Laangano Media
10/08/2025
ከስልጣን ፍላጎት እና በሴራ ፖለቲካ መሪዎችን በማጠላሸት ከሚደርሱበት መግታት አይቻልም።
******************************************
የሰሜናዊ ሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳር የተከበሩ Biruk Solomon በሰራባቸው ተቋማት ውጤታማ እና ፈርሃ-እግዚአብሔር መሪ ናቸው ። ጎርቼ ወረዳ አስተዳዳር በነበሩበት ወቅት 4 አምቡላንስ 1 Hardtop መክና እና ከ50 በላይ ሞተር ሳይክል እንድገዛ በማድረግ ትልቅ አሻራ ያስቀመጠ ጀግና መሪ ሲሆን ከኃላፊነት የተነሳዉም ተገምግሞ ሳይሆን በወቅቱ በነበረው በሴራ ፖለቲካ ነው።
ሀዌላ ወረዳ አስተዳዳር ሆነው በሰሩበት ወቅት ለሕዝባቸው ዝቅ ብለው ያገለገሉ በተለይም መሠረተ ልማት ላይ ትልቅ አሻራ ያስቀመጡ መሪ ሲሆኑ በ 11፡11 ወቅት በህቡዕ በተደራጁ ቡድኖች ግፊት ከኃላፊነት የተነሳ ሲሆን በቅርቡ ሽማግሌዎቹ "በአንተ ላይ ግፍ ተፈጽሟል...Ati daafurtanna Xiimbannahe La'noommoti Sorotena agurinke" ብለዋል።
የአሁኑ የሚዲያ ጦርነት ዓላማው በጎሳ ቀመር በክልሉ ካብኔ በመሆን ስልጣንን ለመቆናጠጥ የሚፈልጉ ወዳጅ መሳይ ሸንጋዮች የከፈቱት ዘመቻ ሲሆን ከሚደርስበት እና እግዚአብሔር ካሰበለት ከፍታ መግታት አይችሉም። በክልሉ ካሉ ዞኖች በተግባር አፈጻጸም ሰሜናዊ ሲዳማ ዞን 1ኛ መሆኑ የሚታወስ ነው።
13/04/2025
NGO ድጋፍ የተሰሩ ጥቅል ጎመን እና ዶሮ እርባታ ባሻገር ላለፉት ሳባት አመታት ለፕሮፓጋንዳ ታስቦ ተጀምረው ዉሃሽታ ሆኖ የቀሩ ፕሮጀክቶች ስንከት፤
1. Affini Hara (ሲዳማ ባህል ማዕከል) 2008 ዓ.ም የተጀመረ
2. ሻፌታ ታውር 2013 ዲዛይን ተደርጎ ግዜያዊ የፖለትካ ፕሮፓጋንዳ ተሰርቶ የተረሳ፤
3. ሀዋሳ ኢኮ ቱሪዝም (ሀዋሳ ሙሉ የሚዞር ፕሮጀክት)
4. ታቦር ታራራ ዙሪያ የሚዞር ማራቶን እስፓልት)
5. ታቦር ታራራ ፕሮጀክት ( ፀጋዬ ቱከ ያስጀመረ)
6. የሎቀ ሰማዕታት ሀውልት ፕሮጀክት
7. ከጥቁር ውሃ እስከ ሞኖፖሊ ድረስ የሚወስድ ኮርደር ልማት፤
8. የቀድሞ የሲዳማ ዞን ስም እየተገነባ ያለው የአስተዳደሪ ህንፃ፤
9. ከኖክ እስከ ጫፌ ድረስ እየተሰራ ያለው አስፓልት ( ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሁለት ቦታ ከፍሎ የሚያልፍ አስፓልት )
10. ከቴክኒክ ሙያ እስከ ሞኖፖሊ ድረስ እየተሰራ ያለው አስፓልት፤
11. ከአላሙራ ኃይስኩል እስከ ዶሮ እርባታ አድርጎ ፤ ማረሚያ በኩል ይዞ ሎቀ ድረስ ሄደው የሚወጣ አስፓልት
12. ከአልቶ ሔዋኖ ት/ቤት እስከ አቡነ ጊዮርጊስ ት/ቤት ድረስ ያለው መንገድ
14. ከቱላ ክ/ከተማ እስከ ሎቄ ድረስ እየተሰራ ያለው አስፓልት
እነኚህ ፕሮጀክቶች ከዚህ በፊት ያሉ አመራሮች ተጀምሮ እስከአሁን ድረስ ሳይጠናቀቁ ብዙ ገንዘብ ፈሶባቸዉ (ክፍያው ሙሉ ወይም በከፍል ተከፍሎ ያለቀ) መንገድ ላይ ቆሞ የቀሩ ናቸው።
ህዝባዊ የለዉጥ ትግል ተጠናክሮ ይቀጥላል ✊
Sidama Affairs SA
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the public figure
Website
Address
HAWASA