Odaa Bus

Odaa Bus

Share

Photos from Gola Bishooftuu's post 04/09/2019
17/06/2019

Oduu Gaddaa
Abban MMI Dr Abiiy
Ahmad Alii Abba fixaa du'aan Aduunyaa kanarra boqotaniru!!

Rabbiin jannata haa keenuf

02/04/2019

Happy first year Anniversary Mr. Prime minster. The last year was ful of challenges and so many good things have happened. I hope you will keep up the good things and learn from the mistakes and succeed in building new Ethiopia. Wish you the best of luck in the rough road ahead. It is not going to be easy but millions are behind you to support in every way they can. The detractors are also there who see everything you do as a threat to their individual or group interests. Particularly those who want to revive the dead Ethiopia that only accepts one particular group and alienates the rest. For these group, Ethiopia is just them. These nostalgic group should have understood long ago that that Ethiopia is certainly gone forever. OPDO of keessaa qulqulleessuu hin dagatinaa!

14/03/2019

የቆርጦ ቀጥል የማጥላላት ፕሮፓጋንዳ ዘመቻና ያለው ነባራዊ እውነታ
==========================================
ቪዲዮ ቆርጦ በመቀጠል የአመራሩን ሞራል መስበር አይቻልም!
(ሀይሌ ጥላሁን)

ቪዲዮ ቆርጦ በመቀጠል እና የቋንቋ ትርጉም በማዛባት ነገሮችን ከተነገሩበት ኮንቴክስት ዉጪ በሌላ ትርጉም በማቅረብ ህዝብን የማባላት አመራሩ ላይ ጥርጣሬ እንዲፈጠር ማድረግ ሰሞነኛዉ ሴራ ሆኗል፡፡ ለአብነትም ኦቦ ለማ መገርሳ በተለያዩ ጊዜያት በመድረኮች ያደረጓቸዉን ንግግሮች ቆርጦ በመቀጠል ንግግሮቹ ከተደረጉበት አዉድ ዉጭ በሌላ ትርጉም በመቅረብ ህዝብ በጥርጣሬ እንዲያያቸዉ ለማድረግ የማደናገር ስራዎችን በመሰራት ላይ ይገኛል፡፡

ሰሞኑን የኦዴፓ የገጠር ዘርፍ ሀላፊ በአቶ አዲሱ አረጋ ላይም ተመሳሳይ ጥቃት እየተፈጸመ ይገኛል፡፡ አቶ አዲሱ ከኦሮሞ አርቲስቶች እና አትሌቶች ጋር በኦሮሞ ባህል ማዕከል አድረገዉት የነበረዉን ዉይይት ሙሉ ቪዲዮዉን የማየት እድል አጋጥሞኛል፡፡ የመድረኩ ተሳታፊዎች በአዲስ አበባ ከተማ መስፋፋት ምክንያት አርሶ አደሩ ላይ ስለደረሰ መፈናቀል በዚህም ምክንያት ወደ ልመና የገቡ እና ራሳቸዉን ያጠፉ አርሶ አደሮች መኖራቸዉን፣ ከአዲስ አበባ ከተማ የሚወጣዉ ፍሳሽ እና መርዛማ ኬሚካል የኦሮሞ አርሶ አደሮችን ኑሮ እያመሰቃቀለ መሆኑን፣ አዲስ አበባ የኦሮሞን አርሶ አደሮች እየበላች እና እየገፋች ወደ ጎን ስተሰፋ ኦዴፓ ምንም የተጨበጠ ስራ አለመስራቱን፤ የተፈናቀሉ አርሶ አደሮችን ለማቋቋምስ ምን ተሰራ ምን ያህል በጀት ያዛችሁ፤ ኦሮሚያ ከፈፊንፊኔ ልታገኘዉ ስለሚገባዉ ልዩ ጥቅም ምንም አልሰራችሁም የሚሉና ሌሎች እጅግ በጣም በስሜት የተሞሉ እና መድረኩን እስከመበተን በሚያደርስ ቶን ሲያቀርቡ ነበር፡፡

አቶ አዲሱም በመድረኩ ማጠቃለያ ለጉዳዩ በተረጋጋ ሁኔታ ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡ በሰጠዉ ማብራሪያም የኦሮሞ አርሶ አደሮች ጭቆናና የመፈናቀል ችግር የዛሬ ሳይሆን ከመቶ ሃምሳ አመት ጀምሮ ያለ ጉዳይ መሆኑን፣ ይህን ችግር በትኩረት መፍታ እንደሚያስፈልግ ተናግሯል፡፡ ኦሮሚያ ከፊንፊኔ ማግኘት ስለሚገባት ልዩ ጥቅምን አስመልክቶም በረቂቅ ህጉ ዉስጥ የተጠቀሱ መሰረታዊ ጉዳዮች(የመርዛማ ኬሚካሎችና የቆሻሻ አወጋገድን ማስተካከል፣የትራንስፖርት ቅንጅት፣ የማህበራዊ አገልግሎቶች፣ የተፈናቀሉ አርሶ አደሮችን መልሶ ማቋቋም…) ወደ ፓርላማ ሳይኬድ፣ የተለየ ህግም ሳይወጣለት በአዲስ አበባ በከተማ መስተዳድር አመራር በእነ ኢንጂነር ታከለ ኡማ እና በካቢኔያቸዉ አማካይነት እየተሰራ እንደሆነም አብራርቷል፡፡ በዚኅ ረገድም ከከተማዉ የሚወጡትን መርዛማ ኬሚካሎች አወጋገድ፣ በከተማዉ ጥግ ጥግ ላይ የሚገኙ የአርሶ አደር ልጆች በቋንቋቸዉ እንዲማሩ የማድረግ ወዘተ ልዩ ጥቅም እና ህግ ማዉጣት ጋር ሳይደርስ በነ ኢንጅነር ታከለ አመራር ሰጪነት እንደሚፈታ ለዚህም ኦዴፓ ጠንክሮ እንደሚሰራ አጠንክሮ ተናግሯል፡፡

አቶ አዲሱ ይህን ጉዳይ በ
ማብራራት ላይ እያለም ከተሳታፊዎቹ አንዱ አቋርጦት ይህን ችግር ለመፍታት ምን ያህል በጀት መድባችኋል እንዴትስ እናምናቸኋለን የሚል ጥያቄ ቀርቦለታል፡፡ ለጥያቄዉም ማብራሪያ በሚሰጥበትም ጊዜ ሁሉንም ነገር በመድረክ መናገር አስቸጋሪ እነደሆነ፤ ይህን ያህል በጀት ተመድቧል ብሎ ዳታ መጥቀስ እንደሚቸገር፣ ነገር ግን የኦሮሞን አርሶ አደር እና የኦሮሞን ህዝብ ጥቅም ለማስከበር የቲም ለማ አመራር ቡድን ላይ በተለይም የኢንጂነር ታከለ ዑማ አማራር ላይ እምነት አንዲጥሉ እና እንዲጉፉአቸዉ ተማጽኖ ጭምር አቅርቦላቸዋል፡፡

አቶ አዲሱ በማብራሪያዉ ላይ አክሎም የተፈናቀሉ አርሶ አደሮችን መልሶ ለማቋቋም እና ከዚህ በፊት ተከስተዉ የነበሩ ችግሮችን ለማረም ከንቲባ ታከለ ዑማ ቆራጥ አቋም ወስዶ በመስራት ላይ እንደሚገኝ ይህንን ማድረጉን ያልወደዱ አካላትም ኢንጂነሩ ላይ ሰፊ የስም ማጥፋት እና ስራዉን የማጠልሸት ስራ እየተሰራ መሆኑን አጥብቆ ተናግሯል፡፡

አቶ አዲሱ አረጋ በዚህ መድረክ የተናገራቸዉ ንግግሮች በእኔ እምነት በምንም መልኩ ለአንድ ወገን ያደላ እና በአሻጥር ፖለቲካ ሊፈረጅ የሚችል አይደለም፡፡ ግለሰቡ የኦሮሞ ፖለተከኛ እንደመሆኑ መጠን፣ በመድረኩ ላይ ሲሳተፉ የነበሩትም የኦሮሞ አርቲሰቶች እና አትሌቶች እንደመሆናቸዉ መጠን፣ ከምንም በላይ ደግሞ እጅግ በጣም ተካረሮ ከነበረዉ እና ሊበተን ጫፍ ደርሶ ከነበሩ የመድረክ ሁኔታ እነጻር ምንም ስህተት አለበት ብዬ አላምንም፡፡

የዚህ ስም ማጥፋት ዘመቻ ዋናዉ ጉዳይ ግን ወዲህ ነዉ፤፤ የኦሮማራን ጽንሰ ሃሳብ ያፈለቁት እና የወያኔን የከፋፍለህ ግዛ ሴራ በአፍ ጢሙ እንዲደፋ ካደረጉት አመራሮች ዉስጥ አዲሱ አረጋ እና ንጉሱ ጥላሁን ግንባር ቀደሞች እንደሆኑ ሁላችንም እናዉቃለን፡፡ የዚህ ቪዲዮ ቆርጦ በመቀጠል እና የቋንቋ ትርጉም በማዛባት ነገሮችን ከተነገሩበት አዉድ ዉጪ በሌላ ትርጉም በማቅረብ ሴራ የአማራዉ ህዝብ የኦሮሞ አመራር ላይ ያለዉን ጥርጣሬ በማሳደግ ወደ እርስ በርስ መበላላት መዉሰድና የለዉጥ እንቅስቃሴዉን መቀልበስ ነዉ፡፡

እኔ በግሌ አዲሱ አረጋን አዉቀዋለሁ፡፡ በህዝቦች እኩልነት እና ወንድማማችነት የሚያምን ሁሉም ኢትዮጵያዉያን በነጻነት መኖር አለባቸዉ ብሎ በጽኑ የመሚያምን ሰዉ ነዉ፡፡ ለዚህም ባለዉጡ እንስቃሴ በፍጹም ቅንነት እና ጀግንነት እየታገለ ያለ ከሴራ ፖለቲካም ሆነ ከጽንፈኛ ብሄርተኝነት የጸዳ ግለሰብ ነዉ፡፡ እኔ በበኩሌ ለአዲሱ አረጋ አንድ ምክር አለኝ ለሴረኞች እና ለቆርጦ ቀጥል ቀጣፊዎች ጆሮህን አትስጥ፡፡ ዉሾቹ ቢጮሁብህም ጉዞህን ወደ ፊት ቀጥል!!

ቸር እንሰንብት!

Want your school to be the top-listed School/college in Ambo?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Address

Ambo