blen dani

blen dani

Share

27/10/2025

በሀረሪ ክልል ከደረጃ በታች በሆኑ ኮሌጆች ላይ እግድ ተጣለ-የሀረሪ ክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ኤጀንሲ

ሀረር፣ጥቅምት 17/2018(ሀክመኮ):-የሀረሪ ክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ኤጀንሲ ከደረጃ በታች በሆኑ ሁለት ኮሌጆች ላይ እገዳ መጣሉን አስታወቀ።

የሀረሪ ክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ኤጀንሲ በማያ ግሎባል ና ሆርን ኢንተርናሽናል ኮሌጅ ላይ እገዳ መጣሉን አስታወቀ።

የሀረሪ ክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ኤጀንሲ ሀላፊ ወይዘሮ ኢማን መሀመድ እገዳው ኤጀንሲው የትምህርት ተቋማት አዲስ ቅበላና ስልጠና ለማስጀመር ያደረጉት ቅድመ ዝግጀት ላይ ያደረገውን ግምገማ መነሻ ያደረገ መሆኑን ገልፀዋል።

ኮሌጆቹ አሁን ባሉበት ደረጃ ምቹ የስልጠና አካባቢ ያልፈጠሩ፣አሰልጣኝ መምሀራን ከማዘጋጀት አንፃር ውስንነት ያለባቸው፣የአደረጃጀት መዋቅራቸው ደረጃውን የማያሟሉ ና ከእስታንዳርድ በታች በመሆናቸው እገዳው መጣሉን ገልፀዋል።

በተለይ ኮሌጆቹ ከግዜ ግዜ አቅማቸው እየወረደ የመጡና አዲስ ቅበላ ለማድረግ አስቸጋሪ በመሆኑ በስልጠና ሂደቱ እክል የሚፈጥሩ ሆነው መገኘታቸውንም አረጋግጠዋል።

በመሆኑም የተጣለውን እገጃ ተላልፈው የተማሪ ቅበላ የሚያደርጉ ከሆነ ኤጀንሲው አስፈላጊውን እርምጃ የሚወስድ መሆኑን አሳስበዋል።

አዳዲስ ሰልጣኝ ተማሪዎችም በኮሌጆቹ ላይ እገዳ የተጣለ በመሆኑ በኮሌጆቹ ለትምህርትና ስልጠና ከመመዝገብ እንዲቆጠቡ የኤጀንሲው ሀላፊ ወይዘሮ ኢማን መሀመድ ገልፀዋል።

27/10/2025
Photos from Harari Region Prosperity Party - ብልፅግና's post 27/10/2025
Photos from Harari Government communication affairs Office's post 27/10/2025
Photos from Ordin Bedri's post 26/10/2025
Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Harar?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address

Harar