The Inerside Miracles consultancy
08/03/2023
1."ባለ ትላልቅ አእምሮ ሰዎች በሃሳብ ላይ ይወያያሉ ፣ መካከለኞቹ በድርጊትና ሁኔታዎች ላይ ይወያያሉ ባለትናንሾች ግን ቁጭ ብለው ሰው ያማሉ ፡፡"
--ሪያኖር ሮዝቪልት
2.‹‹ መብረር ካልቻልክ ሩጥ ፡፡ መሮጥ ካልቻልክ ተራመድ ፡፡ መራመድ ካልቻልክ ዝግ ብለህም ቢሆን ሂድ ፡፡ ምንም ነገር ስታደርግ ወደፊት መሄድህን አታቋርጥ ፡፡››
--ማርቲን ሉተር
3.«ወደፊት የሚመጣውን ማንም አያውቅም ። ቁምነገሩ የሚመጣውን በልበሙሉነት ለመቀበል እንችል ዘንድ ዛሬን በብልሃትና በአግባቡ ተጠቅመን ፣ ነገን በናፍቆትና በደስታ መጠበቅ ነው ፡፡››
--ቻኒንግ ፓሎክ
4."እምነት አላማችንን የሚገነባበት መሰረት ነው ። የምንፈልገው ነገር ምንም ይሁን ምን እምነት ከሌለን ነዳጅ የሌለው መኪናን ለመንዳት እንደመሞከር ይሆንብናል ።"
--ናፖሊዮን ሂል
5.‹‹ ብርሃን ጨለማን ያሸንፋል እንጂ ጨለማ ጨለማን አይገፍም ፡፡ ጥላቻም በጥላቻ አይሸነፍም ፡፡ ያን ማድረግ የሚቻለው ፍቅር ብቻ ነው ፡፡ ››
--ማርቲን ሉተር
6."ወንዝ ድንጋይ ቦርቡሮ የሚገባው ሀይለኛ ስለሆነ ሳይሆን ያለማቋረጥ ስለሚፈስ ነው ፡፡"
--ጂም ዋትኪንስ
7."ህይወት በራሷ ፣ ምንም ያልተሳለባት ባዶ የሰዕል ሸራ ነች ። ስንፈልግ መከራን ፣ ስንፈልግ ሐሴትን የምንስልባት ባዶ ሸራ ።"
--ኦሾ
8."ጥንካሬና እድገት የሚመጡት (persistence) በተከታታይ ጥረትና ትግል ብቻ ነው ።"
--ናፖሊዮን ሂል
9."የሰው ልጅ ውድቀት አንደኛው መንስኤ የውሳኔ ማጣት ነው ። አንድ ሰው ምንም ያህል እምቅ እውቀት ቢኖረው ፤ ምንም ያህል የሚያሰደንቅ ሃሳቦችን ማመንጨት ቢችልም ውሳኔ መወሰን ካልቻለ ግን አቅሙ ሁሉ ከውስጡ አይወጣም ።"
--ናፖሊዮን ሂል
10." ለመጀመር ትልቅ መሆን አይጠበቅብህም ነገር ግን ትልቅ ለመሆን መጀመር አለብህ ፡፡"
--ዚግ ዚግላር
11."አንተ ጠንክረህ በዝምታ ስትሰራ ፣ ስኬትህ ጮኾ ይናገራል ፡፡ "
--ፍራንክ ኦሽን
12. ‹‹ እምነት ማለት ምንም እንኳን ሙሉው የሕይወት መሰላል ባይታይህም የመሠላሉን የመጀመሪያውን እርካብ መርገጥ ነው ፡፡ ››
--ማርቲን ሉተር
13." አንድ የደስታ በር ሲዘጋ ፣ ሌላ የደስታ በር ይከፈታል ። እኛ ግን አብዛኛውን ጊዜ ወደ ተዘጋው በር እንጂ ወደተከፈተልን አናይም ፡፡"
--ሔለን ኬለር
ብልጽግና ፓርቲ በተሣሣተ የኢኮኖሚ ፓሊሲው ህዝቡን በኑሮ ውድነት እየቆላው ይገኛል።ተፎካካሪ ፓርቲዎች ሊሞግቱት ይገባል!!
Click here to claim your Sponsored Listing.