Binyam

Binyam

Share

06/04/2026

✅ ስኬታማ መሆን ትፈልጋለህ?

• ሌሎች በሚተኙበት ጊዜ አጥና

• ሌሎች በሚያቅማሙበት ጊዜ ወስን

• ሌሎች ነገ እያሉ በሚያስተላልፉበት ጊዜ ጀምር

• ሌሎች ዝም ብለው በሚመኙበት ጊዜ ሥራ

• ሌሎች በሚያባክኑበት ጊዜ ቆጥብ

• ሌሎች በሚያወሩበት ጊዜ አዳምጥ

• ሌሎች ፊታቸውን በሚያጠቁሩበት ጊዜ ፈገግ በል

• ሌሎች ተስፋ ቆርጠው በሚተዉበት ጊዜ ጽና።

06/04/2026

የጥፋተኝነት ስሜት እንዲህ ይላል፦
“ከባድ ስህተት ሰርተሃል።”

የእፍረት ስሜት እንዲህ ይላል፦
“ሁልጊዜ ስህተት ትሰራለህ።”

ጸጋ እንዲህ ይላል፦
“ያ ስህተት ማንነትህን አይገልጽም።”

እድገት እንዲህ ይላል፦
“ከዚያ ስህተት ተማርና የተሻልክ ሁን።”

ሁሉንም ሂደቶች ማለፍህን እርግጠኛ ሁን እንጂ ከእፍረት (ውርደት) በኋላ አትቁም።

09/02/2026

ለሰው ታመን እንጂ ሰውን ብዙ አትመን። እወደዋለሁ እንጂ ይወደኛል አትበል። የራስህን እንጂ የሌላውን ማንነት በእርግጠኝነት አታውቅምና።

09/02/2026

የጊዜ እንጅ የሰው ጀግና የለውም!!

👉 ሁሉም በጊዜው ውብ ነው።እባብ በህይወት እያለ ጉንዳንን ይበላል፡፡እባብ ሲሞት ደግሞ ጉንዳኖች ይበሉታል፡፡ጊዜ በማንኛውም ሰዓት ይለወጣልና በህይወትህ የማንንም ዋጋ አናሳንስ።ምን አልባት ዛሬ ጉልበተኛ ሆነን ከሌሎች የተሻልን
ሀይለኛ የሆን ይመስለን ይሆናል።ጊዜ ግን ከእኛ የበለጠ ጉልበተኛ ነው።

👉የዛሬው ህፃን የነገ ጎረምሳ ነው፣የዛሬው ጉልበትህ ነገ ይከዳህና ትላንት ህፃን ባልከው ይተካል።አስብ አንድ ዛፍ መቶ ሺ ክብሪቶችን ሲሰራ አንድ ክብሪት ግን መቶ ሺ ዛፎችን ታቃጥላለች፡፡አንድ መጥፎ ስራም ብዙ መልካም ነገሮችን ታጠፋለች፡፡ወናው ነገር በአስተሳሰብ መልካምና ቅንነትን ተላብሶ መኖር መቻል ነው።

👉የሰውን ልጅ ቀና የሚያደርገው ትራስ ሳይሆን ጊዜ ነው።በዚህ አለም ላይ የጊዜ እንጅ የሰው ጀግና የለውም። ረጋ ብለህ አስብ ሁሉም በጊዜው ውብ ይሆናል። ትዕግስት ካለ ሁሉም እንደ ፈጣሪ ፍቃድ ማጣት በማግኘት፣መራብ በጥጋብ፣ አለማወቅም በማወቅ ይተካል። ለሁሉም ጊዜ አለውና የእናንተ የሆነውን ጊዜ የምንጠብቅበትን ትዕግስት ይስጣችሁ።

08/02/2026

አንዳንዴ...
ግትር ሞጋችነት
ወንድነት አይጠቅምም፤
ያፈቀርከው
የወደድከው
በሩን ሲዘጋብህ
መመልከት ብቻ ነው - የሚኖርህ አቅም፤

በእርግጥ አቅም አይናቅም
የተዘጋብህ በር ባይነቃነቅም
ቁጭ አለ እንዳትባል
ዝም አለ እንዳትባል
በሩን ትዞራለህ - ደጇ ታደባለህ፤
ታውቃለህ አትወጣም
በሩ አይከፈትም
ግን ትጠብቃለህ፤

30/01/2026

የህይወት ምጥቀት
​"በሙሉ አቅምህና በከፍታ መኖር አለብህ፤ የህልውናን አስደናቂ ውበት ልትረዳ የምትችለው ያኔ ብቻ ነው።
​ከዚያ የንቃት ከፍታ ላይ ስትሆን ብቻ ነው፣ በየሰከንዱ የሚፈስሰውን ታላቅ ግርማና ማለቂያ የሌለውን የህይወት ድግስ ማየት የምትችለው።
​በሙሉ ማንነትህ አለመኖር ማለት ደግሞ ህይወትን መሳት ነው፤ በህይወት ውስጥ የሚገኙትን ውበቶችና በረከቶች በሙሉ ማጣት ማለት ነው።"

29/01/2026

ብዙዎቻችን "ፍጹም" ለመሆን ስንጥር "እውነተኛ" መሆንን እንዘነጋለን። እራስን መሆን ማለት ስህተት የማይሰራ ሰው መሆን ማለት አይደለም፤ ይልቁንም በስህተቶቹ የማይሸማቀቅ፣ ከውድቀቱ የሚማር እና በሂደት ላይ ያለ ማንነትን በፀጋ መቀበል ነው።

29/01/2026

አንዳንድ ሰዎች የእኛን ማንነት ሳያውቁ በራሳቸው መንገድ ሊተረጉሙን ይችላሉ እነሱ የፈለጉትን ያክል ስለ እኛ ማንነት ማሰብ ይችላሉ ደስ የሚለው ነገር ግን የኛ ትክክለኛ ማንነት አንዳንድ ሰዎች በሰጡት መላ ምት የሚወሰን ባለመሆኑ ነው
👉ማንም ምንም ቢል የኛ ማንነት የኛ ነው ሰው ስላለ አይቀየርም።

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Adis?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address

Adis