GLN
08/03/2021
የአማሮ ልዩ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ኃላፊ ተገደሉ።
የአማሮ ልዩ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ በተከፈተባቸዉ ተኩስ ህይወታቸዉ አለፈ።
የልዩ ወረዳዉ ዋና አስተዳዳሪ ቆስለዉ አርባ ምንጭ ሆስፒታል እንደገቡ ተሰምቷል።
ጥቃቱ የተፈፀመው በፀረ ሰላም ኃይሎች (የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች) ነው ብሏል የወረዳው መንግስት።
እንደ አማሮ ወረዳ መረጃ በተከፈተው ተኩስ የቡዙሃን ህይወት አልፏል፤ በርከት ያሉ ሰዎች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል።
እስከ አሁን ባለው መረጃ የ 8 ሠላማዊ ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን በጫካ ውስጥ የተበታተኑ እና ያልተገኙ ስለላሉ ቁጥራቸው ከዚህ ሊበልጥ ይችላል ተብሏል።
ጥቃቱ የተፈፀመው በአማሮ ወረዳ እና በምዕራብ ጉጂ ዞን አጎራባች ቀበሌያት መካከል ሠላማዊ ስብሰባ እየተካሄደ በነበረበት ወቅት ነው ሲል የልዩ ወረዳው ኮሚኒኬሽን ገልጿል።
Want your school to be the top-listed School/college in Awassa?
Click here to claim your Sponsored Listing.
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Awassa