልፁ ነበር። በዚያ ብቻ ለምን ትደነቃለህ? የኩኔቶችን ዜማ የሚደግፍ ላሁኖች ሙዚቃ መሣሪያዎች መሠረት የሆኑ የሙዚቃ መሣሪያዎችን ሙሉ ባንድ አድርገው መፍጠራቸውን መቼ ሰማህ? ድንክያ፤ጫቻ ዛእያ፤ኡልዱዱዋ፤ካምባ፤ካራቢያ፤ዲታ፤ እና የመሳሰሉትን በመፍጠር ከዘመን ቀድሞ በመሠልጠን ዜማቸውን በባህላዊ ባንድ ታጅበው ያቀርቡ ነበር።
‎ #5. ጥንታዊ የወላይታ ህዝብ ባህላዊ ልብሶችን ትመለከታለህ። ሃድያ ተብለው የሚጠራው የወላይታ ብሔር ባህላዊ ልብሶች አጠቃላይ ስያሜ በውስጡ አምስት ዓይነት ባህላዊ ልብሶችን የያዘ ነው። አዎ! የወላይታ ህዝብ ከጥንት ጀምሮ የሠለጠነና ምሁር ህዝብ ነው። ለለቅሶ የሚለብሰውን ለሠርግ አይለብስም። ለሠርግ የሚለብሰውን ለጦር ሜዳ አይጠቀምም። ንጉሥ የሚለብሰውን ህዝብ አይለብስም። ለሁሉ የየራሱ ባህላዊ ልብስ በአምስት ዓይነት በማዘጋጀት ሥርዓት ባለው መልኩ የተጠቀመ ህዝብ ነው። በዚያን ዘመን የወላይታ ብሔር ቀያይረው ስለለበስ የአፍሪካ ምድር ላይ የልብስ ፋብሪካና ሌላ ልብስ የሚጠቀም ብሔር ያለ እንዳይመስልህ! አአልነበረም። ግን ጠቢቡ የወላይታ ህዝብ ልብሶቹን በእጆቹ ሸምኖ በማዘጋጀት ይጠቀም ነበር። ልብሶቹም:-ጉቱማ ሃድያ፣ ሴሬ ሃድያ፣ ጉማራ ሃድያ፣ ፓታላ ሃድያ እና ዱንጉዛ ሃድያ በመባል ይታወቃሉ። ዕድለኛ ከሆንክ ስትመጣ አይተህ ትመሠክራለህ።
‎ #6. ጥንታዊ ቤተ-እምነቶችን ታያለህ። በደቡብ ኢትዮጵያ አካባቢ ከየትኛውም ብሔር ቀድሞ የክርስቲና እምነት የተቀበለው የወላይታ ህዝብ ነው። ከ700ዓመት በላይ ዕድሜ ያስቆጠሩ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማንያን ቤተክርስቲያንን ታያለህ። ከወላይታ ህዝብ የተገኙ አባታችን ሶስተኛውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ያረፉበትን መቃብር ታያለህ። በኢትዮጵያ ደረጃ ከሁሉም ቀድሞ የወንጌላውያን አቢያተክርስቲያናት እምነት የተቀበለው የወላይታ ህዝብ ነው። ለአብዘኞቹ የወንጌላዊት ቤተ-እምነቶች እናት የሆነችው የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን የተጀመረችው ብሎም ስያሜዋን ያገኘችው በወላይታ እምነት አባቶች ነው። በርካታ ነቢያት ፈጣሪ በሰጣቸው ራዕይ መሠረት የሚንትሪ ቤተ አምልኮ መሥርተው ባሁኑ ጊዜ በየቀኑ በሺዎች የሚቆጠሩ አዳዲስ ነፍሳት ወደ ፈጣሪያቸው መንግሥት እንዲቀላቀሉ በማድረግ ላይ ያሉ ታላቅ አገልጋዮች የተወለዱበት ሀገር ወላይታ። በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ኃላፊነት የሚሠሩ ታላላቅ የእስልምና እምነት ተከታዮችና ዕድሜ ጠገብ መስገዶች ያሉበት ሀገር ነው ወላይታ። የደቡብ ኢትዮጵያ አካባቢዎችን ሙሉ የሚያስተዳድረው ፣ ሰፊ በመንፈሳዊና ማህበራዊ ድጋፎችን በመስጠት የሚታወቀው የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የመጀመሪያው የደቡብ አካባቢዎች ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ታገኛለህ። በሐዋሪያት ቤተ እምነት፣ በአድቫንቲስት ቤተ- እምነት፣ በይሆዋ ምስክሮች ቤተ እምነት ፣ ወዘተ የወላይታ ምድር ተቀዳሚ ናት። መጥተህ ካየህ ከሰማኸው ይበልጣል።
‎ #7. በእንግዳ ተቀባይነቱ፣ በአቃፍነቱ፣በለጋስነቱ፣በጀግንነቱ፣በሥራ ወዳድነቱ፣በጥበቡ፣በታታሪነቱ፣በፈጠራ ሥራዎች፣ በምርምር፣ ወዘተ የሚታወቀውን ታላቁን የወላይታ ህዝብን ታያለህ። በእርግጥ የወላይታ ህዝብና ወላይትኛ ቋንቋ የሌለበት የዓለም ክፍል የለም። ቢሆንም መነሻውጋ በመምጣት የሚታየው ህዝብና የሚትሰማው ወላይትኛ የተለየ ደስታ እንደሚሰጥህ ሙሉ እምነት አለኝና ግድ የለም ና!
‎ #8. መጥተህ የሚትመገበው በዓለም ደረጃ ተወዳጅነትን ያተረፈው የወላይታ ባህላዊ ምግብ። አንተ ብቻ መምጣትህን እርግጠኛ ሁን። የወላይታ ህዝብ ሎጎሙዋ፣ ሱልሱዋ፣ቆጭቆጫዋ፣ ባጭራ፤ሼንደራ፣ፕጫታ፣ ሙቹዋ፣ ፖሻሙዋ፣ ብላንዱዋ፣ Cadhdhiyaa፣ፕላ፣ጉርዱዋ፣ እና ከሁሉም በላይ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ የጥሬ ስጋ አምሮቱን ለማርካት ወደ እኛ እንዲመጡ ምክንያት የሆነውንና በብዙ ዓይነት ዳጣ በተለየ አቀራረብ የሚቀርበውን፤ የወላይታ አምባሳደርም የሆነውን ቁርጥ ሥጋ በቃኝ እስኪትል ድረስ ልመግብህ ተዘጋጅተው እየጠበቀ ነዉ።
‎ ስትመጣ የመንገድ ችግር የሌለበት፤ ስትደረስ የመብራት፣ የንፅህና ውኃ፣ ንፁህ ማረፊያ ሥፍራ፣ የኔትወርክና የነፃ ዋይፋይ ችግር በፍጹም አይገጥምህም። ዛሬ ያገኘህ ወላይታዊ ወንድምህ ሆኖ በሴኮንድ ይግባባሃል። ወደ ቱሪዝም መዳረሻዎች የሚያጓጉዙ ምቹና ዘመናዊ ተሽከርካሪዎች እንዲሁም ደግሞ እንግሊዘኛን ጨምሮ ከሀያ በላይ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገራትን ቋንቋዎችን አቀላጥፈው የሚናገሩ አስጎብኚዎች ተዘጋጅተው ይጠብቁሃል። ና!
‎ ግን ትመጣለህ ወይስ ዝም ብለህ አስለፈለፍከኸኝ?
‎youtube.com/


Photos from Gifaataa Tube's post 27/05/2025

የተከበራችሁ የወላይታ ዞን ባለስልጣናት፣ ባለሀብቶች የተለያዩ የግል ድርጅቶች መሪዮች እና ባለቤቶች

የወላይታ ዲቻ እሁድ ሰኔ 1 ከሲዳማ ቡና ጋር ለሚጫወቱት የዋንጫ ጨዋታ ከወዲሁ አስፈላጊውን ሁሉ ዝግጅት እና ትብብር በማድረግ ለምሳሌ መኪና፣ ባንዲራ እና የዎላይታን ህዝብ ማንነት የሚያሳውቅ ዱንጉዛ እገዛ ከወዲሁ ቢጀመር መልካም ነው።

ክለባችን ወላይታ ዲቻ ዋንጫውን ይዞ እንዲመለስ ዘንድ ሙሉ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ያስፈልጋል።

አስፈላጊው ሁሉ ዝግጅት እና ትብብር ከተደረገ እና ተጓዥ ደጋፊዎችም በሜዳው ተገኝተው ለተጨዋቾቹ ድጋፍ ሞራል ቢሰጡ እና አስፈላጊው ሁሉ ትብብር ቢደረግ ዲቻ ዋንጫውን ይዞ እንደሚመለስ ትልቅ እምነት እና ተስፋ አለን

ምክንያቱም ክለባችን ዲቻ ከዚህ በፊት ዛማሊክን እዛው በሀገሩ እና እዚህ በሀገራችንም ጭምር አሸንፎ የማይፋቅ ታላቅ ድልን ማስመመዝገቡ ትልቅ ምስክርነት ነው። ድል ለወላይታ ዲቻ 💪
ኑናራ ዲያጌ ኡባ ጦንያጋ

Photos from Gifaataa Tube's post 27/05/2025
Want your business to be the top-listed Media Company in Sodo?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Address

S**o