Goitom Abrha

Goitom Abrha

Share

27/03/2024

እውነተኛ እርዳታ እንዴት ያለ ነው?
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
አንድ ቀን እናቴ ጎረቤቶቻችንን ጨው ስትጠይቅ ሰማሁ። ነገር ግን ቤት ውስጥ ጨው ነበረን ስለዚህ ለምን ጎረቤቶችን ጨው እንደምትጠይቅ ጠየቅኳት። እሷም መለሰችልኝ:-—"ምክንያቱም ልጄ ጎረቤቶቻችን ብዙ ገንዘብ ስለሌላቸው በቤታቸው የተቸገሩትን ብዙ ጊዜ ይጠይቁናል። እኔም ደግሞ እንደምፈልጋቸው እንዲሰማቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ ትንሽ እና ውድ ያልሆነ ነገር እጠይቃቸዋለሁ፤ በዚህ መንገድ እነሱ የሚፈልጉትን ሁሉ እንዲጠይቁን የበለጠ ምቾት እና ቀላል ይሆንላቸዋል።"አለችኝ
የእናቴ መልስ እራሴን እንዳይበት አደረገኝ። ከኔ በተለያየ መንገድ አቅማቸው ያነሰ ጓደኞቼን እንዴት ነው የማግዛቸው? የበለጠ አለመቻላቸው እንዲሰማቸው በማድረግ፣ በማሳቀቅ፣ ሌሎች እንዲያውቁልኝ ለታይታ ወይስ ለክብራቸው በመጠንቀቅ?
ከእናቴ የተማርኩት ከልብ የሆነ ርህራሄ፣ ትህትና፣ ደጋፊነትን ነው። እገዛ ስንፈልግ ጓደኛቻን፣ ጎረቤቴቻችን ወይም እርዳታ የጠየቅነው ሰው እንዲሰጠን የምፈልገውን ምቾትና ክብር እኛም ልንሰጥ ይገባል። ጓደኞቻችንን፣ ጎረቤቶቻችን ወይም ማንኛውንም ሰው ስንደግፍ በእውነተኛ ኢትዮጵያዊ ባህላችን እና እሴቶታችን ለሰው ልጅ ክብር እና ስሜት በመጠንቀቅ ሊሆን ይገባዋል!!!...

የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ
አበቃሁ
*የታሪክ ምንጭ- ፋጢማ አንፊግ
✍️ Hanna Yeshinegus (18/7/2016)

24/03/2024

በዚህ አለም የሚያረጋጋ ቃል ቢኖር አንዱ "ሁሉም #ያልፋል" የሚለው ነው፤ #ሀዘኑም ያልፋል፣ደስታውም ያልፋል፣ ንዴቱም ያልፋል፣ እርካታውም ያልፋል፤ ሌላውን ተወው አንተም እኔም #እናልፋለን! በፍጥረት አለም ፀንቶ የሚኖር ነገር ቢኖር አምላክ ብቻ ነው።

ታዲያ ለሚያልፍ ችግር ለምን አብዝተህ ትጨነቃለህ? ለሚያልፍ ቀን ለምን ራስህን ትጎዳለህ? ህይወትህን ነብስ ዝራበት፤ የምትወደውን ስራ፣ የምትወዳትን የራስህ ለማድረግ ተዘጋጅ፣ #መንፈሳዊነትህን ሳትለቅ የምድርን በረከት ሁሉ አጣጥም፤ #ሳታልፍ በፊት #ኑር ወዳጄ!

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Adigrat?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address

Adigrat