Solomon & Genet Building Contractor

Solomon & Genet Building Contractor

Share

Photos from Solomon & Genet Building Contractor's post 01/07/2016

የሞጆ - ሀዋሳ የፍጥነት መንገድ ልዩ ገፅታዎች
202.48 ኪ.ሜ ርዝመት ያለው የሞጆ - ሀዋሳ የፍጥነት መንገድ በአራት ኮንትራቶች ተከፋፍሎ ነው ግንባታው የሚካሄደው።
የሞጆ - መቂ 56 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር፣ የመቂ - ዝዋይ 36 ኪሎ ሜትር፣ የዝዋይ - አርሲ ነገሌ 57 ነጥብ 1 ኪሎ ሜትር እና የአርሲ ነገሌ - ሀዋሳ 51 ነጥብ 68 ኪሎ ሜትር
እስካሁን የሞጆ - መቂ እና የመቂ - ዝዋይ ወደ ግንባታ ተሸጋግረዋል።
የዝዋይ - አርሲ እና የአርሲ ነገሌ - ሀዋሳ በጨረታ ሂደት እና ዝግጅት ላይ ይገኛሉ፡፡
በፍጥነት መንገዱ ግራና ቀኝ መሃል አካፋይ 9 ሜትር ስፋት ያለው ክፍት ቦታ የተተወ ሲሆን፥ ይህም በዛፎችና በአበቦች ይዋባል።
ከመንገዱ መነሻ እሰከ ማብቂያው ድረስ በግራና በቀኝ በኩል 1 ሚሊየን የሚሆኑ ዛፎች ይተከላሉ፡፡
መሉ ፕሮጀክቱ ሰውም ሆነ እንስሳት እንዳይገቡበት በአጥር የሚታጠር ይሆናል።
የአካባቢው ህብረተሰብና እንስሳት የፍጥነት መንገዱ ከአንዱ አቅጣጫ ወደ ሌላው አቅጣጫ በተሽከርካሪዎች ሆነ በእግር የሚያቋርጡባቸው ከመንገድ በላይ ወደ 59 የተለያዩ ቦታዎች የሚዘጋጅላቸው ሲሆን፥ ለተሽከርካሪዎች ደግሞ በተመሣሣይ 41 የተለያዩ ቦታዎች የመሬቱን እና የአካባቢውን አቀማመጥ ባገናዘበ መልኩ የሚገነባላቸው ይሆናል፡፡
መንገዱ የፍጥነት መቆጣጠሪያ ቴክኖሎጂም ይገጠምለታል።
በሁለተኛው የእድገት እና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን የአዳማ - አዋሽ - ሜኤሶ - ድሬዳዋ፣ አዲስ አበባ - ጅማ እና አዋሽ - ሰመራ ዘመናዊ መንገዶችን ለመገንባት ታቅዷል።
credit: Samson Wondimu

16/06/2016

★★ሰለሞን ገነት ሕንፃ ስራ ተቋራጭ ★★
ዘመኑ ባፈራቸው ምርጥ ልምድ ባላቸው መሀንዲሶች እና መሳሪያዎች በመታገዝ በጥራትና ለዕይታ ማራኪ በሆነ መልኩ ማሰራት የሚፈልጉት ማንኛውም አይነት ግንባታ አለዎት? እንግዲያውስ መልዕክት ያስቀምጡልን ስልክ ቁጥርዎን በመጨመር፡፡
ፔጃችን ላይክ ማድረግ አይርሱ፡፡ ለጓደኛና ወዳጅ ዘመድዎም ያካፍሉት፡፡

Want your business to be the top-listed Contractor in Sebeta?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address

Ethiopia Addis Ababa
Sebeta